>

ታላቁ የኢትዮጵያ መሪ  ግ/ቀ/ አጼ ኃይለ ሥላሴ ከ58 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬው እለት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት [OAU] እንዲወለድ ያደረጉት ታሪካዊ ንግግር! (አቻምየለህ ታምሩ)

ታላቁ የኢትዮጵያ መሪ  ግ/ቀ/ አጼ ኃይለ ሥላሴ ከ58 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬው እለት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት [OAU] እንዲወለድ ያደረጉት ታሪካዊ ንግግር!
አቻምየለህ ታምሩ

ግርማዊ  ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከታች የምታደምጡትን የ40 ደቂቃ ታሪካዊ ንግግር ከዛሬ 58 ዓመታት በፊት ግንቦት 17 ቀን 1955 ዓ.ም. ያደረጉት ሲሆን ታሪካዊ ንግግሩ በንጉሡ ግብዣ አዲስ አበባ ላይ ተሰብስበው የነበሩ ነጻ የአፍሪካ መንግሥታት መሪዎች የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እንዲመሰረቱ ያደረገ የ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ  ታላቅ ንግግር ነው።  የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የተወለደው በዚህ የንጉሠ ነገሥቱ  ታሪካዊ ንግግርና  ታላላቆቹ ረዳቶቻቸው ባደረጉት የረቀቀ ዲፕሎማሲ ጥረት ነው።
የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ውልደት የንጉሠ ነገሥቱ የድካም ውጤት እንደሆነ ከኛ ከኢትዮጵያውያን በላይ የሚያውቁት አፍሪካውያን ግርማዊ ጃንሆይን «የአፍሪካ አባት» ሲሉ በክብር ይጠሯቸዋል። በአፍሪካ ኅብረት መታሰቢያ የቆመለት ዶክተር ክዋኔ ንክሩማህ ሳይቀር የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በግርማዊ ንጉሠ ነገሥቱ ድካም መመስረቱን ተከትሎ በዚያው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በተወለደበት የአፍሪካ አዳራሽ ባደረገው ታሪካዊ ንግግር የኢትዮጵያን አስተዋጽኦ በግጥም እንዲህ ሲል ገልጾታል፤
Ethiopia shall rise
Ethiopia, Africa’s bright gem
Set high among the verdant hills
That gave birth to the unfailing
Waters of the Nile
Ethiopia shall rise
Ethiopia, land of the wise;
Ethiopia, bold cradle of Africa’s ancient rule
And fertile school
Of our African culture;
Ethiopia, the wise
Shall rise
And remold with us the full figure
Of Africa’s hopes
And destiny.
ወገንተኛ ያልሆኑ አፍሪቃውያንም ታላቁን የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን «ኃይለ ሥላሴ የአፍሪቃ አባት» በማለት ያዜሙሏቸው ለአፍሪካ በዋሉት ውለታና ለአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ባደረጉት ወደር የሌለው አስተዋጿቸው ነበር። ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን የአፍሪካ አባት አይደሉም ብሎ የተከራከረው «ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር አንድ ሰዓት ቁጭ ብሎ ማውራት ዩንቨርስቲ ገብቶ ተመርቆ ከመውጣት እኩል ነው፤ ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር መቀመጥና መነጋገር አንድ ቤተመፃሕፍት ከመግባት ጋር እኩል ነው» ሲል የተናገረው ነውረኛው መለስ ዜናዊ ብቻ ነበር።
ከአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ውልደት ኀምሳ አመታት በኋላ የተመሰረተው የአፍሪካ ቨርቹዋል ዩኒቨርሲቲ፤ በቅኝ ግዛት ውስጥ ስለነበሩ አገሮች እርዳታ፤ አንድ አፍሪካ ከመመስረቱ በፊት በተለያዩ የአፍሪካ ክፍለ አሕጉራዊ አካባቢዎች ሊመሰረቱ ስለሚገባቸው ስለ AMU, CEN-SAD, COMESA, EAC, ECCAS, ECOWAS, IGAD and SADC ምክረ ኃሳብ ያቀረቡትም ግርማዊ ጃንሆይ ነበሩ።
ግርማዊ ጃንሆን በንግግራቸው መጨረሻውም አዲስ አበባ የተሰበሰቡት ነጻ የአፍሪካ መሪዎች በኢትዮጵያ የተዘጋጀውን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ቻርተር እንዲፈርሙና ከታሪክና ትውልድ ተወቃሽነት እንዲተርፉ በእግዚያብሔር ስም ጠይቀዋቸዋል። መለስ ዜናዊ ክዋሜ ንክሩማህን የአፍሪካ አባት ያደረገው በዚህ መልክ ሞግተው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እንዲቋቋም ያደረጉትን ታላቁን ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን ያዋረደ መስሎት ነበር።
ሆኖም ግን እውነት ይዘገያል እንጂ ተደብቆ አይቀርምና እነሆ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እንዲመሰረትና በአዲስ አበባው ጉባኤ ድርጅቱን ሳይመሰረት የአፍሪካ መሪዎች ቢለብያዩ እያንዳንዳቸው የአፍሪካ መሪዎች በታሪክና በትውልድ ሲወቀሱ እንደሚኖሩ የሞገቱበት የጭካኔ ታላቅና ታናሽ ወንድማማቾቹ መንግሥቱ ኃይለ ማርያምና መለስ ዜናዊ ግን የደበቁበት የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሙሉ ታሪካዊ ንግግር እንዲህ ተቆፍሮ ሊወጣ ችሏል።
Filed in: Amharic