በኢትዮጵያ ሠማይ ሥር እየተካሄዱ ላሉ አስር እውነቶች እጮሃለሁ!
አሰፋ ሀይሉ
1. በኦነግ-መራሹ መንግሥት በትግራይ ህዝብ ላይ በትግራይ እየተካሄደ ያለው ጭፍጨፋ እንዲቆም እጮሃለሁ!
2. በኦነግ-መራሹ መንግሥት በአማራ ህዝብ እና በኦርቶዶክስ ክርስትያኖች ላይ በኦሮሚያና በጉሙዝ እየተካሄደ ያለው ጭፍጨፋ እንዲቆም እጮሃለሁ!
3. በኦነግ-መራሹ መንግሥት ሰብዓዊ መብታቸው ተረግጦ በእሥር የሚንገላቱት እነ እስክንድርና ሌሎች እንዲለቀቁ እጮሃለሁ!
4. በኦነግ-መራሹ መንግሥት የአማራ ሀይል ከራሱ ምድር (ከወልቃይት-ሑመራ-ፀለምት-ራያ) ለማስወጣት ‹‹አማራ ከምዕራብ ትግራይ ይውጣ›› በሚል ከኢዜማና ዓለማቀፍ ሀይሎች ጋር እየተዶለተ ያለው መጠነ-ሰፊ ሴራ በአስቸኳይ እንዲቆም እጮሃለሁ!
5. ኦነግ-መራሹ መንግሥት የተሳሳተ መረጃ ለዓለም በማሰራጨት እያደረገ ያለውን ፀረ-አማራ በጀርባ የማስወጋት ሴራ ለማክሸፍ፣ በቻልኩት ሁሉ መንገድ፣ የውጪ መንግሥታትና ዓለማቀፍ ተቋማት የአማራ ሕዝብ ወደታሪካዊ ግዛቱ እንደተመለሰ እንዲያውቁ አብክሬ እጮሃለሁ!
6. በኦነግ-መራሹ መንግሥት ግብዣ ወደ አልፋሽካ የገባው የሱዳን ጦር ሠራዊት ከኢትዮጵያ ምድር እንዲወጣ እጮሃለሁ!
7. በኦነግ-መራሹ መንግሥት ግብዣ እስከ አክሱምና አድዋ የገባው የኤርትራ ሕዝብ ሠራዊት ለአላስፈላጊ ጦስ ከመዳረጉ በፊት ከኢትዮጵያ ግዛት እንዲወጣ እጮሃለሁ!
8. በኦነግ-መራሹ መንግሥት እየተቀነባበሩ ያሉ ዘረኛ፣ ጠባብና ከፋፋይ የኦሮሙማ ፋሺስታዊ ሴራዎችና ፕሮጀክቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ ከሁሉም ጉዳዮች በላይ አብዝቼ እጮሃለሁ!
9. በኦነግ-መራሹ መንግሥት አማካይነት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የተደቀነው ሥጋት ከወያኔም ሆነ ከማንኛውም ውጫዊ አካል ከሚመጣ ሥጋት ሁሉ የበለጠ የህልውና ሥጋት ውስጥ የሚጨምረን መሆኑን ደግሜ ደጋግሜ ሚሊዮን ጊዜ እጮሃለሁ!
10. በኦነግ-መራሹ መንግሥት የተጠለፈው የመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ፀረ-ኢህአዴግ የዲሞክራሲ ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል አምባገነኑና ገዳዩ ኢህአዴግ ከሥልጣን እስኪወርድና የተመኘነው ለውጥ እስኪመጣ ድረስ፣ ትንፋሼ እስከፈቀደልኝ ደጋግሜ እጮሃለሁ!
አንድ ቀን ጩኸታችን ወደ እውነተኛ ተጋድሎ ይቀየራል!
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!
ይኸው ነው!