>

 ". ...ከዛሬ ጀምሮ ፍርድ ቤት መቅረብ አንፈልግም... !!! እነ ጃዋር መሐመድ - ኢትዮ ኢንሳይደር

 

 “. …ከዛሬ ጀምሮ ፍርድ ቤት መቅረብ አንፈልግም… !!!

እነ ጃዋር መሐመድ
 
*…የረሀብ አድማ እናደርጋለን…!!!” 
ኢትዮ ኢንሳይደር

በእነ ጃዋር መሐመድ መዝገብ የተከሰሱ 24 ተከሳሾች ከዛሬ ጀምሮ ጉዳያቸውን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት እንደማይቀርቡ አስታወቁ። ተከሳሾቹ በትግራይ እየተካሄደ ነው ያሉትን “የጅምላ ግድያ እና ኢ-ፍትሃዊ አገዛዝ” ለመቃወም ለሁለት ቀናት የረሃብ አድማ እንደሚያደርጉም ገልጸዋል።
ተከሳሾቹ ፍርድ ቤት ያለመቅረብ ውሳኔያቸውን ያስታወቁት፤ መደበኛ የክስ ሂደታቸውን እየተመለከተ ላለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሁለተኛ የጸረ-ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት ዛሬ ረቡዕ ግንቦት 18 በጽሁፍ ባቀረቡት አቤቱታ ነው። በችሎቱ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ ጃዋር መሐመድ የኮሎኔል ገመቹ አያና እና የሌሎች ተከሳሶችን ጉዳይ በመጥቀስ የፍርድ ቤት ውሳኔ በተገቢው መንገድ ተፈጻሚ እየሆነ አይደለም ብለዋል።  “እኛ እዚህ የመጣነው ከተፈረደብን ለመቀጣት፤ ነጻ ከተባልን ለመውጣት ነው” ያሉት አቶ ጃዋር፤ “ከዛሬ ጀምሮ በገዛ ፍቃዳችን ፍርድ ቤት አንቀርብም” ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አስታውቀዋል።
Filed in: Amharic