>

ምርጫ ቦርድ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ አላከብርም አለ... ! አሻራ ሚዲያ 

ምርጫ ቦርድ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ አላከብርም አለ… !

አሻራ ሚዲያ 

 የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት እነ አቶ እስክንድር ነጋን በተመለከተ የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እጩ እንዳይሆኑ ሰጥቶት የነበረውን ውሳኔ በመሻር እንዲመዘገቡ ትዕዛዝ መስጠቱ የሚታወቅ ነው።
በውሳኔው መሰረት የባልደራ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በዕጩነት ለማስመዝገብ እና እንደ ፍርዱ እንዲፈፀም ለምርጫ ቦርድ በደብዳቤ የተጠየቀ ቢሆንም ምርጫ ቦርድ  ውሳኔ እንደማይፈፅም በደብዳቤ ምላሽ ሰጥቷል ።
ይህን ተከትሎ የባልደራስ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት አስቸኳይ  ስብሰባ ጠርቷል።
Filed in: Amharic