>

ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ቀውስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሰጡት መግለጫ  (ፍትህ)

ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ቀውስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የሰጡት መግለጫ 

ፍትህ

 «የፖለቲካ ቁስሎች ሐይል ባለው ጡንቻ ሊፈወሱ አይችሉም!»
በተለያዩ የኢትዮጵያ ግዛቶች እየተባባሰ ያለው ሁከት እና እየበረታ የመጣው የክልልና የዘር ክፍፍል በጣሙን አሳስቦኛል።በትግራይ ውስጥ የደረሰው መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ረገጣ፤ በስፋት የተዛመተው የወሲብ ጥቃት ተቀባይነት የሌላለውና ሊቆም የሚገባ ነው።ከእያንዳንዱ የህይወት መስክና የዘር ምንጭ ያሉ ቤተሰቦች በሰላምና በደህንነት በአገራቸው ሊኖሩ ግድ ይላል።የፖለቲካ ቁስሎች ሐይል ባለው ጡንቻ ሊፈወሱ አይችሉም።በትግራይ ክልል ውስጥ በጦርነት ያሉ ሁላ የተኩስ አቁም ስምምነትን በማወጁ ረገድ ሊጸኑ ይገባል።የኤርትራና የአማራ ሐይሎች መውጣት አለባቸው።በዚሁ ሳምንት ውስጥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኢትዮጵያ ከ1970ዎቹ በሗላ የመጀመሪያው የርሃብ አደጋ ይደርስባታል ሲል አስጠንቅቋል።ሁሉም አካላት፣ በተለይም የኢትዮጵያና የኤርትራ ሐይሎች መጠነሰፊ የርሃብ አደጋን ለመከላከል በአስቸኳይ ገደብ የለሽ የበጎ አድራጎት ተደራሽነትን እውን ሊያደርጉ ይገባል።
የኢትዮጵያ መንግስትንና ተቋማትን እርቅን፣የሰብዓዊ መብትን፣ብዝሃንነትን እንዲያከብሩ እንዲያስፋፉ ዩናይትድ እስቴስ ታሳስባለች።ይህንን ማድረጉ የአገሪቱን የግዛት ጥምረትና አንድነትን የሚያጸና፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ጥበቃን የሚያረጋግጥ ብሎም በአስቸኳይ የሚፈለግ እርዳታ እንዲደርስ የሚያደርግ ይሆናል።የኢትዮጵያ መንግስትና በሁሉም የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ያሉ ባለድርሻ አካላት ሁሉን አቀፍ የሆነ ውይይት ሊያደርጉ ይገባል።ተባብሮ ሲሰሩ ለኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ የሆነ ራእይን በማቀናጀት ለወደፊቱ ለአገሪቷ ፖለቲካዊ መሰረትን በመጣል ቀጣይ የሆነን የምጣኔ ሐብት እድገትንና መልካም እድልን ሊያጎለብቱ ይችላሉ።
ኢትዮጵያን ለመርዳት፣ ተግዳሮቶቿን ለማሳሰብ፣ በአገራቶቻችን መካከል ጠንካራና ቀጣይ ግንኙነትን ለመገንባት እና ከአፍሪካ ህብረት፣ከተባበሩት መንግስታትና ከሌሎችም አለም አቀፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ለመስራት ዩናይትድ እስቴት ጽኑ ናት።የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ የሆኑት ጄፍ ፌልትማን በቀጥናው ውስጥ ተያያዥነት ያላቸውን ግጭቶች ሰላማዊ እልባት ለመስጠት፤ ብሎም የኢትዮጵያን የህዳሴ ግድብ ውዝግብ ሁሉም አካላቶች የሚስማሙበት መፍትሔን ለማምጣት፤ የዩናይትድ እስቴትስን ኢዲስ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እየመሩ ነው። ልዩ መልእክተኛው ፌልትማን  ወደ ቀጣናው በሚቀጥለው ሳምንት በማቅናት ሒደቱን ያሳውቁኛል።የአሜሪካ ዲፕሎማሲ የኛን እሴት ያነጸባርቃል፦ አርሱም ነጻነትን መጠበቅ፣ሁለንተናዊ መብቶችን መደገፍ፣የህግ የበላይነትን ማክበር እና እያንዳንዱ ግለሰብን በክብር ማስተናገድ ነው።
Filed in: Amharic