>
5:13 pm - Saturday April 19, 2960

ታዋቂ የዩናይትድ ስቴትስ ሴናተር ኢትዮጵያ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ተቃወሙ...!!!  (DW)

ታዋቂ የዩናይትድ ስቴትስ ሴናተር ኢትዮጵያ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ተቃወሙ…!!! 

DW

*...  «ግጭቶችን ለማስወገድ እየሠራች ባለችበት ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት የእኛ ርዳታ ነው። እንዲህ ያለ ድርጊት ወደ ሰላማዊ መፍትኄ ለመጠጋት አይበጀንም»
 
ታዋቂው የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል እና የኦክላሆማ ግዛት ሴናተር ጂም ኢንሆፍ በፕሬዚደንት ጆ ባይደን የሚመራው የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ኢትዮጵያ ላይ የጣለውን ማእቀብ እንደሚቃወሙ ገለጡ።
የሴኔቱ የጦር አገልግሎት ኮሚቴ አባል የኾኑት ሴናተር ጂም፦«የባይደንን አስተዳደር ጠንካራ የቪዛ እገዳን እቃወማለሁ» ሲሉ ይፋዊ የትዊተር ገጻቸው ላይ ጽፈዋል። «ግጭቶችን ለማስወገድ እየሠራች ባለችበት ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት የእኛ ርዳታ ነው። እንዲህ ያለ ድርጊት ወደ ሰላማዊ መፍትኄ ለመጠጋት አይበጀንም» ሲሉም አክለዋል።
አንጋፋው አሜሪካዊ ሴናተር በረዥም ጊዜ ወታደራዊ አመራር ይታወቃሉ። በዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚንስቴር ውስጥም በረዥም ጊዜ አገልግሎታቸው ስማቸው ይነሳል። ከብሔራዊ መከላከያ ኢንዱስትሪ ማኅበር በቅርቡ የአይዘንአወር ሽልማት ስለመቀበላቸው የሕይወት ታሪካቸው የበይነ መረብ መረጃ ይጠቁማል።
ፎቶ ምንጭ (የሴናተር ጂም ኢንሆፍ ይፋዊ ድረገጽ)
Filed in: Amharic