>

ከኬንያ ክህደት በስተጀርባ....!!! ( መስቀሉ አየለ) 

ከኬንያ ክህደት በስተጀርባ….!!!

      ( መስቀሉ አየለ) 

… ኢትዮጵያና ኤርትራ ላይ በእያቅጣጫው የሚደረገው ከበባ “ጅቡቲ ልደርስ ነው ” እያለ ነው። ኤርትራ “ደረስኩበት” ባለችው መረጃ መሰረት ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ የሚደረገውን የአውሮፕላን በረራ ላልተወሰነ ግዜ ዘግታዋለች። የእኛውም ጠሚዶ በየቦታው መሮጡን አቁሞ በግቢው ውስጥ መወሰን ጀምሯል። በሌላ በኩል ደግሞ “ውስጡን ለቄስ “የሆነችው ኬንያም አገር ተብላ ባለፈው ሰሞን በተባበሩት መንግሥታት ማዕቀብ እንዲጣልብን ጣቷን በቀሰረችብን ማግስት ዛሬ ደግሞ ከግብጽ ጋር የመማገጧ ነገር እንዲሁ በምዕራባውያን የተገባላት አንድ ቃል ስላለ ነው።
… “ከእዚህ በኋላ ኢትዮጵያ እንደ አገር ስለማትቀጥል እኛ በሄድንበት መንገድ የምትሄጅ ከሆነ ከቡራኬው ትካፈያለሽ… አገሪቱ ስትፈርስ በውስጧ ያሉትን እንደ አፍሪካ ኅብረት፣ አውሮፓ ኅብረት፣ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ኦፍ አፍሪካ እንዲሁም በጀርመን መንግሥት ውጭ የተመሰረተው AFrican peace keeping force ወዘተን ከአዲስ አበባ ተነሥተው ወደ ናይሮቢ እንዲዛወሩ እናደርጋለን።” የሚል የቃል ተስፋ ስለተሰጣት ነው።
… የአፍሪካዋ ዋና ከተማ ለቅርጫ የመታጨትን ሴራ በጓሮ በር በኩል የሰማችው ሩዋንዳም እንዲሁ ሌላዋ ተቀናቃኝ በመሆን ከሽንጡም ይሁን ከሻኛው ቢደርሰኝ ብላ የጎንዮሽ መንገድ መጀመሯም ይሰማል። “የበሬው ቆ’ጥ ይወድቅልኛል” ብላ ስትከተል የኖረችውን ቀበሮ ተረት ልብ ይሏል። ለማንኛውም እንዲህም መታሰቡ ቄሮ፣ ህወሓትና እነ ድምጻችን ይሰማ በጋራና በተናጠል የተጫኑትን አጀንዳ ተሸክመው “ገና ብዙ ርቀት ይጓዛሉ” ከሚል ተስፋ ተነስተው ነው። ተስፋ ርቆ የተሰቀለ ዳቦ መሆኑን የሚያውቁ ብጹዓን ናቸው።
… ከአርባ ዓመት በፊት የንጉሡ ሥርዓት መውደቁንና አገሪቱ በጥቂት አስር አለቆች እጅ የመግባቷን ነገር እንዲሁም በመሃል የግራ ዘመም የተማሪዎች ንቅናቄ በጎንደርና በኤርትራ ደግሞ የኢዲዩና የሻቢያን እንስቃሴ ያዩት ምዕራባውያንና አረቦች “ግዜው አሁን ነው” በሚል በዚያድ ባሬ ሶማሊያ ጀርባ ታዝለው ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሄዱበት ኩነት የፈጠረው መዘዝ ካርታ ላይ ብቻ የቀረችውን ሶማሊያን ትቶ ማለፉን ዛሬ የሚያስታውሱት አይመስልም። ነገ ደግሞ ኬንያ እና ሱዳን
Filed in: Amharic