>

አማራውና የህውሃት ዛቻ...!!! (ትንግርቱ ተክሌ)

አማራውና የህውሃት ዛቻ…!!!

ትንግርቱ ተክሌ

በስራ ምክንያት ዘግየት ብልም አንዲት ሀሳብ ማታ እንቅልፍ ነስታኝ ነበር ያደርኩት!
የጌታቸው ረዳን ቃለ መጠየቅ ማታ እንዳጋጣሚ የመስማት እድል ነበረኝ!
ቃል በቃል፦  “ከአማራ ኤሊት ጋር የምናወራርደው ሂሳብ ይኖረናል” ይላል!
ልብ አድርግ፦ ህውሓት በለው የአለምአቀፉ ማህበረሰብ ሁሉ ሳይቀር በአንድ ላይ ቆሞ…” የኤርትራ ሰራዊት ትግራይን ወደ ድንጋይ ዘመን መለሷት፣ የኤርትራ ሰራዊት ከትግራይ ለቆ ይውጣ፣ በኤርትራ ሰራዊት እየተዘረፈን ነው፣ ሴቶቻችን እየተደፈሩብን ነው…” የሚል እውነትም ሀሰትም የሆነ ግን ደግሞ በጣም ብዙ ብዙ በደል ደረሰብን እየተባለ ሲነገር በየለቱ ስንሰማ ከርመናል!  ዛሬም ይህ ጩኸት እንደቀጠለ ነው ብቻ ሳይሆን በሀገራችን ላይ ያስከተለውንም መዘዝ አይተናል! ዛሬም የኤርትራ ሰራዊት ይውጣልን የሚለው ጩኸት እንደቀጠለ ቢሆንም የአሸባሪው ትህነግ ዛቻ ግን ዛሬም አማራው ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ስትሰማ መቼስ መረገምህ አይቀርም!
ህውሓት ከ60 ምናምን ዐመት በኋላ ዛሬም “ጠላታችን አማራ ነው የምናወራርደውም ሂሳብ ይኖረናል” ብሎ በቃል አቀባዩ በጌታቸው ረዳ በኩል ያለአንዳች ሀፍረት በአደባባይ እቅጩን ነግሮናል! አስገርሞኛልም፣ አሳዝኖኛልም!
ስለዚህ አማራው እንደ ህዝብ ምን ማድረግ ይኖርበታል?
1. ህውሃት ካንተ ጋር የማወራርደው ሂሳብ አለኝ ብሎሃልና በዛ ልክ አንተም ህውሃት ማን እንደሆነ ተረድተህ ራስህን ለሚመጣው ነገር ሁሉ ዝግጁ አድርግ፣
2. ህውሃት እንድታንሰራራ የሚደረግን ማንኛውንም ግፊት በአንተ ላይ የተቃጣ የሞት አዋጅ አድርገህ ቆጥረህ የራስህን የመኖር ህልውናና ለማረጋገጥ በሚያስችል ቁመና ላይ መገኘት ይኖርብሃል፣
3. የኢትዮጵያ መንግስት ለያዘው አቋም ያለአንዳች ማቅማማት ሙሉ ድጋፍህን ስጥ፣
4. ለወንድም የትግራይ ህዝብ ዛሬም ህውሃት በሀሰት የሚያቀርብብህን  የሀሰት ውንጀላና እና የጥላቻ ቅስቀሳ እንዲያውቀው ከማድረግም ባሻገር ከትግራይ ህዝብ ጋር ያለህን ግንኙነት ለማጠናከር ጥረት አድርግ፣ ከትግራይ ህዝብ ጋር የሚደረግ ማንኛውም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የህውሓትን ለአማራ ህዝብ የህልውና አደጋ መሆኑን ከግንዛቤ ውስጥ ባስገባና ለዛም እውቅና በሚሰጥ መልኩ መደረግ ይኖርበታል፣
5. ህውሃት አማራን በጠላትነት መፈረጁን ቢያቆምም ባያቆምም፣ በኢትዮጵያ ሀገረመንግስት ውስጥ ዳግም መንግስት የመሆን እድል ማግኘት አይደለም ዳግም መንግስትነትን ማሰብ እንዳይችል ማድረግ ብቸኛው አማራጭህ ሆኖ ቀርቧል! ከዚህ አንጻር ህውሃት ሽበርተኛ ብቻ ሳይሆን ለአማራ ህዝብ ዘላለማዊ የህልውና አደጋ መሆኑን በትክክል ተገንዝበህ በዛ ልክ ራስህን አዘጋጅ!
በመጨረሻም በኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ላይ በምዕራባውያን የሚደርሰውን ማንኛውም ጫና ከመንግሥት እና ከሀገርህ ጎን በክብር ቆመህ እንድትመክት በአክብሮት እጠይቃለሁ!
Filed in: Amharic