>

በዚህ ወቅት ከኦሮሞ ብል[ጽ]ግና የከፋ የኢትዮጵያ የኅልውና አደጋ የለም! (አቻምየለህ ታምሩ)

በዚህ ወቅት ከኦሮሞ ብል[ጽ]ግና የከፋ የኢትዮጵያ የኅልውና አደጋ የለም!

አቻምየለህ ታምሩ

በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ ኅልውና ላይ የተደቀነው ትልቁ አደጋ በበላየ ሰብአ ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሙማ አፓርታይድ አገዛዝ እንጂ ማናቸውም የውጭ ወረራ ኃይል አይደለም። “ድምፃችን ለነፃንታች” የሚል ሰልፍ ለማድረግ የተዘጋጁ ሰዎች ዋናውን የኢትዮጵያ የኅልውና አደጋ ወይም ፈረንጆቹ “The Elephant in the Room” የሚሉትን ማየት የተሳናቸው የተሸጡ ፍጡራን ናቸው። ኬንያን ያህል ታማኝ የኢትዮጵያ የምንጊዜውም ወዳጅ እንኳን በኢትዮጵያ ጀርባ ከኢትዮጵያ የምንጊዜም ጠላት ጋር የጦር ስምምነት ለመፈረም የተገደደችው ሰማዩንም ምድሩንም የኔ ነው የሚለው ኦሮሙማ በኢትዮጵያ ውስጥ የለመደውን ኬንያም ተሻግሮ ለማድረግ በመነሳቱና የኬንያ ክፍል የሆነውን ሞያሌን በስመ ኦሮሞ ወደ ኦሮምያቸው ለመጠቅለል በመንቀሳቀሱ ኬንያም  ይህንን ድንበር ተሻጋሪ የኦሮሙማ ወረራ የውሕዷ ኬንያ የኅልውና አደጋ  አድርጋ በማየቷ ነው።
በመሆኑም ዛሬ ላይ ዋናው የኢትዮጵያ የኅልውና አደጋ ወይም “The Elephant in the Room” በጥንካሬዋ ስትመክተው የኖረችው የውጭ ጠላት ሳይሆን ከውጭም ከውስጥም ያጋጠሟትን ጠላቶቿን እንዳትመከት የኖረውን ጥንካሬዋን በኦሮሙማ እየሰበረ ያለው በመንግሥትነት የተሰየመው የኦሮሞ ብል[ጽ]ግና ነው።
በመንግሥትነት የተሰየመው የኦሮሞ ብል[ጽ]ግና ለኢትዮጵያ ያለው ጥላቻ ከየውጭ ጠላቶቻችን ሁሉ ይከፋል። ሱዳን ታላቁ የዓባይ ግድብ የሚገነባበትን የጎጃም ክፍል የነበረውን መተከልን ጨምሮ ወያኔ ግማሹን ጎጃምን ወስዶ የፈጠረውን “ቤንሻንጉል ጉሙዝ” የሚባለውን ክልል ባጠቃላይ ይገባኛል ማለቷ ተሰምቷል። የኦሮሞ ብል[ጽ]ግና መተከል ወደ ጥንት ይዞታው ወደ ጎጃም ተመልሶ የኢትዮጵያ ክፍል ከሚሆን ሱዳን ግድቡ የሚገኝበትን መተከልንና ክልሉን ባጠቃላይ ብትወስደው ይመርጣል።
ዛሬ የዐቢይ አሕመድ አማካሪዎች በሆኑት በሌንጮ ለታና ገላሳ ዲልቦ ይመራ የነበረው ኦነግ ከ1983 ዓ.ም. በፊት ሱዳን ውስጥ ዋና ጽሕፈት ቤታቸውን አቁመው ኦሮምያ ሪፑብሊክን ለመመስረት ሲታገሉ ሱዳን ለምታደርግላቸው ውለታ እንከፍላለን ብለው ቃል የገቡት ሱዳን በኢትዮጵያ ላይ ያላትን የመሬት ጥያቄ እናውቅልሻለን የሚል ብቻ ሳይሆን ናይሎቲክ ያሏቸው ጉሙዞችና በርታዎች ወደ ሱዳን እንዲጠቃለሉ በሚደረገው የሱዳን ጥረት ዋና ተዋናይ ለመሆን ነበር። ሱዳን ዛሬ ላይ እንዲህ በይፋ አካባቢውን ይገባኛል ከማለቷ በፊት አካባቢው የሱዳን እንደሆነ በመጽሐፍ ጽፈው ያሳተሙት ዛሬ ላይ የዐቢይ አሕመድ አምባሳደሮችና አማካሪዎች የሆኑት የኦነግ ዶክተሮችና ፕሮፈሰሮች ናቸው።
ሱዳን በጎንደር በኩል ወደ ውስጥ ከ50 ኪሎ ሜትር ገብታ የኢትዮጵያን መሬት እንድትይዝ ያደረገውም ዐቢይ አሕመድ ራሱ መሆኑን የሱዳኑ ኢታማጆች በአደባባይ የተናገረውን ልብ ይሏል። ይህ የዐቢይ እርምጃ የመንፈስ አባቶቹና አማካሪዎቹ የሆኑት እነ ሌንጮ ለታና ገላሳ ዲልቦ ለሱዳን በገቡት ቃል ማዕቀፍ የተፈጸመ ይሁን አይሁን ወደፊት የሚታይ ይሆናል።
በመንግሥትነት የተሰየመው የኦሮሙማ የአፓርታይድ አገዛዝ በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ ኅልውና ላይ የተደቀነው ትልቁ አደጋ ስለመሆኑ ከዚህ በፊት የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች አገር በቀል ወኪል ለነበሩት ሰዎች  ያደረገውን ማየቱ ብቻ ይበቃል። በበላየ ሰብእ ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሙማ አፓርታይድ አገዛዝ ለዘመናት የውጭ ወረራ ኃይል ወኪሎች የነበሩ ባንዳዎች የኩራት ምልክቶች ሆነዋል። ከነዚህ አንዱ በግብጽ ርዳታና በሶማሊያ ድጋፍ እየታገዘ ባሌን፣ ሐረርጌን፣ አርሲንና ከፊል ሲዳሞን ከሶማሊያ ጋር ለመቀላቀል በኢትዮጵያ ላይ የዘመተው የምዕራብ ሶማሊያው ጀኔራል ዋቆ ጉቱ ተጠቃሽ ነው።የግብጽና የሶማሊያ ወራሪ አገዛዞች ወኪል የነበረው ዋቆ ጉቱ በስሙ ፋውንዴሽና ትምህርት ቤት የተቋቋመለት በዐቢይ አሕመድ ትዕዛዝ ነው። በተቃራኒው ደግሞ ፋሽስት ጣሊያን ያረደው የታላቁ አርበኛ የደጃዝማች አበራ ካሣ ልጅ አርበኛው ደጃዝማች አምዴ አበራ ካሳ በአርበኛነት ለተዋደቁበት ውለታ ለስማቸው መጠሪያ ይሆን ዘንድ የተሰራ ቅርስ የፈረሰው  በዐቢይ አሕመድ ትዕዛዝ በኦሮሞ ብል[ጽ]ግና ነው።
የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ወኪል የነበረው ዋቆ ጉቱ ጀግና፤ የታላቁ አርበኛ የደጃዝማች አበራ ካሣ ልጅ አርበኛው ደጃዝማች አምዴ አበራ ካሳ ደግሞ ባንዳ ናቸው እስካልተባለ ድረስ የኢትዮጵያ አርበኞችን አሻራ እያወደመ በባድማቸው ላይ  የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ወኪል የነበሩ ዋቆጉቱዎችን ከፍ ከፍ ከሚያደርገው የኦሮሙማ አገዛዝ በላይ በኢትዮጵያ ኅልውና ላይ የተደቀነው ሊኖር አይችልም። ሲጀመር የግብጽና የሶማሊያ ወኪል ለነበረው ዋቆ ጉቱ በስሙ ትምህርት ቤትና ፋውንዴሽን የሰየመ አገዛዝ በምን ሞራሉ ነው ስለ ኢትዮጵያ ነጻነትና የውጭ ጣልቃ ገብነትን በመቃወም ሊያወራ የሚችለው? የውጭ ጣልቃ ገብነትን መቃወም በነ ዋቆ ጉቱ በኩል እነ ሶማሌያና ግብጽ ያደረጉትን ግልጽ ወረራ አይጨምርምን?
በመሆኑም ኢትዮጵያ በጥንካሬዋ ስትከላከላቸው የኖረቻቸውን የውጭ ጠላቶች እንዳትከላከል አድርጎ የውስጥ ጥንካሬዋን በኦሮሙማ ከሰበረው የኦሮሞ ብል[ጽ]ግናና ከኦሮሞማው ዋና ስራ አስፈጻሚው  ከዐቢይ አሕመድ በላይ በዚህ ወቅት በኢትዮጵያ ላይ የተደቀነ የኅልውና አደጋ የለም”
ዋና ከተማችንን አዲስ አበባን ጨምሮ ኦሮምያ በሚባለው ክልልና በዙሪያው የሚገኙ የኢትዮጵያ ክፍሎች በኦሮሙማ ዘንዶ  በብርሀን ፍጥነት እየተሰለቀጡ ናቸው። ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ወደ ዋና ከተማችን ወደ አዲስ አበባ መግባት ድንበር አቋርጦ ወደ ጎረቤት አገር ከመሄድ እንዲከብድና ኦሮምያ የሚባለው ክልል ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያውያን በቋንቋ እየተለዩ የሚታረዱበት ቤርሙዳ  ያደረገው ዐቢይ አሕመድ፤ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ኦሮምያ ወደሚባለው ቤርሙዳ የሚገባ ሰውም ሆነ መኪና የማይመለስባትን ምድር የፈጠረው የኦሮሙማ አገዛዝ ስለየትኛው ያስጠበቀው የሕዝብ ነጻነት  ነው “ድምፃችን ለነፃንታች” በማለት ሕዝብ እንዲሰለፍለት የሚጠይቀው?
ባጭሩ የዚህ ወቅት የኢትዮጵያ የኅልውና አደጋ የሚያጋጥሟትን በጥንካሬዋ ስተከላከላቸው የኖሩትን የጥንት ጠላቶቿን በጥንካሬዋ እንዳትቋቋማቸው የጥንካሬን የጀርባ አጥንት  በኦሮሙማ እየሰበረ የሚገኘው የኦሮሞ ብል[ጽ]ግና  ነው። ሕዝብ ድምጹን ለነጻነቱ ማሰማት ካለበት በዚህ የኢትዮጵያ የኅልውና አደጋ ላይ መሆን ይኖርበታል!
Filed in: Amharic