>

ከምር ግን … ምን ማለት ነው...?  (ዘመድኩን በቀለ)

ከምር ግን … ምን ማለት ነው…? 

ዘመድኩን በቀለ
አማሪካ ከኢትዮጵያ ላይ እጅሽን አንሺ ብለህ ስትፈክር ትውልና ወዲያው ሩሲያ ቻይናና ቱርክ ግን እጃችሁን በኢትዮጵያ ላይ ጫኑ ማለት ምን ማለት ነው? ፉከራው ኪላሽ አያደርግም ወይ? 
• አማሪካ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አትግቢ ብሎ ፈክሮ ሲያበቃ ሩሲያ… ህንድ… ቻይና እና ቱርክ ግን እንዳሻችሁ ሁኑብን ማለትስ እርስ በርሱ ኪላሽ በኪላሽ አያደርግም ወይ? አማሪካስ ዝም ብላ የምታይ ይመስልሻል ወይ? እስተዛሬ የበላሻትን ክፈዪ ብትልስ መልሱ ምንድነው የሚሆነው? ኧረ ብልጼ ትንሿ ደርግዬ ኧረ አረጋጊው የእኔ እናት። ነውር እኮ ነው እሙ።
• ኤርትራን አዲግራት፣ ዓደዋ እና መቀሌ ድረስ አስገብቶ… ሱዳንን የጎንደር ከተማ ከተም በሪው ድረስ አስወርሮ ሲያበቃ ” ሉዓላዊነታችንን አናስደፍርም” ብሎ መፈክር ይዞ በሸገር ጎዳና ሲቀደዱ መዋልስ እርስ በእርሱ ኪላሽ በኪላሽ አይሆንብንም ወይ?
• በፖለቲካ አመለካከታቸው ምክንያት የታሰሩ ዜጎችን ፍቱ…በአርቴፊሻል ረሃብ ምክንያት አደጋ ለተደቀነበት የትግራይ ህዝብ የእርዳታ እህል የሚደርስበትን መንገድ ፈልጉ። አመቻቹም። ከሁሉም የፖለቲካ ሃይሎች ጋር ብሔራው ውይይት እና እርቀ ሰላም አውርዱ። ወዘተ ወዘተረፈ ለሚለው የአማሪካ ጥያቄ፦
• የህዳሴ ግድባችንን ከመሙላት የሚያግደን አንዳችም ኃይል የለም !!
• መሪዎቻችንን ራሳችን በራሳችን እንመርጣለን  !! የሚል መፈክር ይዞ አደባባይ መውጣት ምን የሚሉት ቦለጢቃ ነው?
… የሚገርመው በሰልፉ ላይ አማሪካ ስለከሰሰችው የዐማራ ልዩ ኃይል ብልፅግኔ… ብልጽግኑ… ብልጽግኒሻ አንዳች ነገር አልተነፈሰችም። ከህወሓት ጋርም ተደራደሩ የሚለውንም ቃል ባላየ ባልሰማ ነው የተሸበለለችው። አይ ብልጼ… እንኳን በሦስተኛ ዓመትሽ ለተቃውሞ ሰልፍ አበቃሽ። ያውም ተአማሪካ ጋር።
… ከምር እንነጋገር ካልን በኢትዮጵያ ጉዳይ አማሪካንን ከቱርኩ ኤርዶጋን ጋር ማነፃፀር የእብደት እብደት ነው። ወደድንም ጠላንም በብዙ ምክንያት አማሪካ የኢትዮጵያ ባለውለታ ናት። “የነቀዘ” ስንዴም ቢሆን ሰጥታ ሚልዮኖችን ከሞት የታደገች ሃገርም ናት። በዲቪ ቢሉ በትምህርት ዕድል መቶ ሺዎችን የረዳች የሚልዮን ቤተሰቦችን ጉረሮ የደፈነች ሃገር ናት። በጤናው… በትምህርት ዕድል ወዘተ… በሃገሪቱ በጀት ውስጥም ቢሆን ተሳትፎዋ የጎላ ነው። እናም ከአማሪካን ጋር በበሰለ ዲፕሎማሲ በእልህ አስጨራሽ ትግል በመወያየት ወደ ሰላም መምጣት እንጂ በጩጬው መሪ በአቡቹ ብልጥ አራዳ የመንደር ጎረምሳ ስታይል በአጉል ጀብደኝነት ከአማሪካ ጋር ሰፋጣ አያዋጣም።
• ወደ አማሪካ ለሽያጭ የሚሄደው ምርት ከቆመ፣ ወይም እጥፍ ታክስ ይጨመርበት ከተባለ።
• የኡትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አማሪካ ምድር ድርሽ እንዳይል ከተባለ።
• ለመድኃኒት… ለሴፍቲኔት የሚሰጠው ዕርዳታ ከቆመ፣
• አማሪካ ለኢትዮጵያ መንግሥት የምትሰጠውን የበጀት ድጎማ ካቆመች። አደጋው ቀላል አይመስለኝም።
… ለጀግናው የሃገር መከላከያ ሠራዊት የሚከፈል ደሞዝ አይገኝም።
… ለመንግሥት ሠራተኛውም የሚከፈል ደሞዝ አይገኝም።
… ዛሬ ሰልፍ ወጥቶ አማሪካንን ሲራገም የዋለው ምስኪን የቀበሌ ሠራተኛም ቢሆን ለብሶ የሚወጣው ቲሸርት እና አበል እንኳ ነገ አያገኝም።
• ድግስ አይኖርም። የብልፄ ድግስ ማለቴ ነው።
… እናም ወዳጆቻችን ብልጥግናዎች ተረጋጉ። እስከዛሬ ሲሰድቡት የከረሙትን የዓድዋ ድል ሲያጣጥሉ የከረሙ የብልጼ ሰዎች ዛሬ ላይ የደሃውን ስነ ልቦና ወደ አጉል ጀብዱ በመቀስቀስ እሪቡራከረዩ ማለት ፌር አይደለም። አጉል የማያዋጣ እልህም ውስጥ አትግቡ። አቁሙ። እረፉ። ይልቅ የአዋቂ ምክር ስሙ። እንደ መንደር ጎረምሳ በባዶ ሜዳ ዊኒጥ ዊኒጥ አትበሉ። ጣታችሁን አማሪካ ላይ… ወደ ውጪ ከመቀሰራችሁ በፊት በመጀመሪያ የውስጥ ጉዳያችሁን ፈትሹ። ድሮም እናንተና ቤተሰቦቻችሁ የማትበሉትን ስንዴ ” የነቀዘ ነው” ምናም እያላችሁ በደሃው ጉሮሮ ላይ 12 ቁጥር ሚስማር አትሰንቅሩ። አትቀርቅሩ።
… ይሄንና ይሄን የመሰለ ቀና ምክር የምንመክረውን ሰዎች ደግሞ” ባንዳ… ፈሪ… ሃገር ሻጭ ምናምን እያላችሁ አታቀሳስሩን። ሼም ይዞኝ እኔም ከእናንተ ጋር ኤርዶጋንን ደግፌ አብሬአችሁ እንድሰለፍም አትጠብቁ። ከቱርክ ሰይፍ ይልቅ የአማሪካ የነቀዘ ስንዴ በስንት ጣዕሙ እንደሚሻለን መቼም አልነግራችሁም። እናም ፈዳላዎች እረፉ። ተረጋጉ። ከአማሪካ ጋር እሰጥ አገባውን አቁሙና በትዕግስት ይህን የመከራ ጊዜ በድርድር… በንግግር… ራሳችሁን በማስተካከል እለፉ። መጀመሪያ በሃገር ውስጥ የሚታረደውን የሰው እርድ አቁሙ። አስቁሙ።
… በአሁኑ ሰዓት አማሪካ ገንዘብሽንም… እርዳታሽንም ይዘሽ ገደል ግቢ የሚባልበት ጊዜ አለመሆኑንም እወቁ። የእነ መስፍን ፈይሳን፣ የእነ ናትናኤል መኮንንን እና የእነ ስዩም ተሾመን ትን የሚል ትንታኔ እየሰማችሁ አትዘባነኑ። ተናግረናል ከአማሪካ ጋር በመነጋገር፣ በመወያየት፣ በማስረዳት፣ በመረዳት ችግሩን ፍቱ። አይ ብላችሁ ሄጵ የምትሉ ከሆነ ግን ያው መንገዱን ጨርቅ ያድርግልን።
… የህዳሴው ግድብ እስከ አሁን አልቆመም። አይቆምምም። የህዳሴው ግድብ ከዚህ በኋላ አንዳች ቢደርስበት ከምደረ ገጽ የሚጠፉት ግብጽና ሱዳን ናቸው። እናም በእሱም አታስፈራሩ። ይልቅ የተጠየቃችሁትን ብቻ መልሱ እንጂ ያልተጠየቃችሁትን እያወራችሁ ስትበጠረቁ አትዋሉ።
… የዐማራ ልዩ ኃይልን ሕግ ለማስከበር ነው የላክነው እንጂ ርስት ለማስመለስ አይደለም የላክነው ያለው እኮ ቀድሞ የብልጽግና ፓርቲ ነው። ለአማሪካ የዐማራን መምቻ ዱላ ካቀበሉ በኋላ መልሶ የዐማራ ወዳጅ መምሰል ይሄ ምኝህን ፈልግ ሰገጤያዊ የቦለጢቃ ፍልስፍና ነው። በዐማራ ሰበብ ዐማራን ሆድ አስብሶ ማስፎከር አይጠቅምም። እንዲያውም አቢቹ ብቻውን ስለማይችለው “ይኸው እነርሱ ናቸው አልወጣ ያሉኝ” በማለት ከትግራይ ቀጥሎ ዐማራን በኃያላኑ ሃገራት ሊያስወቅጥ ያሴረ ነው የሚመስለኝ። ለፋሲል ከነማ መንግሥት ያሳየው ደግነትም ከመሬት ድንገት የበቀለ አይደለም። 25 ሚልዮኑም የተጠና ልገሳ ነው። እናም በዐማራ ስም ብልፄ መነገድሽን አቁሚ።
• ከወንድሜ ኤርሚያስ ለገሰ ገጽ የቃረምኳትን ላጋራችሁ :-
በገዥው ፓርቲ አስገዳጅነት የሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ የሚከተሉትን መፈክሮች እንደሚይዝ ይጠበቃል፣
1. “ደሃ አገር ሉአላዊነት የለውም!”
           ጠሚር ዓብይ አህመድ
                     ***
2. “ስንዴ ለማኝ አገር መብትና ነጻነት የለውም!”
            ጠሚር ዓብይ አህመድ
                   ***
3. “አለም ባንክ እና አይ.ኤም.ኤፍ የእናት መቀነት ናቸው!”
           ጠሚር ዓብይ አህመድ
                     ***
4.”ታሪክ የሌላቸውና በንዋይ ብዛት የሚያስቡ አገራት በገንዘባቸው አያዙንም!”
            ጠሚር ዓብይ አህመድ
                ***
5. “አሜሪካ ብትቀር የሚቀርብን የነቀዘው ስንዴያቸው ማራገፊያ መሆን ብቻ ነው!”
        ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ
                 ***
6. “አሜሪካ እጇን ከኢትዮጵያ ካላነሳች በቅርቡ ትጠፋለች!”
       ፕሮፍ አልማርያም ገ/ማርያም
                   ***
7. “የአሜሪካን የጉዞ እገዳ አገራዊ አንድነታችን እንዲፈጠር ያደርጋል!”
           ተወዳጁ ኢቲቪ
                  ***
8. “ራሺያና ቻይና የምንግዜም አጋራችን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!”
         አንዳርጋቸው ጽጌ
               ***
9. “አሜሪካን ሆይ! ከኢትዮጵያ ምርጫ ተሞክሮ ውሰጂ!”
               ፕሮፍ አልማርያም ገ/ማርያም
                       ***
10. “ብልፅግና ሆይ! ውታፍ ነቃይ የሚለውን ቃል ከመዝገበ ቃላት ይሰረዝልን!”
               ተደጋፊ ተደማሪዎች
                         ***
11. “ፈጣሪ ያሻግረናል!”
                ጠሚር ዓብይ አህመድ
                       ***
12. “ዓብይ አህመድ ያሻግራል!”
                 ፕሮፍ ብርሃኑ ነጋ
13. እናንተ ጨምሩበት!!
ኢትዮጵያ ያለ አቢይ አህመድ አሊም ታሸንፋለች !! ለዘላለምም ትኖራለች !!
Filed in: Amharic