>

የትግሬ ብሔርተኞች የማይሽር የአማራ ጥላቻ    (አቻምየለህ ታምሩ)

የትግሬ ብሔርተኞች የማይሽር የአማራ ጥላቻ   

አቻምየለህ ታምሩ

የኢትዮጵያን የቅርብ ጊዜ ፖለቲካና ታሪክ የሚያውቅ  ሰው ሁሉ እንደሚገነዘበው የትግሬ ብሔርተኛ ማለት የትግሬን ሕዝብ በሙሉ፣ የትግሬን ልሒቃን በጅምላ ወይም የትግሬ ተወላጅነት ያለውን ፖለቲከኛ ሁሉ የሚያጠቃልል እንዳልሆነ ያውቃል። እኔ የትግሬ ብሔርተኛ የምለው የትግሬን አድማስ ትግራይ ውስጥ ብቻ የወሰነን፣ በዚህ አድማስ የተለየ የትግሬ አገር ለመፍጠር የተቆረጠ ካርታ አንጠልጥሎ ሲዞር የሚውልን፣ ከኢትዮጵያ ታሪክ ጋር የተፋታንና  የሕወሓት ፕሮግራም አራማጅ የሆነን ፖለቲከኛ ሁሉ ነው። ይህ የብሔርተኛነት ብያኔ የነገድ ብሔርተኛ ነኝ የሚልን የማናቸውንም ነገድ ተወላጅ ብሔርተኛ ሁሉ የሚያጠቃልል ነው።
የትግሬ ብሔርተኞች ሁሉ የፖለቲካ አፋቸውን የፈቱት በማይሽር የአማራ ጥላቻ ስለሆነ፤ ፖለቲካ፣ ጦርነት፣ ቸነፈር፣ ወዘተረፈ በተነሳ ቁጥር በአእምሯቸው ጓዳ ተቀርጾ የሚታያቸው ጠላት ለአቅመ ፖለቲካ ሲደርሱ የተቀረጹበት የአማራ ሕዝብ ነው። ከዛሬ ሰላሳ ዓመታት በፊት የቀድሞውን የኢትዮጵያ ጦር በማፍረስ  ከበረሀ ያመጧቸውን  የገበሬ ወታደሮች  አቧድነው  በራሳቸው አምሳል ወንበር ጣባቂ እንዲሆን ባደራጁት ሠራዊት ላይ ባለፈው ኅዳር ወር “መብረቃዊ ጥቃት” ፈጽመው የአማራ ተወላጅነት ያላቸውን ታዛዦቻቸውን [አዛዦችን ላለማለት ነው]  ብቻ እየለዩ ካገቱ በኋላ በቀሰቀሱት ጦርነትና በጫሩት እሳት ሲለበለቡ [በመካከሉ በንጹሐን ትግሬዎች ላይ ስለሚደርሰው ጉዳት አይደለም እያወራሁ ያለሁት] የሚያጠቃቸው ጠላት የሚታያቸው አማራ ሆኖ ነው።
የሕወሓት ጆሴፍ ጎብልስ የሆነው ጌታቸው ረዳም ከሰሞኑ ከተደበቀበት የአይጥ ጉድጓድ ውስጥ አንገቱን አስወጥቶ ለበመቀል በዛተበት ንግግሩ ያደረገው ይኼን ነው። ጌታቸው ረዳ ባስተላለፈው የዘር ጥላቻ ቅስቀሳው ከአማራ [ልሒቃን ጋር] የሚያወራርደው ሒሳብ እንዳለው ዝቷል። ጌታቸውን ለዚህ ፍጅት ዛቻ ያበቃው መሬት ላይ ያለ ነበራዊ እውነት ሳይሆን በትግሬ ብሔርተኞች አእምሮ ውስጥ ሁሉ ተቀርጾ  ትምህርትና እድሜ ሳይሽረው የሚኖረው የአማራ ጥላቻቸው ነው።
የትግሬ ብሔርተኞች ሁሉ በጦርነት የሚፋለሟቸውም ይሁን በመድረክ የሚሟገታቸው ሰው ሁሉ የሚታያቸው አማራ ሆኖ ነው። እነሱ ራሳቸው በኦሮሞነት አደራጅነት በአማራ ጥላቻ ያሳደጓደቸው የኦሮሞ ብሔርተኞች ከአፍ እስከገደቡ በመንግሥትነት የተሰየሙበትን የኦሮሙማ የጭካኔ አገዛዝም የአማራ መንግሥት እንጂ የኦሮሞ መንግሥት ሆኖ አይታያቸውም።
ጌታቸው ረዳ ከአማራ [ልሒቃን ጋር] የሚያወራርደው ሒሳብ እንዳለው የዛተው በትግራይ የሚካሄደውን ጦርነት የሚመሩት አዝማቾች፣ የጦሩ ጠቅላይ አዛዥ፣ ኤታማጆሩ ሹሙ፣ ወዘተ. . የአማራ ተወላጅነት ያላቸው አለመሆኑ ጠፍቶት አይደለም። የትግራዩ ጦር አዝማቾች በነገድ አማራ ባይሆኑም ለጌታቸው ረዳና ለትግራይ ብሔርተኞች ግን የሚታዩዋቸው አማራ ሆነው ነው። ያለፉትን ሶስት ዓመታት ከሕወሓት የተማረውን ጭካኔ አበልጽጎ የኢትዮጵያን ምድር የንጹሐን መታረጃ ቄራ ያደረገው አውዳሚው የኦሮሙማ የአፓርታይድ አገዛዝ ለትግሬ ብሔርተኞች ግን የሚታያቸው እንደ ኦሮሞ ገዢ መደብ ወይም ሰማዩንም ምድሩንም ኦሮሞ ለማድረግ የኦሮሞ ብሔርተኞች በመንግሥትነት የተሰየሙበት አገዛዝ ሆኖ አይደለም። በትግራዩ ጦርነትም ያደረጉት ይህንን ነው።
ሕወሓት ራሱ ባደራጀው ሠራዊት ላይ “መብረቃዊ ጥቃት” ፈጽሞ ከቀሰቀሰው ጦርነት ራሱን ለመታደግ ጠቅላይ ሚንስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ተብዮው ወደ ትግራይ ያዘመተው ጦር መሪዎች እነማን እንደነበሩ ፓርላማ ተብዮውን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ በውጊያው መሪ ሆነው ተሰልፈዋል ያላቸውን  አዋጊዎች እየጠራ ከሰጣቸው የማሞካሻ ስም መገንዘብ ይቻላል። ዐቢይ አሕመድ በዚህ ሀያ የሚሆኑ አዋጊዎችን ስም እየጠራ ባሞካሸበት የፓርላማ ተብዮ ሪፖርቱ ውስጥ የአማራ ተወላጅነት ያለው አዋጊ የምናገኘው ከአማራና ከአገው ቤተሰቦች የተወለደው ሕወሓት ራሱ የፈጠረው ብአዴን “ታጋይ” የነበረው  አበባው ታደሰን ብቻ ነው።
ዐቢይ አሕመድ ፓርላማ ተብዮውን ባስቸኳይ ጠርቶ የትግራዩን ጦርነት ባግባቡ መርተው በድል በማጠናቀቃቸው የማቆላመጫ ስም እየሰጠ ያመሰገናቸው ሀያው ወታደራዊ  አዛዦች  የመዝገብ ስምና የነገድ ምንነት የሚከተለውን ይመስላል፤
1. “ድል ቁርሱ”  — “ጀኔራል” ብርሃኑ ጁላ [ኦሮሞ]
2. “ትንታጉ” — “ሌ/ጀኔራል” አበባዉ ታደሰ [አማራ + አገው]
3. “ነበልባሉ” — “ሌ/ጀኔራል” ባጫ ደበሌ [ኦሮሞ]
4.  “ሀገር ወዳዱ” — “ሌ/ጀኔራል” ዮሐንስ ገብረመስቀል [ትግሬ]
5. “ግስላዉ” — “ሌ/ጀኔራል” ጌታቸዉ ጉዲና [ኦሮሞ]
6. “አነፍናፊዉ” — “ሌ/ጀኔራል” አስራት ዲናሮ  አሕመድ[ኦሮሞ + ደቡብ]
7. “የጦርነት ሊቁ” — “ሜ/ጀኔራል” አለምሸት ደግፌ [ኦሮሞ]
8.  “ሰዉ ኃይል አመጋጋቢው” — “ሜ/ጀኔራል”  ሀጫሉ ሸለማ [ኦሮሞ]
9. “አይበገሬዉ” — “ሜ/ጀኔራል” ዘዉዱ በላይ [አገው]
10. “ሳተናዉ” — “ሜ/ጀኔራል” በላይ ሥዩም [አገው]
11. “ልበ ቆራጡ” — “ሜ/ጀኔራል”  መሰለ መሰረት [ደቡብ]
12. “ሎጂስቲክስ አሳላጩ” — “ሜ/ር ጀኔራል” አብዱራህማን እስማኤል [ኦሮሞ]
13. “ንስሩ” — “ሜ/ጀኔራል” ሹማ አብደታ  [ኦሮሞ]
14. “አርዕድ አንቀጥቅጡ” — “ሜ/ር ጀኔራል”  ይልማ መርዳሳ [ኦሮሞ]
15. “ነጎድጓዱ” — “ሜ/ጀኔራል” ሰለሞን ኢተፋ [ኦሮሞ]
16. “ንስሩ  — “ሜ/ጀኔራል” ብርሃኑ በቀለ [ኦሮሞ]
17. “ካርታን እንደ ምድር አንባቢዉ” — “ብ/ጀነራል” ተስፋዬ አያሌዉ [ኦሮሞ]
18.” ጀግናዉ” —  “ብ/ጀነራል” ሙሉዓለም አድማሱ [አገው]
19. “ጀግናዉ” —  “ብ/ጀነራል” ግርማ ከበበዉ [ኦሮሞ]
20. “ቆራጡ”  — “ብ/ጀነራል” ናስር አባዲጋ [ኦሮሞ]
እንግዲህ! ምንም እንኳን ሕወሓት የለኮሰውን የትግራይ ጦርነት በድል አጠናቀቁ ብሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስም እየጠራ ያሞካሻቸውየምድርና የሰማይ አዋጊዎች እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ቢሆኑም የትግሬ ብሔርተኞች ግን እንደገደላቸውና እንደጨፈጨፋቸው የሚቆጥሩት በጥላቻ ፖለቲካ አፋቸው ሲፈቱ በአእምራቸው ጓዳ የቀረጹትን አማራ ነው። ራሱ ያደራጀውና በኢታማጆር ሹምነት የመራውን ጦር የመታው ጻድቃን ገብረ ተንሳይም ሆነ ጌታቸው ረዳ በአማራ ላይ የበቀል ሰይፋቸውን እንደሚመዝዙ የዛቱት አዛዦቹና የነገድ ጀርባቸው ከላይ የቀረበው እንደሆነ ጠፍቷቸው አይደለም።
የሆነው ሆኖ ጻድቃን ገብረ ተንሳይም ሆነ ጌታቸው ረዳ ላለፉት 46 ዓመታት አማራን በጠላትነት በመፈረጅ  አማራን ማጥፋትን እንደ ርዕዮተ ዓለም  በሽፍትነትም ሆነ መንግሥትነት ዘመናቸው ሲያራምዱ መኖራቸው ጸጽቷቸው አለመቀየራቸውንና ዛሬም ከትግራዩ ጦርነት ጋር በተያያዘ ላም ባልዋለችበት ኩበት እየለቀሙ ለሌላ ዙር የአማራ ማጥፋት ፖለቲካ መዘጋጀታቸውን በየቴሌቭዥኑ እየወጡ በግልጽ መዛታቸውን ወድጄዋለሁ።
እነ ጌታቸው፣ ጻድቃንና የተቀሩት የትግሬ ብሔርተኞች ዛቻዎችና እየጎሰሟቸው ያሉት የእልቂት አዋጆች መከራ ያስተማራቸው መስሎት እጅና እግሩን አጣጥፎ ለተቀመጠው አማራ የማንቂያ ደወሎች ናቸው። አማራ ሆኖ መፈጠሩን ብቻ እንደጠላት ቆጥረው የትግሬ ብሔርተኞች እየጎሰሙ ያሉትን ሌላ ዙር የእልቂት ነጋሪት አማራ እየሰማ ከወዲሁ ተደራጅቶ የታቀደለትን አይቀሬ የበቀል ፍጅት ለመመከት የሚያስችለውን  ሁሉ  የመከላከል ዝግጅት የማይጀምር ከሆነ በአይቀሬው የነ ጻድቃንና የነ ጌታቸው ሌላ ዙር የበቀል ፍጅት በሚደርስበት ጥፋት ሁሉ የሚፈረድበት እንጂ የሚታዘንለት አይሆንም!
አማራ ባለፉት 46 ዓመታት የደረሰበትን ተነግሮ የማያልቅ መከራ ያስተናገደው የነ ጌታቸው ረዳንን፣ የነ ጻድቃን ገብረ ተንሳይንና ሌሎች የርዕዮተ ዓለም አጋሮቻቸው በአማራ ላይ ፍጅት ለመፈጽም የሚያራምዱትን ጸረ አማራ ፖለቲካና የሚሰብቁትን የበቀል ጦር  ከምር ወስዶ ራሱን ከእልቂት ለመታደግ የቤት ስራውን ባለመስራቱ ነው። ከዚህ ውድ ዋጋ ካስከፈለው ንዝሕላልነት ተምሮ አማራን ፈጽሞ ለማጥፋት ባቆበቆቡና ጠላት ባደረጉት ጠንቆች መሀል የወደፊት ሕዝብ ለመሆን ራሱን ካላዘጋጀ ኅልውናው ማክተሙ ሳይታለም የተፈታ ነው።
አማራ የተጋረጠበትን የኅልውና አደጋ ለመጋፈጥም የአማራ ግንባር ቀደም ባላደሞች፣ በልቶ ማደርን ብቻ የሕይዎት መመሪያቸው ያደረጉ የአማራ ርግማኖችና አማራ መቃብሩን ፈንቅሎ እንዳይወጣ መቃብር ጠባቂ እንዲሆኑ የተፈጠሩ ሆዳም አማሮች ነውረኛ ድርጅት የሆነውን ብአዴንና የብአዴንን መንፈስ ማስወገድ የተጋድሎው ጅማሬ መሆን አለበት። የዛሬዎቹ እነ ዐቢይ አሕመድ አማራን አጥፍታችሁ እደሩ ቢላቸው አጥፍተው ከማደር፤ የትናንቶቹ  እነ ጌታቸው ረዳ በለስ ቀንቷቸው ነገ ወደ አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ቢመለሱ ወልቃይትና ራያ የትግራይ እምብርት መሆናቸውን ከመመስከር የማይመለሱትን እነ አገኘሁ ተሻገርን፣ ብናልፍ አንዷለምንና ምን ነካው የማይባለው ብአዴንን ተሸክሞ አማራ የሚሻገረው ችግርና የሚያልፈው መከራ በፍፁም የለም!
Filed in: Amharic