>

ሦስቱ ሰኔዎች፤ ሦስቱ ጥቅምቶች፤  የአዋሳው 11/11 የምርጫ ሸፍጥ ምህንድስና ነው...!!! (ስርዓት ሥላሴ)

ሦስቱ ሰኔዎች፤ ሦስቱ ጥቅምቶች፤  የአዋሳው 11/11 የምርጫ ሸፍጥ ምህንድስና ነው…!!!

ስርዓት ሥላሴ

*… አብይ ባሌ ላይ “ከአገሪቱ እንብርት አባራናቸዋል፣ ከእኛ ፈቃድ ውጪ ትውር አይሉም” ሲሉ ማህበረ ተጋሩን፣ አርፋችሁ ተቀመጡ ቤተ -:መንግሥትን አትሰቡ ነበር። በሌላ በኩል “አብርኃ ደስታ አሸንፈኝ እንጂ አቅፌ ሥልጣኔን አስረክብኃለሁ”ም ብለዋል የባልደራስ ምሥረታ ያሳበዳቸው ዕለት…
ዕለተ ማክሰኞ ማዕዶተ ይግቡ
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በቢሆነኝ የተብራራ ብራ
በሰብለ ህይወት አዝመራ
ለራህብ የሚራራ።
“ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።”
(ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር  ፲፯)
#ዕፍታ ለትውስታ።
#ሦስት ሰኔወች፣ #ሦስት ጥቅምቶች፣ 11/11 ነገረ አዋሳ ለምርጫ ምህንድስና የተሰሩ የሞገድ መጽሐፍ፣ እና የ90 ደቂቃ በኢንተቤ ትወና የተከወነባቸው የገዳ ምርጫ ቦርድን ህጋዊ ዕውቅና ለማሰጠት የተሰናዱ ኦፕሬሽን ናቸው ብዬ በድምፅም በፁሑፍም በተደጋጋሚ ሠርቻለሁኝ።
ይህን ሊቀ ትጉኃን አቶ ሰለሞን ኃይሌ የማይወዛወዙ ዶፋን ችለው ከእኔ ብራና ጋር የዘለቁት ቅኑ የብራናዬ ታዳሚዬ ያውቁታል። ግን ሰሚ አልነበረም። እስከዚህ ድረስ በጥልቀት ሄዶ የምርጫ መሰናዶ ስለመደረጉ የተነተነ ተንታኝ አላውቅም።
#ሙሉ መሰናዶ እና ሂደቱ።
ምርጫን አስበው በሱማሌ ማፈናቀል የሠሩትም ለዴሞግራፊው ስኬት ስለምርጫው ስለመሆኑ ኦህዴድ ስልጣን ከመያዙ በፊት ስለመሆኑም በአፅህኖት ፅፌያለሁ።
ከዛም በኋላ “እንሞታታለን እንጂ ቤተ – መንግሥት አንለቅም” የጠቅላይ ሚር አብይ አልነበረም። በጨፌ ስብሰባ ለተነሳው ጥያቄ ዶር ለማ መገርሳ ሲመልሱ ቃሉን ተጠቅመውበታል። የቁም ሰማዕቱ ዶር አብርኃም ዓለሙ ተርጉመውት በርዮት ሚዲያም፣ ዘሃበሻ ላይም ለህትምት በቅቶ ስላነበቤኩ  ያም ለምርጫ መሰናዶው ጥጉ እስከምን እንደሆነ ፅፌበታለሁ፣ በድምፅም ሠርቸበታለሁ። ግን አልተስተዋለም።
ይህም ብቻ አይደለም እሳት ለብሰው ነፍሳቸውን ስተው እንደ አንድ ወጠጤ ጎረምሳ ጅማታቸው ተገታትሮ እሳት ጎርሰው እሳት ለብሰው ዶር አብይ አህመድ “ጦርነት ውስጥ  እንገባለን” ሲሉ ባልደራስን ይህም ከምርጫው ቅድመ መሰናዶ ጋር አልታዬም።
በነገራችን ላይ አዲስ አበባ በኦሮሚያ ሥር ከመስከረም 5/2011 ጀምሮ እንደምትዳደርም ፅፌያለሁ። የቀረው የሰነድ ርክክቡ ብቻ ነው።
አቶ እስክንድር ነጋ በያንዳንዱ ውሎው ሲታገት፣ ሲገፋ፣ ሲገለል ይህም ከምርጫ መሰናዶ ጋር አልተያያዘም። በዚህ ውስጥ ምርጫ አጀንዳ ሆኖ አልቀረበም። እሱ እስከ ቲሙ ከታሠረ በኋላ ያለውም የአደባባይ ሚስጢር ነው።
ተፎካካሪ/ ተቃዋሚ/ ተቀናቃኝ/ ቤተኛ/ በተገኜበት አብን በአቶ በለጠ ሞላ ባቀረበው መግለጫ መንግሥት የመሆን ህልሙ ብላሽ እንደ ሆነ ዶር አብይ ተናግረዋል።
አትሰቡት ለዛውም እናንተ ብለው በማባጨል፣ በማቃለል፣ በማጣለል፣ ተሟጋቹ ደጋግሞ እማዳምጠው ግን “ለአንድ ክልል ብለን ህገ መንግሥት አናሻሽልም” ባሉት ላይ ነው የሚተኮረው። እንጂ እናንተ ቤተ – መንግሥትን ታስባላችሁ ሲያምራችሁ ይቅር ብለው በስላቅ ተናግረውታል።
ባሌ ላይ “ከአገሪቱ እንብርት አባራናቸዋል፣ ከእኛ ፈቃድ ውጪ ትውር አይሉም” ሲሉ ማህበረ ተጋሩን፣ አርፋችሁ ተቀመጡ ቤተ -:መንግሥትን አትሰቡ ነበር። በሌላ በኩል “አብርኃ ደስታ አሸንፈኝ እንጂ አቅፌ ሥልጣኔን አስረክብኃለሁ”ም ብለዋል ስለ ባልደራስ ምሥረታ ያሳበዳቸው ዕለት።
ለዛውም ባልደራስ ሲቢክስ ድርጅት ነበር። መጋቢት አንድ የባልደራስ ስብሰባ ጥሪ እኮ በቤተመንግሥት ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ሰወች በአቶ ንጉሡ ጥላሁን ሰብሳቢነት አቶ ጃዋር እና ጋዜጠኛ ሲሳይ ገላጭ የሆኑበት ጉዳይ እኮ ባልደራስ አትኩሮት እንዳያገኝ ነው።
እስከዚህ ዕለት ድረስ የአዲስ አበባን ህዝብ አልሰበሰቡም። 9 ክልሎች በ100 ቀን ሲሰበስቡ ድሬ እና አዲስ አልተካተቱም። የገዳው ካፒቴን አቅደው ነው የሚከውኑት። የሚገርመው ለዬፕሮጀክታቸው የሚያደነዝዙ፣ አቅም የሚዘርፋ አፍዝ አደንዝዝ ጀሌወች አሏቸው። ወቅታቸው ሲጠናቀቅ ይሰናበቱ እና አዲስ ምልምሎች ይተካሉ።
#ጉዞው …
መደመር 50በ60 ዓመት የተሰናዳ ነው ሲሉ ባለ ሃብትን ሰብስበው ለሥንት ዘመን ዙፋኑን ቸክለው ለመዝለቅ እንዳሰቡ ቁልጭ ያለ ጭብጥ ነበር።
እኔ 50በ60 ያረጠ ብዬ ጽፌ ነበር። ለዛ የሚሆን ከጠበንጃ በስተቀር ክህሎት፣ ዊዝደም፣ ስልት፣ ተመክሮ፣ ዲስፕሊን፣ ሞራሊቲ እንደሌላቸው ስላጠናሁት ነበር ያን በአፅህኖት የፃፍኩት።
አለኝ የሚሉት ሊኖራቸው ቢችልም የኢትዮጵያን መሃያ እዬበሉ ለጃራ ነፍስ መዳን፣ ለኦነግ ድል ስምረት መረጃ ያቀበሉ ነፍስ ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ፣ ሰላም እና ፀጥታ ሊያስቡ?
ለመሆኑ ዬኢንጂነር ስመኜው ህልፈት የአንድ ተራ ዜጋ ነበርን? የሉዓላዊነት የመደፈር ጠረን አልነበረውምን?
#ሌላስ ……
የአማራ የበቃኝ አብዮት “ተራ ጩኽት” ብለው ሲያጣጥሉ በምን የብስጭት ልኬታ በንዴት፣ በቁጭት፣ በድንፋታ “ከምርጫ ውጪ ምንም የሚሆን ነገር የለም ፔሬድ” ሲሉ ድፍረቱ ሲነሪቲ ያላቸውን ሁሉ ረሽነው፣ ከጨዋታ ውጪ አድርገው፣ አግለው፣ አስረው፣ አግደው ተልዕኮው መጠናቀቁን ስላረጋገጡ ነበር እንደዛ የተናገሩት።
የአቶ ልደቱ አያሌው መከራ በራሱ እኮ ብዙ የዕውነት አመክንዮችን ያሳያል። መስታውት ነው። ራዲዮሎጂ።
ኮቢድ ስበብ ስለመሆኑ እኮ ትግራይ ምርጫ ባካሄደ በሳምንቱ ነበር እኮ ምርጫ እንዲካሄድ የተወሰነው።  ጦርነቱም ይፈለግ እንደነበር እራሳቸው በአማራ የበቃኝ ንቅናቄ ማግሥት የሰጡት ቃለ ምህዳን በቂ ነው። አይደለም ኮቢድ አንበጣ “መደመር” ናፈቀው ያሉ ሰው እኮናቸው።
ከአንድ ቀን በፊት ቅዱስ ሲኖዶስ አቋም ተብሎ ከተነገርን ውስጥ “ምርጫውን በፀጋ መቀበል” የሚል አለበት። ይህ ማለት ሞጋሳ ምርጫውን አጠናቋል ጥምቀቱ እንደ በረከት ቁጠሩት የሚል የከንቲባ ፅህፈት ቤት ልጥፍ ውሳኔ በተዋህዶ እጬጌ አንደበት እንድናዳምጥ ሆኗል።
የአጣዬ፣ የሽዋ ሮቢት ውድመት እኮ ከኦህዴድ የጫካ ወታደራዊ ክንፍ ጫና ለመዳን እኛን ምረጡን ነው። በዚህም ላይ ፅፌያለሁ። በዬከተሞች ያለው ቀውስ የሚደራጀው፣ የሚመራው በጠቅላይ ሚር ጽህፈት ቤት ነው። ይቀጥላልም። ቃጠሎውም፣ ፈንጅ ቀበራውም፣ ሰላምን ማወክንም።
የኢትዮጵያ ህዝብ ያላወቀው ምርጫን በሚመለከት ኦህዴድ ቤተ መንግሥት ከገባ ጀምሮ ለሰከንድ ሳይዘናጋ የተጋበት፣ እራሱን የቻለ በዶር አብይ አህመድ አማካኝነት የደህንነት፣ የኮማንድ ፖስት ቢሮ ያለው ነው። አቶ ታማኝ በዬነ አገር የሄደበት ቁምነገር ምርጫ እና ምርጫ ብቻ ነው። ሌላ ተልዕኮ የለውም።
በስውር የሚሠሩ ብዙ በጣም ብዙ ትብትብ ጉዳዮች አሉ። በቃን ይጠልፋታል። ያን ዘመን ተሻጋሪ የቅዱስ ሲኖዶስ መንፈስ ቅዱሳዊ ተልዕኮ ጠልፈው ክብሩን ዝቅ ለማድረግ እንደሄዱበት ሁሉ።
አሁን ሌላ ኦፕሬሽን፣ ይህን የሚያዘናጋ ወይ የሚደልዝ ሌላ ማት ደግሞ ይላካል። ሲኦል። የጊሊሶ የአማራ ጭፍጨፋ ዓለም አቅፍ ዕውቅና ሲቸረው በማግሥቱ የትግራይ እና የፌድራሉ ጦርነት ተከሰተ።
#እኔ የሚርበኝ የቤተ መንግሥቱ ለኦዳ ፅናት አይደለም። እእ!
ተጨቁኖም፣ ደህይቶም፣ ሰላሙን ባልነሱት ህዝባችን። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ፆታ አላቸው ብዬ አላምንም። ሃይማኖት አላቸው ብዬ አላምንም። የሚታመን፣ የሚያምኑት ጓደኛ አላቸው ብዬ አላምንም። አሳቻ ናቸውና።
 ቀለማቸውም፣ ጎዳናቸውም፣ ፍላጎታቸውም፣ ራዕያቸውም አሳቻ ነው። መተርጎም አይቻልም። ከባድ ሰው ናቸው። አናውቃቸውም።
የሚገርመኝ በፖለቲካ ሳይንስ ሊቅ የሆኑት ሳይቀሩ አሉታዊ ዴሞግራፊ በታወጀባት፣ ሥራ ላይ በዋለባት አገር ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማሰባቸው ነው። ዴሞክራሲ ቀርቶ #ዲክታተርነት ሲናፍቅ የሚቀር ነው የሚሆነው።
በድምፅ እኮ ነው 100/100 በተመረጠው ፓርላማቸው የተመረጡት። በህወሃት መራሹ ኢህአዴግ A አዲስ አበባ ላይ አብዛህኛው ድምፅ ከኦህዴድ እና ከግርባው ብአዴን ሙሉው ከደህዴን 8፣ አዋሳ ላይ ከአንድ ድምፅ በስተቀር ተመርጠዋል።  ህወሃትም መርጧቸው ነበር እኮ አይደል?
ተልዕኳቸው ግን በጦርነት ድል አድርገው ሥልጣን እንደያዙ ማሳወቅ ፈለጉ። ሞገድ ጋዜጣን ድርጊት ላይ አዋሉት። በራስ የመተማመን አቅማቸው ድውይ ስለሆነ ይፎካከሩኛል፣ ሲነሪቲ አለው የተባለውን ሁሉ አስወገዱ። ዶር አንባቸው መኮነን የተገደሉት እኮ በዚህ ነው።
#ቁርጥ ይታወቅ።
ከሳቸው በላይ የወጣ ተቀባይነት ያገኜ ነፍስ እሳቸው በህይወት እያሉ አይፈቀድለትም። ውጪም ይኑር አገር ውስጥ። ጎልቶ ሥም እንዲወጣ አይሹም።
እሳቸው ወደ ሥልጣን ከመጡ አይደለም ፖለቲከኛ አርቲስት ተፅዕኖ ፈጣሪ አልተፈጠረም። የተፈጠረውንም በሙሉ አራገፉት። የኔታ ጎዳና ያዕቆብ “እምናከብረው አሳጡን” ሲሉ ሰምቻለሁ። እኔ ሥጋቴ ሁሉንም ዘርፈው ከማተባችን ጋር እንዳያፋቱን ነው።
ኃይማኖቶች ሳይቀሩ ነው በከፋ ሁኔታ ተዳፍረው ከደረጃቸው ያወረዷቸው። ኢትዮጵያ እራሷን ይቀኑባታል። ቢችሉ #ኢትዮጵያ #ከካርታ ተሰርዛ #አብይ እንድትባል ይሻሉ። ይህን ደግሞ ጠብቁት።
መስቀል አደባባይን #አብይ #አደባባይ ያሰኙታል የፒኮኩ ልዑል። አብሯቸው ያለው የጨለማው ይመስለኛል። የቀደመ ሰውኛ ጠረናቸው ሁሉ ምናኔ ላይ ስላለ። የሳይንስ እና የቴክኖሎጂ ሚር እያሉ ሌላውን ሰውኛዊውን አብይ ዘርዝረውልን ነበርና።
ሳጠቃልለው ለእኔ የኬሎ መረጃ ብርቄ አይደለም። ሰበር ዜናዬም አይደለም።
አስቀድሜ የቀደሙትን የ2016 ሳይንስና ቴክኖሎጂ ላይ የተከታተልኳቸውን ዶር አብይ በሐምሌ 19/2010 ላይ በኢንጂነር ስመኜው ደመከልብነት ደወል ስለነቃሁኝ ……
 ከ2010 መጨረሻ  ጀምሮ ምልከታዬን በከበቡሽ ብሎጌ፣ በፀጋዬ ራዲዮ፣ በከበቡሽ ዩቱብ ቻናሌ፣ ፌስቡክ የጀመርኩት በቅርቡ ቢሆንም ስፅፍ ባጅቻለሁ።
ይብላኝላቸው አሁንም “ተረኛ” እያሉ ለሚያለዙት ሰብዕናወች። የሳቸው ሰባራ ሰንጣራን ሲጥፋ ውለው ለሚያድሩ ነፍሶች። የዚህ ሁሉ መከራ ግርዶሾች እነሱው ናቸው። አንድ ቀን 24 ሰዓት ለጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ብዙ ነው። 100 ቀኑን እኮ አይተናል። ፈጣን ናቸው። አቀናጅተው አደራጅታው ነው ሁሉን የሚሠሩት።
እኛ ደግሞ ወጥ ሃሳብ እንኳን የለንም። የህወሃት ቀሪ ክፍል አሁንም አማራን ይከሳል፣ ዕድል ካገኜም ከማውደም አይታቀብም፣ አብዛኞቹ የአማራ ሊቃናት እንደለመደባቸው የሌላ ጎጆ አደራጅ ናቸው።
ግርባው ብአዴን “ጭምት አዲስ አመራር” እያሉ ያሽሞነሞኑ ሁሉ ዛሬ ተያይዞ ምሾ ማውረድ ሆነ። እኔና ብዕሬ ደግሞ ሰከን ብለን በመረጋጋት መከታተል። የሚደንቀን ሰበር ዜና የለምና።
ውዶቹ መረጃ ሊንኮችን እለጥፋለሁ። ጊዜ ያላችሁ ፈትሿቸው። ዕለቱ በዚህው ዘለግ ባለው ፁሑፌ ርጋ እለዋለሁ። ኑሩልኝ ለእኔም ለቅኒትም ኢትዮጵያም። ማለፊያ ጊዜ። ቸር ወሬ ያሰማን። አሜን።
 • አንድ የፖለቲካ ሂደት ማዕቀፍ አለው።
 በማዕቀፉ ውስጥ አውራ እና ጅረት ጎዳናዎች ይኖራሉ።
በኦሮሙማ አውራ ጎዳናዎች ላይ ቁጥር አንድ አስኳሉ ኡለታዊ ዴሞግራፊ ነው። እኔ ዴሞግራፈን እራሴ ነኝ አሉታዊ እና አወንታዊ ብዬ የከፈልኩት። ምክንያቴ በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ወደ ሌላ ቦታ ሊወሰዱ የሚችሉ ዜጎችን አስመልክቶ የሚኖረው የዴሞግራፊ ዓይነት አፈጻጸሙ ህዝቡን አወያይቶ፤ አነጋግሮ አስወስኖ ከሆነ አወንታዊ ነፍስ አድን ነው ብዬ አስባለሁኝ።
ኦህዴድ የፈጸመው፤ በመፈጸም ላይ ያለው፤ ወደፊትም የሚፈጽወም በጎጃም፤ በወሎ፤ በጎንደር፤ በትግራይ በደቡብ፤ አፋር፤ ሊፈጽም ባሰበው ዴሞግራፊ ግን አሉታዊ ነው ብዬ ነው እማስበው። ወረራ፤ መስፋፋት እና አስሜሌሸን ለመፈጽም ታቅዶ ስለሆነ።
የሚገርመው ባለው ላይ መቀጠል ሳይሆን ነበሩን የሺህ ዘመናት እርሾ አድነድዶ፤ አውድሞ አዲስ መፍጠርም ሌላው የአፍራሹ ዴሞግራፊ የ ኦፕሬሽን አካል ነው። ሁሉንም ድሃ አድርጎ ከዜሮ መጀመር ነው ትልሙ። ሰሞኑን አዲስ የከተማ ፕላንም አቅዷል።
የሆነ ሆኖ የጨፌ ኦሮምያ መረጃ ከወጣ በኋላ በተከታታይ ሰርቸበታለሁኝ። ለዚህ ነው ሰብር መረጃወች ብርቄም፤ ድንቄም እማይሆኑት። ከዛ ስለምነሳ ምርጫ ቢባል፤ ሸጋ ንግግር ጠቅላዩ አደረጉ ቢባል፤ ፓርክ ቢደራጅ ለእኔ ምንም ነው።
ምክንያቱም አሉታዊ ዴሞግራፊ ፋሺዝም ነው እና። በፋሺዝም ውስጥ ብናኝ ሰውኛ፤ ተፈጥሮኛ የሆነ ጠረን አይገኝም። ፈጽሞ። ሌአለው ቀርቶ ሌቢስቶች የሎቨቢ ሥራቸውን ከዚህ ቢጀምሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ድጋፍ ባገኙ ነበር። ምክንያቱም ፋሺዝምን አለም የተጠዬፈው ፖለቲካ ስለሆነ። ግን ከሥር መነሳት ሲቻል ብቻ ነው።
እኔ ግን አቅሜን አላባክንም። እርግጥ ነው ያን የፋሺዝም ወራራን ለማስቆም የአቶ እስከንድር ነጋ ንቅናቄ በነበረበት ወቅት የተቻለኝን ያህል ደግፌያለሁ። እሱ እስር ቤት እስከ ቲሙ ከገባ በኋላ የሚሆነው ነገር ለለት ጉርስ ከሚሆን ባለፈ አገር በማዳን፤ ፋሺዝማዊውን ጉዞ ከመሳቆም ጋር አቅም ያለው የፖለቲካ ሂደት ስለማላይ በስክንት ነው እምጓዘው።
ነገር ግን ከምንም ያለ ይሻላል፤ ቤቱ ተዘግቶ ከሚጠብቅ ቢፈከፈት መልካም ነው ብዬ ስለማምን በተደሞ ብቻ ነው እምከታተለው። ለማንኛውም ቀድመው የተሠሩ ምልከታወች በድምጽ እና በጹሑፍ እንሆ።
 አደብ ያላችሁ ወገኖቼ ቢያንስ አሁን ቢዘገይም እባካችሁ ከ አሉታዊው ዴሞግራፊ ለመነሳት ሞክሩ። ስለ አማራ ጭፍጨፋ፤ መፈናቀል፤ ስለተዋህዶ መጎሳቆል፤ ስለ አማራ ወዳጆች መንገላለታት ምንጩ አሉታዊ ዴሞግራፊ ፖሊሲው ስለሆነ ነው ኦሮሙማ።
ችግር ከምንጩ ካልተነሳ መስታገሻ እንጂ መፍትሄ አይገኝም። ማሸነፊያ መንሹ ተስቶ ነው ተስፋ የሚወጠነው። ለዚህም ነው ተስፋ እዬራቀን የሄደው። ምርጫ በሚመለከት ናዚዝ በምርጫ እኮ ነው ሥጣን ያገኜው። አይደለም ወይ?
• ምርኩዝ።
የኦሮሙማ ጠቀራዊ የዲሞግራፊ ፋሽስታዊ ጉዞ ከአቶ ለማ መገርሳ አንደበት።
•Jun 3, 2020
ዴሞግራፊ የዴሞክራሲ ውድቀት እንጂ የዴሞክራሲ ተስፋ የልቅና ምህንድስና አይደለም።
•Jun 6, 2019
አሉታዊው የዴሞግራፊ ፍልስፍና የበቀል ፍልስፍና ነው።
•Jun 8, 2019
አሉታዊ ዴሞግራፊ የቂም ደም ነው።
•Jun 11, 2019
አሉታዊ የዴሞግራፊ ምህንድስና የበታችነት ስሜት ደዌ ነው። {የወግ ገበታ}
•Jun 13, 2019
የአሉታዊው የዴሞግራፊ ዕሳቤ ለአላዛሯ ኢትዮጵያ የታዘዘ የጢስ አይዎሎጂ ነው። {የወግ ገበታ 17.06.2019}
•Jun 17, 2019
2021 ኤፕሪል 16, ዓርብ
ኢትዮጵያውያን አብይ ሠራሸ አይደለንም።
2019 ዲሴምበር 29, እሑድ
የዴሞክራሲ ጽንሰት ውርጃ {ዘለግ ያለ ሙግት ከምርጫ ቦርድ ጋር}
2019 ዲሴምበር 16, ሰኞ
ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።
50በ60 ያረጠ ፖለቲካ።
በሰጨኝ ለጠቅላይ ሚ/ር ፈጽሞ አያምርም።
Ethiopia: ርዕዮት ዜና መጽሄት || አዲስ አበባ እና የኦዴፓ/ኦነግ ሸፍጥ || Reyot News Magazine – 3/9/2019
Mar 9, 2019
“ጠላን ከጥሩው ነገርን ከሥሩ” ይላሉ ባለቅኔወቹ ጎንደሮች።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
01/06/2021
ዕውነት ሰብል ስለሆንክ ተመስገን የእኔ ሉዑል!
Filed in: Amharic