>

"እሞታለሁ እንጅ ስልጣን አለቅቅም...!!!" መርስኤ ሀዘን ወልዴ

“እሞታለሁ እንጅ ስልጣን አለቅቅም…!!!”

መርስኤ ሀዘን ወልዴ

የአብይ አሽቃባጮች አፋሽ አከንፋሾች ምነው ዝም አላችሁ ?

የብልጽግና ስራ አስፈጻሚ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ጠቅላዩ እሞታለሁ እንጅ ስልጣን አለቅቅም: እያለ ነው ::
“እስከሚቀጥለው 10 ዓመት ድረስ ማንም ሰው መያዝ አይችልም፤ እሞታለሁ እንጅ ስልጣን አለቅም” ብሏል:: በዚህም አይቆምም ” ከወዲሁ እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ ምርጫውን አሸንፈናል፤ ምንም ጥርጣሬም ምስጢር የለውም፤ ምርጫውን አሸንፈናል፤ በቅላሉ ነው ያሸነፍነው…ይህና ሌላም አምባገነናዊ ንግግራቸው  በድብቅ ተቀድቷል የተባለ ድምፁን ሰምተናል:: ሊንኩን ተጭነው ያድምጡ 6:28 ደቂቃ በኇላ::
የሙክታሮቪች ማስተባበያ
ሾልኮ ወጣ ስለተባለው የጠቅላዩ ድምፅ
ድምፁን ሰማሁ። የሰማሁት በጥንቃቄ ነው። እየተሸረበ ካለው ሴራ እና በየትኛውም መልኩ የአብይን ማስወገድ አለብን ከሚባለው ከበሮ ድለቃ አንፃር ነው ይህን ወጣ የተባለውን ድምፅ የሰማሁት።
ድምፁ በአንድ መድረክ ላይ የተነገረ ስለ መሆኑ ምንም ማስረጃ የለም። ቆርጦ የተቀጠለ ሊሆን የመቻሉ እድል ከፍተኛ ነው።
“እሞታለሁ እንጂ ስልጣን አልሰጥም!”
የሚለው አገላለፅ ……. በጭብጨባ ተቋርጧል። እንዲህ ያለ አገላለፅ የብልፅግና አመራርን ያስደነግጣል እንጂ በፍፁም በጭብጨባ ድምቀት ለማጀብ አይቻልም፣ ምክንያቱም እኔ በሚል የተገለፀ ነው እንጂ “
ብልፅግና አይለቅም” የሚል አይደለም። አብይ እንዲህ ያለ ነገረን ለነሙስጠፌ ይናገራል ማለት ይከብደኛል።
ከላይ የተገለፀው
ንግግሩ በዚህ መልኩ አልቆ ሊሆንም ይችላል …..
“እሞታለሁ እንጂ ስልጣን አልሰጥም ….. የሚለው ህወሓትም በህዝብ ትግል ተወግዷል”
“እሞታለሁ እንጂ ስልጣን አልሰጥም …. ማለት አይጠቅምም …. ስልጣንን ህዝብን አስከፍተን እንዳንለቅ በርትቶ መስራት ነው እንጂ”
ሊሆን ይችላል።
ሌላም ሌላም አገላለፅ ይከተል ይሆናል። ስለዚህ ቆርጦ የተቀጠለ ነገር አለ ብሎ መጠርጠር ይገባል። አብይን በየትኛውም መልኩ ማስወገድ አለብን እያሉ ያሉ አካላት መሰሪ አካሄዳቸው እንዲህ ያለ ቆርጦ ቀጥል ድምፅ ማቀነባበር ቀላል ስራ ነው።
ድመፅ ሾልኮ ወጣ ለማስባል አንደኛው መንገድ፣ ድምፁ እጅግ ሊሰማ የሚከብድ፣ ግን በጣም በጥሞና ቢሰማ፣ ቢቻል በፅሁፍ እየታገዘ ቢሰማ ግልፅ ሊሆን በሚችል መልኩ እንዲሆን በማድረግ ለማሳመን መሞከር ነው።
ይህ ዝቅተኛ ድምፅ ደግሞ ቆርጦ ቀጥል ድምፅን ለመቀላቀል ይመቻል።
ለምሳሌ
“ከፍተኛ ደም መፋሰስ ሊኖር ይችላል” ማለት ደም መፋሰስን እኛ እንፈጥራለን ማለት አይደለም። ኢትዮጵያ እና ምርጫን በተመለከተ በርካታ ሰዎች ምርጫው ደም መፋሰስ ሊያስከትል እንደሚችል ይገምታሉ። ጠቅላዩ በየትኛው አውድ እንደተናገሩት ሙሉ ታሪኩ የለም። ቆርጦ የተቀጠለ ሊሆን ይችላል።
“ግብረሀይል” የተባለው ምርጫን ለመቀስቀስም ሆነ ሌላ ፖለቲካዊ ተልዕኮ ያለው ግብረሀይል ሊሆን ይችላል።
“ምርጫውን አሸንፈናል!” ማለትም በየትኛው አውድ፣ በየትኛው ሁኔታ እንደተነገረ የድምፅ ማስረጃው ደካማ ነው።
ለምሳሌ 
የህዳሴውን መጀመሪያ ሙሊት ልክ እንደሞላን ከፍተኛ መነቃቃት ተፈጥሮ ነበረ። ይህ ተከትሎ ጠቅላዩ “ምርጫውን አሸንፈናል” ሊሉ ይችላሉ። የህዝብን ቀልብ ስበናል ብለህ ስልጠና የምትሰጠውን የራስህ ፓርቲ ካድሬዎች ልታነቃቃ ትችላለህ።
“ምርጫውን አሸነፈናል!” ማለት ለህዝብ እና ለራስህ ካድሬ ስብሰባ ትርጉሙ ይለያያል።
እንዲህ እንዲህ እያልን ማፍታታት ይቻላል።
ስለዚህ ሾልኮ ወጣ በተባለው ድምፅ ሙሉ በሙሉ እውነት ነው በማለት ማመን ይከብዳል። በተለያዩ መድረኮች የተደረጉ ንግግሮችን ቀጣጥለው የሆነ ትረረክት መፍጠር የተፈለገ ይመስላል።
ይህን በመፃፌ በርካቶች በዚህ ሾልኮ ወጣ በተባለው ድምፅ ያመኑ ሰዎች ሊናደዱ ይችላሉ።
እኔ ታማኝነቴ ለራሴ ህሊና ነው። መንግስት አጥፍቶኣል ብዬ ካመንኩ “ሺፍታ መንግስት፣  ወሮበላ መንግስት” ለማለት ምንም አልፈራም።
እንዲህ ተቆራርጦ የመጣ ድምፅን ደግሞ እመን ቢሉኝ አላምንም።
መንግስት መወቀስ ባለበት መወቀስ አለበት። እንዲህ ቆራርጠው እየሰፉ ግን ህዝብን ማሸበር ተገቢ አይደለም።
በዚህ ምርጫው ላይ ጥላ ለማጥላት በሚፈለግበት ጊዜ “ሾልኮ ወጣ” በሚል የሚላክን እኩይ አላማ ላዘለ መልዕክት ሙሉ ሳይሆን ግማሽ ጆሮን መስጠት ነው። የተቆራረጠ ድምፅን እውነት ለማስመሰል የዘመኑ ቴክኖሎጂ አቅሎታል።
እኛ ደግሞ አጀንዳ ከሚቀርፁልን በላይ አዕምሮኣችንን መጠቀም አለብን።
Filed in: Amharic