>

ባልደራስ ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ እንዲታገድ ጠየቀ...!!! (ወንጭፍ) 

ባልደራስ ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ እንዲታገድ ጠየቀ…!!!

ወንጭፍ 


ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) በግፍ እስር ላይ የሚገኙ መሪዎቹ እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ ተጠርጣሪዎች እንጂ ፍርደኞች ባለመሆናቸው በመጭው ምርጫ በዕጩነት እንዲቀርቡ ጠይቆ በምርጫ ቦርድ ተከልክሏል። ሆኖም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት በመውሰድ ሲከራከር ከቆየ በኋላ የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የመመረጥና የመምረጥ መብታቸው እንዲከበር ወስኗል። ይሁን እንጂ ቦርዱ የፍርድ ቤትን ውሳኔ አልተቀበለም። በመሆኑም ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ሊደረግ የታቀደው ምርጫ ታግዶ እንዲቆይ ባልደራስ የአፈፃፀም እግድ እንዲያወጣ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳዩን እንደሚያስረዱ ይጠበቃል።

Filed in: Amharic