ለሰላሣ ቀናት በእስር ላይ የቆዩት አቶ ታዲዮስ ታንቱ ዛሬ በአራት ሺህ ብር ዋስትና ተለቀቁ…!!!
ዶይቼ ቬለ
አቶ ታዲዮስ «በህቡዕ በመደራጀት ከውጪ ካሉ አካላት ጋር በመሆን ስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ እንዳይከናወን እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ» በሚል ወንጀል ተጠርጥረው ነበር ሚያዝያ 27 ቀን 2013 ዓም በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት።
በተጨማሪም ሕዝቦችን ለብጥብጥና ሁከት እንዲነሳሱ እና እንዲንቀሳቀሱ አድርገዋል በሚልም ተጠርጥረው ፖሊስ ምርመራ ሲያደርግባቸው ቆይቶ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋስ ለቋቸዋል ሲሉ ጠበቃቸው አቶ እንደገና ግዛው ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። ጠበቃቸው እንዳሉት ፖሊስ ምርመራውን አልጨረስኩም በእስር ቆይተው ምርመራውን ላጠናቅ የmkል መከራከሪያ አቅርቦ ነበር።ሆኖም የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ጠበቃቸው ግለሰቡ በእስር የሚያቆያቸው ምንም ምክንያት የለም በሚል ያቀረቡትን መከራከሪያ ተቀብሎ ይህንን ብይኑን ማሳለፉን ለዶቼቬለ ተናግረዋል።አቶ ታዲዮስ ታንቱ በሕትመት የመገናኛ ብዙኃን ዘርፍ የረጅም ጊዜ ልምድ ያላቸው ጋዜጠኛና ደራሲ እንዲሁም ለተገፉ ሰዎች ተቆርቋሪ ሰው መሆናቸው ይነገራል።