>

ኢትዮጵያ ይዛብን የነበረውን መሬታችንን 92⁰/⁰ አስመልሰናል...!!! (የሱዳን ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ኡስማን ሳለህ)

ኢትዮጵያ ይዛብን የነበረውን መሬታችንን 92⁰/⁰ አስመልሰናል…!!!
የሱዳን ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ኡስማን ሳለህ

ኢታማዦር ሹም፦ እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያ ይዛብን የነበረውን መሬታችንን 92⁰/⁰ መልሰና ።
ጋዜጠኛው አሁንም በኢትዮጵያ ስር የቀረ «.የሱዳን መሬት አለ .?»
ኢታማዦር ሹሙ፦ አዎ አለ ግን አሁን ላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ስራዊት እንደሚባለው ደካማ አይደለም ሀይሉን አደራጅቶ በተጠንቀቅ ቆሞ ነው የሚገኘው
 ጋዜጠኛው፦ ስለዚህ እናተ ወደፊት መሄድ ያልቻላችሁት የኢትዮጵያ መከላከያ
ስራዊት ስላለ ነው .?
ኢታማዦሩ፦እንደነገርኩህ የኢትዮጵያ መከላከያ ስራዊት በውጭ እንደሚወራው ደካማ ትጥቅና ትንሽ የሰው ሀይል ያሉት አይደለም ! በሚዲያ የሚወራውና እመሬት ላይ ያለው የተለያዩ ናቸው !
.
ጋዜጠኛው፦ የኢትዮጵያ መከላከያ ስራዊት የተረዳጀና እስካፍንጫው የታጠቀ ከሆነ እንዴት ይሄንን ሁሉ መሬት ወደ ውስጥ ገብታችሁ ያዛችሁ ?
ኢታማዦር ሹሙ፦ እንደዛ አይደለም።
እኛ ከኢትዮጵያ ጋር በጦርነት አሸንፈን የያዝነው መሬት የለም። የኢትዮጵያ መከላከያ ስራዊት ለቆ ሲሄድ እኛ ተከትለን ነው የሰፈር ነው። የተወሰኑ የአማራ ሚኒሻዎች የደፈጣ ውጊያ አድርገው ብዙ ሰው ገለውብናል
እንጅ” የኢትዮጵያ መከላከያ ስራዊት ጋር አንድም ቀን የፊት ለፊት ጦርነት ገጥመን
አሸንፈን የወሰድነው መሬት የለም።
.
ጋዜጠኛው፦ አሁንስ ከግብፅ ጋር ያደረጋችኋቸው ልምምዶች ለኢትዮጵያ ማስጠንቀቂያ ነበር የሚባለው እውነት ነው. ?
ኢታማዦር ሹሙ፦ በሚዲያ እንደዛ ይበላል እንጅ፣ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት የምትገባበት ነገር የለም። ግብፆች ፍላጎት ሊኖራቸው ይችላል፣ ጦርነቱ ከተነሳ ግን መቆም ወደማይችልበት ሁኔታ ስለሚቀየር እኛ ጦርነቱን ሳይሆን ሰላማዊ ድርድሩን ነው የምንፈልገው !
Filed in: Amharic