>

ኢትዮጵያን የብልፅግና ሳይሆን የብልግና ተምሳሌት የሚያደርግ ጉዞአችሁን አቁሙ ብለናል...!!! (ጎዳና ያእቆብ)

ኢትዮጵያን የብልፅግና ሳይሆን የብልግና ተምሳሌት የሚያደርግ ጉዞአችሁን አቁሙ ብለናል…!!!

ጎዳና ያእቆብ

 

*… እኔ ሊገባኝ ያልቻለው በአዲስ አበባ ስንት ሚሊዮን አርሶ አደር ነው ያለው? ለልማት ተነሺውስ እውነት አርሶ አደሩ ብቻ ነው? ድሮስ አርሶ አደሩንም ይሁን ሌላውን በልማት ስም የተፈናቀለውን የገፋው ማን ነው? ያው እነ አዳነች አቤቤ ያደጉበት ኢህአዴግ አልነበረም? አጥፍተናል ይቅርታ ይደረግልን ብለው ተለሳልሰው በለውጥ ስም የገቡት እንሱው አይደሉም? 
አሁን ደርሶ ወቃሽ: ከሳሽ ሲያሻቸውም ሆደ ሰፊና ይቅርታ አድራጊ መስለው የመቅረብ የግብዝነት ብቃት ከየት የመጣ ነው? ማን ነው <አርሶ አደሩን>> ያፈናቀለ? ማንስ ነው ከመፈናቀላቸው ያተረፈ? ለተቀረው አዲስ አበቤ ላለፉት 27+3 አመታት የፍትህ እጦት: ግፍ: መፈናቀል ካሳ ሚከፈለውና ምላሽ የሚሰጠው ለመሆኑ መች ነው?
እንዴት 3 አመት ሙሉ የግብር ከፋዩን ሀብት ትጫወቱበታላችሁ? እንዴትስ ይህንን ያህል ሕዝብ ትንቃላችሁ? እንዲህ አይነት እብሪት ነው የዛሬ ሶስት አመት የሕዝብ የቁጣ ማእበል በህዋሓት ላይ ብቻ ሳይሆን በመላው ኢህአዴግ ላይ የመጣው:: ግፍን መፍራት ጎጂ ባህል እንደሆነባችሁ ግልፅ ቢሆንም ቢያንስ ለስልጣናችሁ ማቆያ እንዲሆን ሕዝብ መናቅ ተዉ::
እንዲህ አይነት ብልሹ አሰራር የ ኦሮሞን ባህልና እሴት ወግ የማይወክል ለኦሮሞም የማይጠቅም ነውና ባህላችንን ወጋችንን እና መልካም ስማችንን አታጥፉ:: ለልጆቻችንና ለልጅ ሎጆቻችን ግፍናና ቂም አታውርሱ::
እንዲህ አይነቱ በማኅበረሰብ ንግድ ትናንት ህዋሓት በስሙ ለሚምልና ለሚገዘትበት ለትግራይ ማኅበረሰብ ከማይነገር የሰቆቃ ዳፋና ጥላቻ በቀር የተረፈው ነገር እንደሌለ አስቡ:: እብድ ማለት ለመሳሳይ ስራ ደጋግሞ እየሰራ የተለየ ውጤት የሚጠብቅ ነውና ከኦሮሞ ማኅበረሰብ ጫንቃ ላይ ወርዳችሁ እራሳችሁን ችላችሁ እበዱ:: የስልጣን ዘመን እንደሆነ እንደማንኛውም ነገር ይወለዳል: ያድጋል: ይጎለምሳል: ያረጃል በመጨረሻም ይሞታልና የማይሞት ክፉ ስምና ጥላቻ ለማኅበረሰብ ጥላችሁ አትለፉ::
በኦሮሞ ላይ የምትፈፅሙት cultural Genocide ዘላቂነት ያለውና ብዙ ጣጣ የሚያመጣ እንደሆነ እናንተም ለዛላለም በስልጣን ላይ እንደማትቆዩ አስተውሉ:: ለማንም ብላችሁ ሳይሆን ይህ የስልጣን ሆይሆይታ ሲያልፍ እንዴት ነው የምንኖረው? ልጆቻችንስ የልጅ ልጆቻችንስ የትና እንዴት ነው የሚኖሩት ብላችሁ አስቡ:: እናንተ በምትፈፅሙት ግፍ ለትውልድ እዳ የሚያመጣ ስንት የአኖሌን ሀውልት በምትገፉት ማኅበረሰብ ልብ ውስጥ እየገነባችሁ እንደሆነ ቆም ብላችሁ አስቡ::
ትላንት የናንተ ጌቶች የት እንዳሉ: የሚነግዱበት ማኅበረሰብ ደግሞ የሚያልፍበትን የማይገባ መከራ ልብ በሉ:: ለነገሩ ልብ ቢኖራችሁ እንደዚህ አይነት አይናውጣ ባልሆናችሁም ነበር::
እኔ የማዝነው በናንተ እኩይ ተግባር ካለስሙ ስም የሚሰጠው ደጉ የኦሮሞ ማኅበረሰብ ነው:: ሀጫሉ ሁንዴሳ እውነቱን ነው << በብልፅግና ዘመን ለኦሮሞ የተረፈው ነገር ቢኖር ስድብ ነው>> ያለው:: አንባሩን ያጌጠበት ሌላ ተከሳሽ….. አለ ዘፋኙ::
የኦሮሞን ወጣት በየቦታው እየደፋችሁ: አናቶች አባቶችንና እመጫቶችን በእስር ቤት እያጎራችሁ በአደባባይ በኦሮሞ ስም ሀብት እየተቀራመታችሁ እንደማንኛውም ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ኑሮውን ለማሸነፍ ቀን ከሌት የሚደክመውንና በአብዛኛው ከእለት ጉርሱ የተረፈ ነገር የማያገኘውን የኦሮሞ ማኅበረሰብ ጥላቻ ታከማቹለታችሁ::
በናንተ ምክንያት መልካም ስሙ ይጠፋል: ይጎድፋል: ይቆሽሻል:: ጥጃ ጠግባ ሳትጠባ ላይ የማያልበልው ማኅበረሰብ በናንተ ስግብግብና አልጠግብ ባዮች አይን ይታያል:: አይ እናንተ ለኦሮሞ ማኅበረሰብ ላይ ለሰራችሁት በደል ፈጣሪ ሲከፍላችሁ ብቻ ያሳየኝ::
በኦሮሞ ስም ያፈናቀላችሁት: የገደላችሁት: ያረዳችሁት የአማራ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ደም እዳ በናንተ ላይ እንጂ በልጆቻችሁና በደጎ የኦሮሞ ማኅበረሰብ ላይ እንዳይደርስ ፀሎቴ ነው:: እናንተ የማትጠግቡ  አያ ጅቦች ስለሆናችሁ የሚደርስባችሁን መከራ የስራችሁን  ጀባ ከማለት ውጪ ምን ይባላል:: የምትጓዙበት መንገድ ኢትዮጵያን የብልፅግና ሳይሆን የብልግና ተምሳሌት የሚያደርግ ነው::
Filed in: Amharic