ጎዳና ያእቆብ
የ US-EU Roundtable ውይይት እጅግ በጣም ልብ የሚሰብርና አይን ገላጭ ነው:: 353,000 ትግራዋይ የረሀብን ጉንፋን እየሳሉ ባሉበት በዚህ ወቅትና ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚፈልጉበት ሁኔታ ላይ ናቸው ዜጎቻችን ያሉት::
በኢትዮጵያ ውስጥ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ናቸው ያሉት:: የአማራውም መከራ ቀጥሏል:: ወሎ ውስጥ እንዲሰፍሩ የተደርውጉ አማራ ተፈናቃዮችም በዚህ ሰአት በረሀብ አለንጋ እየተገረፉ ነው ያሉት::
ተአማራዊ ብልፅግና እያሉ በዜጎች መከራ ላይ የሚቀልዱትን ትተን በአንድነት ልንቆም: አንዳችን የአንዳችን መራብ መጠማት መታረዝ መከደል መደፈር መፈናቀልም ሊሰማንና ከሚያዝኑት ጋር አብረን ልናዝን ይገባል::
በመጣው በውጭ ጫና ላላፉት ሁለት ሳምንታት የአማራው መታረድ ጋብ ማለቱን እንደ እፎይታ ክፍለ ጊዜ ልንቆጥረው የምንችል ይመስለኛል:: በርካታ ነብስ በግፍ ከመታረድ ድኗል:: ጫናው ሲበዛ መግደል መቆሙም ወንጀሉ የሚፈፀመው ጫካ ባሉ በአሽባሪ ብድኖች ሳይሆን በራሱ በምንግስት እንደሆነ ጥሩ ማሳያ ነው::
በዚህ ሰአት የአለም መንግስታት ማንን ሰምተው ጫና አመጡ የሚለው ሳይሆን የሚያሳስበኝ ጫና በመፈጠሩ ምክንያት አማራን በማንነቱ እየመረጡ ማረዳቸውን ማቆማቸውን እንደ የጋራ ድል ልንቆጥረው ይገባል:: ለጊዜው ያቆሙት ማረድ ጫናው ጋብ ሲልላቸው መቀጠላቸው ስለማይቀር ጊዜአዊውን እፎይታ ዘላቂ ለማድረግ በአንድነት መስራት: ለይቶሳይሆን ለግፉአን ሁሉ እኩል መጮህን መለማመድ ይኖርብናል::
ይህ ካለፉት 27 አመታት የቀጠለውን የግፍ አገዛዝ ከተሰቀለበት ማማ አውርደነው እና ለሕዝብ ድምፅ ጆሮ ያለው መዋቅራዊ ዲሞክራሲንና የዜግነት ፓለቲካን አስፍነን ስንጨርስ ዛሬ የሚያጨቃጭቁን ነገሮች እልባት ያገኛሉ::
ግፈኞች በሹፈት ይቅርታ ሳይሆን በበፍትህ አደባባይ በህግ ይዳኛሉ:: የፈሰሰውን የንፁኃንን ደም ከእጃቸው አንድ ሁለት ብለን ቆጥረን እንወስዳለን::
እስከዛው ግን ነገሮች ሁሉ ቅደም ተከተል አላቸውና ማን ተሰማ ማንስ አልተሰማም ከሚል ንትርክ ወጥተን ህዝባችንና ሀገራችንን እንታደግ:: እዬዬም ሲዳላ አይደል? ሌላው ነገር ቀን: ሁሉን አሳታፊ ውይይት: ብሔራዊ እርቅና እና መዋቅራዊ ለውጥ ይፈታዋል:: በመከራ ላይ ላላችሁ ወገኖቼ ሁሉ አይዟችሁ ለማለት እወዳለሁ::
በዚህ በተከፋፈልንበትና እርስ በርሳችን በተጨካከንበት ወቅት ተስማሙ ተወያዩ ጦርነት አቁሙ እርቀ ሰላም ፍጠሩ ለሚሉን የሚያስታርቁ ብፁአን ናቸው የሚለውን የመድኃንያለምን ቃል በማስታወስ ብሩክ ሁኑ እላለሁ::