>

"ኢዜማዎችን " የኮንቪንስና ኮንፊውዝ " ኤጀንት እንደሆኑ ነው የገባኝ....!!!" (መስከረም አበራ)

ኢዜማዎችን ” የኮንቪንስና ኮንፊውዝ ” ኤጀንት እንደሆኑ ነው የገባኝ….!!!”

መስከረም አበራ

በፊት ኢዜማዎች ውስጥ የሚገቡኝ ሰዎች ነበሩ። አሁን አሁን ግን አይገቡኝም። ኮንፊውዝ ሆነው ኮንፊውዝ እያደሩግኝ ነው። በተቃዋሚው በኩል የመንግስት ረዳት ተዋዋናያን የሆኑ ብሄራዊ መግባባት ከማይፈልጉት ውስጥ በምሳሌነት የሚጠቀሰው ኢዜማ ነው። ከቴሌ መሸጥ በተመለከተ ብቻ ካልሆነ ምንም ከመንግስት የሚለይበት ነገር የለም ። ኢዜማዎች ሽግግር መንግስት አያስፈልግም ይበሉ ጥሩ ግን ዲያሎግ አያስፈልግም ማለት ምንም ሊገባኝ አይችልም።
እስከተወሰነ ድረስ እኔ ኢዜማዎችን አምን ነበር አሁን  ግን እየገባኝ ያለው የኮንቪንንስና ኮንፊውዝ ኤጀንት እንደሆኑ ነው።
ኮንቪንስና ኮንፊውዝ የብልጽግና ፖሊሲ ብቻ አይደለም። ኢዜማም የሚጋራው ይመስለኛል። ቁርጠኛ የነበሩና ጫካ ድረስ የገቡ ሰዎች ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መንግስት ጥሰት ሲደረግ በስሙ ጠርተው እንኳ ሲያወግዙ አይሰሙም። አብይ የፈጠረው ቀውስ አይደለም ቢሉም እንኳ ድርጊቱን በስሙ ጠርቶ ማውገዝ ይቻል ነበር። መንግስት ጥረት አለማድረጉን እንኳ ሲኮንኑ አይታይም። ከዚህ ውጪ በኢዜማ ሰዎች ውስጥ ስልጣን ከሰሜን ወደ ደቡብ እንዲሸጋገር የሚሹ እንዳሉ ይታወቃል ስለዚህ  የፓራዳይም ሽፍት መኖሩ ተመችቷቸዋል።”
Filed in: Amharic