ወያኔና የማይነገሩለት አለማቀፍ ወንጀሎቹ. . . !!!
አቻምየለህ ታምሩ
የወያኔው ቅምጥ ማርቲን ፕላውት በትግራይ ሕዝብ ላይ የኬሚካል ጦርነት ሊከፈት እንደሆነ አድርጎ ዛሬ ያሰራጨው ወሬ ወያኔ ራሱ በትግራይ ሕዝብ ላይ ለመፈጸም ያሰበውና እየጠየቀው ያለው አለማቀፋዊ ወታደራዊ ጣልቃገብነት የግድ እንዲል የወጠነው የወንጀል መርኅ ግብር አለመሆኑን እርግጠኛ መሆን አይቻልም።
ወያኔ አለማቀፍ ወንጀሎችን በትግራይ ሕዝብ ላይ እየፈጸመ ሌሎች እንዳደረጉት አስመስሎ ከጣራው በላይ በማስጮህ ያልተቋረጠ አለማቀፍ ድጋፍና ርዳታ የማግኘትና ፖለቲካ የመስራት የ47 ዓመታት ልምድ ያለው የወንጀል ኢንተርፕራይዝ ነው። በየቴሌቭዥኑ በትግራይ ሕዝብ ላይ እንደተፈጸመ የምንሰማውን የጭካኔ አይነት ሁሉ በተሳካ አኳኋን የመፈጸመ የ47 ዓመታት የደረጀ ልምድ ያለው ወያኔ ራሱ ነው።
በ1977ቱ ርሀብ ካለቀው የትግራይ ሕዝብ መካከል ብዙውን ማትረፍ ይቻል ነበር። ሆኖም ግን ወያኔ ሕዝቡ እንዲያልቅና አለማቀፍ ርታዳ እንዲጎርፈለት ስለፈለገ ሕዝቡን በርሀብ እንዲያልቅ አድርጎ የታረዙትን ለመታደግ የመጣውን ዓለም አቀፍ ርዳታ መሳሪያ ለመግዛት፣ ማለሊትን ለማደራጀትና ሕወሓትን በትጥቅ ለማጠናከር አውሎታል። ይህን የሕወሓት ታሪክ የነገሩን የሕወሓት መስራቾቹ እነ አረጋዊ በርሀና ዛሬ ኬሚካል የጦር መሳሪያ ወደ ትግራይ እንደገባ የሚነግረው እንግሊዛዊው አቃጣሪ ማርፒን ፕላውት ናቸው።
የሐውዜንን ጭፍጨፋ ያቀናጀው ወያኔ ራሱ ስለመሆኑ እንደ አቶ ገብረ መድኅን አርአያ የነገሩን ታሪክ ነው። ብዙ ሰው የማያውቀው ግን ወያኔ የመንፈስ አባቱን ሻዕብያን ለመክሰስ በአይደር ትምህርት ቤት ላይ ያካሄደውን ጭፍጫፋ ነው። በአይደር ትምህርት ቤት ላይ የተካሄደውን ጭፍጨፋ እስካሁን ብዙ ሰው የሚያውቀው ሻዕብያ ያደረገው ጭፍጨፋ እንደሆነ ነው። እኔም መቀሌ መኖር እስክጀምር ድረስ የማምነው ይህንን በስፋት ሲነገር እንሰማ የነበረውን ወሬ ነበር።
ሆኖም ግን መቀሌ መኖር ከጀመርሁ በኋላ ከራሱ ከሕዝቡ ለማወቅ እንደቻልሁት መቀሌ የሚገኘውን የአይደር ትምህርት ቤት የደበደበው ወያኔ ራሱ መሆኑን ነው። እንዲህ አይነት ትልቅ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ አስቸጋሪ ስለሆነብኝ መቀሌ ስኖር የሰማሁትን ነገር በብዙ መልኩ ለማጣራት ሞክሬያለሁ። በስተመጨረሻም አሜሪካን አገር መከጣሁ በኋላ ከቀዳሚ የዐይን ምስክሮች ባገኘሁት ምስክርነት መሰረት ለማረጋገጥ እንደቻልሁት የአይደር ትምህርት ቤትን የደበደበው ወያኔ ራሱ መሆን ለማወቅ ችያለሁ።
አይደርን ወያኔ ራሱ ስለመደብደቡ ያረጋገጡት የዐይን ምስክሮች የአይደር ትምህርት ቤት ሲደበደብ እዚያው መቀሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ግቢ የነበሩትና ድብደባው ከመፈጸሙ ከደቂቃዎች በፊት ወደ ኤትርራ በመብረር ኤርትራ ውስጥ የአውሮፕላን ድብደባ ፈጸመው የተመለሱት የኢትዮጵያ አየር ኃይል አብራሪዎች የነበሩ የወቅቱ ፓይለቶች ናቸው። እኔን የሚጠራጠር ቢኖር ዛሬም ድረስ በሕይዎት ያሉትን የዐይን ምስክር የሆኑትን የኢትዮጵያ አየር ኃይል አብራሩ የነበሩትን ኮሌኔል ፋንታ ኦላናን፣ ጀኔራል አላዲንንና ካፒቴን ተሾመ ተንኮሉን በመጠየቅ ማረጋገጥ ይችላል።
ባጭሩ በትግራይ ሕዝብ ላይ ተካሄደ እየተባለ የምንሰማውን ጭካኔ ሁሉ በትግራይ ሕዝብ ላይ ወንጀል እየፈጸመ አለማቀፍ ድጋፍ የማግኘት ልምድ ያለው ወያኔ እንዳልፈጸመው ርግጠኛ መሆን አይቻልም። በግፍ ባሰራቸው ወንዶች ብልት ላይ ጠርሙስ እያንጠለጠለ ዘራቸውን እንዳይተኩ ሲያኮላሽ፤ አስሮ በሚመረምራቸው ሴቶች ማኅጸን ላይ ፍም እሳት እየጨመረ የኢትዮጵያ ሴቶችን ሲያሰቃይና የውሸት ምስክር እየገዛ በተከሳሾች ላይ በውሸት ሲያስመሰከር የኖረ የጭካኔ አገዛዝ የፈለገውን አገርና አካባቢ ወታደራዊና ልዩ ኃይል ዩኒፎርም እየለበሰና እያስለበሰ ዓለም አይታገሰውም የሚለውን አይነት ጭካኔ በትግራይ ሕዝብ ላይ ከመፈጸምና እንደገና ወደ ስልጣን ያመጣኛል ያለውን ማናቸውንም አለማቀፍ የወንጀል ድርጊቶች ከማድረግ ወደኋላ የማይል መሆኑን እኔ በበኩሌ አልጠራጠርም።