>

የውኃ ላይ ሞት ምንኛ አሰቃቂ ነው? - ነፍስ ይማር  ወገኖቼ.!!!  (ዘመድኩን በቀለ)

የውኃ ላይ ሞት ምንኛ አሰቃቂ ነው?

– ነፍስ ይማር  ወገኖቼ.!!! 

ዘመድኩን በቀለ

… መነሻቸውን ከጂቡቱ ወደብ አድርገው በየመን በኩል ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመግባት በጀልባ ተሳፍረው ጉዞ እንደጀመሩ የተነገረላቸው ኢትዮጵያውያን የተሳፈሩበት ጀልባ በመስጠሟ ምክንያት በአንድ ጊዜ በጀልባዋ ተሳፍረው የነበሩት 300 ያህሉ ኢትዮጵያውያን ሰጥመው መሞታቸው ተነግሯል።
… የመን በዕድል የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን በየመን የሚጠብቃቸው እስር፣ እንግልት፣ ራብ እና ስቃይ ነው። የመን ጦርነት ላይ ናት። በጦርነቱ መሃል ከሳዑዲ በሚጣሉ ቦንቦች ተቃጥለው የሚሞቱትም የትየለሌ ናቸው። በራብ የሚሞቱትም የትየለሌ ናቸው።
በእሳቱ… በዐውሎና በወጀቡ… የበረሃውን እሳተ ገሞራ የመሰለ አሰቃቂ የሞት መንገድ አልፈው እንደ ዕድል ሆኖ ሳዑዲ የሚገቡትም ቢሆን በሳዑዲ የሚገጥማቸው እና የሚጠብቃቸውም አማሰለ ሲኦል ወደሚሆን ዘብጥያ፣ ወኅኒ ቤት መወርወር፣ ጀርባቸው እስኪላጥ መደብደብ እና መገረፍ፣ ነው።
… ይሄ ሁሉ ሞት ከፊቱ ተደቅኖ ኢትዮጵያውያን ግን ወደሞት ከመትመም ወደ ኋላ ሲመለሱ አይታይም። በሃገር ውስጥ ስደት ሶርያን የበለጥን እኛ ይህ የሞት ዜና እየተሰማ እንኳ ሺዎች ወደ ሶማሊ፣ ወደ ኬንያ፣ ወደ ሱዳን ሊቢያ፣ ወደ ጂቡቲ፣ በመሰደድ የበረሃ ጉዞ ላይ ናቸው። የ300 ኢትዮጵያውያንን በባህር ላይ መስመጥና መሞት የሰሙ ቀሪ ስደተኞችም ሌላ ጀልባ በመጠባበቅ እና ወደ የመን ለመሰደድ በተስፋ የጅቡቲ ወደብ ላይ ተቀምጠው ስደቱን በመጠባበቅ ላይ ናቸው። የውኃ ላይ ሞት ደግሞ እጅግ አስጨናቂ ነው።
… ነፍስ ይማር … በሰላም እረፉ።
Filed in: Amharic