>

የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች   በፈፀሙት ጥቃት ከአስር በላይ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ሰራተኞች ተገደሉ...!!! ሚዛን ቴሌቭዥን 

የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች   በፈፀሙት ጥቃት ከአስር በላይ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ሰራተኞች ተገደሉ…!!!
ሚዛን ቴሌቭዥን 

*… ግድያውም ብሄርን ለይቶ የተፈፀመ ጥቃት መሆኑ ታውቋል
 
*…. ግድያው ምርጫ ሊካሄድ ጥቂት ቀናት ሲቀሩት የተፈፀመ ጥቃት በመሆኑ  ለመሸፋፈን እየተሞከረ ነው ተብሏል
 
በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎችበኦሮሚያ ክልል ግንደበረት አካባቢ በተፈፀመው እገታ ትናንት ማምሻውን የተገደሉት ከአስር የሚበልጡት እነዚሁ ሰራተኞች ድልድይ ጠግነው ወደ ካምፖቸው ሲመለሱ መሆኑን  በስፍራዉ የነበሩ የአይን እማኞች ለሚዛን ቴሌቭዥን አረጋግጠዋል፡፡
ጥቃቱ የደረሰባቸዉ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ስራተኞች ግንደበረት አካባቢ ድልድይ ለመጠገን ከአዲስ አበባ ዋናው መስሪያ ቤት የተላኩ መሆናቸውንም ለማወቅ ተችሏል::
ሰሪተኞቹ በኦነግ  ታጣቂዎች ብዙ ስቃይ ከደረሰባቸው በኃላ በጅምላ እንደተገደሉ የመረጃ ምንጫችን አረጋግጧል::
በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በግፍ የተገደሉት የኢትዯጵያ መንገዶች ባለስልጣን ሰራተኞች መሀንዲሶችን ጨምሮ የተለያዪ የሙያ ዘርፍ ያላቸው ናቸው::
ግድያውም ብሄርን ለይቶ የተፈፀመ ጥቃት መሆኑ ታውቋል::
የሟቾችን ብሄርና ስም ካጣራን በኃላ ይፋ እንደምናደርግ ከወዲሁ እንገልፃለን::
በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን መስሪያ ቤት ውስጥ ሀዘኑ እንደተሰማ ቢታወቅም ምርጫ ሊካሄድ ጥቂት ቀናት ሲቀሩት የተፈፀመ ጥቃት በመሆኑ  ለመሸፋፈን እየተሞከረ ነው ተብሏል::
የሟቾቹ አስከሬን ገና ወደ አዲስ አበባ እንዳልመጣም ለማወቅ ተችሏል::
Filed in: Amharic