>
12:50 pm - Friday March 24, 2023

ጸረ አማራነት ተፈጥሮው የሆነው ብአዴን የሚባለው የባንዶች ማኅበር የሚወገድበት ጊዜው አሁን ነው! (አቻምየለህ ታምሩ)

ጸረ አማራነት ተፈጥሮው የሆነው ብአዴን የሚባለው የባንዶች ማኅበር የሚወገድበት ጊዜው አሁን ነው!   
አቻምየለህ ታምሩ

ጸረ አማራነት ተፈጥሮው የሆነው ብአዴን የሚባለው የባንዳዎች ማኅበር አብርሀም አለኸኝ በሚባለው የአማራ ሕዝብ ሸክም በኩል ሲናገር እንደተሰማው የኅልውና አደጋ ለተጋረጠበት የአማራ ሕዝብ የቆመ ሁሉ በጥላቻ የናወዘና ጽንፈኛ እንደሆነ ነግሮናል። ብአዴን አማራን ጠላት ያደረጉ ኃሎችን ጉዳይ እስከጥግ ድረስ ሲያስፈጽም በኖረባቸው ባለፉት ሰላሳ ዓመታት ሁሉ  እንቅፋት ይሆኑኛል የሚላቸውን የአማራ ልጆች ሲያጠፋ የኖረው እንዲሁ ጽንፈኛ እያለና ሎሌ ያደረጉት ድርጅቶች ጀርባ ያለውን ሕዝብ እንደሚጠሉ በመክሰስ ነበር።
ነውረኛው ብአዴን  የሕወሓት ጉዳይ አስፈጻሚ ሆኖ ሲኖር ለሕዝብ ቀድመው የደረሱ የአማራ ልጆችን ሁሉ ሲበላ የኖረው የኅልውና ተጋድሏቸውን የትግሬ ጥላቻ እንደሆነ አድርጎ በማቅረብ ነበር።
ከአራት  ዓመታት በፊት አደባባይ የወጡ የአማራ ልጆች በባሕር ዳር፣ በጎንደር፣ በወልድያ፣ በመርሳ፣ በቆቦ፣ ወዘተ. . . በሕወሓት ስናይፐር የወደቁትም ባንዶቹ እነ አብርሀም አለኸኝ ዛሬ ከነ ዐቢይ አሕመድ በትዕዛዝ ተቀብለው ሲያስተጋቡት የምንሰማውን አይነት ተመሳሳይ የሐጢአት ክስ ከተዥጎደጎደባቸው በኋላ ነበር።
ከሕወሓት ነውረኛ ድርጅትነት ወደ ኦሮሙማ ጉዳይ አስፈጻሚነት ከተሸጋገረ ወዲህ ደግሞ ለጉዳይ አስፈጻሚነቱ እንቅፋት ይሆናሉ የሚላቸውን የአማራ ልጆች የሚከሳቸው በኦሮሙማ ጥላቻ ነው።
በመሰረቱ አማራ በአማራነቱ እንዲደራጅ ከተገደደባቸው ምክንያቶች ቀዳሚው ብአዴን የሚባለው ከአማራ ሕዝብ ባሕል፣ ታሪክ እና እሴት የተፋቱ፣ እንጥፍጣፊ ኢትዮጵያዊነት፣ ኅሊና እና ወገናዊነት የሌላቸው ወያኔዎች “ገ’ለን ቀብረነዋል” ያሉት አማራ ከተዘጋጀለት የቁም መቃብር መግነዙን ቀዳዶና በጣጥሶ፤ የጫኑበትን የመቃብር ድንጋይና አፈር ፈነቃቅሎ ወደ ብርሃን አለም እንዳይወጣ መቃብር ጠባቂ እንዲሆኑ ተደርገው የተፈጠሩ ባንዶች ማኅበር እና የወንጀለኞች ስብስብ መኖሩ ነው።
በእጀ መድኀኒቱ ሐኪም በፕሮፈሰር አስራት ፕሬዝደንትነት  የተመሰረተው ቀዳሚው የአማራ ድርጅት መዐሕድ የተፈጠረው የሕወሓቱ  ነውረኛ ድርጅት ብአዴን በ1986 ዓ.ም. ባሳተመው ድርጅታዊ ፕሮግራሙ ገጽ ሁለት ላይ በግልጽ እንደነገረን  ወራሪ፣ ነፍጠኛ፣ ትምክሕተኛና ብሔረ፣ ብሔረሰቦችን ሲጨቁን ኖረ ያለውን የአማራ ሕዝብ ለማጥፋት እንደሚታገል አላማውን ይፋ ማድረጉ ተከትሎ ነበር።
ለዚህ ዓላማ የተፈጠረው ብአዴን እስካለ ድረስ፤
1ኛ፡ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማና ካርታ ብቻ ይዘው ኢትዮጵያ የሁላችን አገር እንድትሆን የሚታገሉ የአማራ ልጆችን ቀለብ  ከሚሰፍሩላቸው ጌቶቻቸው በትዕዛዝ በሚወርድላቸው መመሪያ  መሰረት በጥላቻና በጽንፈኛነት የሚከሱ፤ የሚያሳድዱና የሚገድሉ የአማራ ባንዶች መጠጊያ ያገኛሉ፤
2ኛ፡ ኦሮምያ የሚባል በኢትዮጵያ እምብርት ላይ የበቀለን እባጭ አማራ የማይኖርበትና አማርኛ የማይነገርበት አገር ለማድረግ የተቆረጠ ካርታ አንጠልጥለው ሲዞሩ የሚውሉ ኦነጋውያንን [ኦሕዴዶች ሁሉ ኦነጋዊ እንደሆኑ ልብ ይሏል] ፍላጎት እስከጥግ ድረስ ለማስፈጸም ፍቃደኛ የሆኑ እንደ አብርሀም አለኸኝ አይነቶቹ ብአዴናዊ “ኤሊቶች” እንዳሸን ይፈላሉ፤
3ኛ፡  እነ በረከት ሰምዖን የግዑዛን ሎሌዎቻቸው ማኅበር የሆነውን ነውረኛ ድርጅት በእንደራሴነት ፈጥረው በተለይም ሰሜኑ አማራ [የአማራ ክልል ላለማለት ነው] እንዳይተማመንና አንድ ልብ እንዳይሆን አስልተው የዘረጉት፤ ዛሬም እነ ዐቢይ አሕመድ እየተጠቀሙበት ያለው የቢሮክራሲና የቁጥጥር ስርዓትን እንዳለ ይቀጥላል።
ስለዚህ አማራ አገር አልባ የሆነው፤ ኢትዮጵያም የአማራ መታረጃ ቄራ የሆነችው ብአዴን  የሚባለው የአማራ ርግማን አማራ ለማጥፋት ባካሄደው ትግል መሆኑን [ብአዴን በ1986 ዓ.ም. ያሳተመውን ድርጅታዊ ፕሮግራም ልብ ይሏል] የሚያውቅና የሚጣላ ኅሊና ያለው ሰው ሁሉ የኦሮሙማ ጉዳይ አስፈጻሚዎቹ እነ አብርሀም አለኸኝና መሰል ባንዶችን ከአማራ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ለማስወገድ የሚቻለውን ጠጠር ሁሉ  ይወርውር። አማራው እንዳይተማመንና አንድ ልብ እንዳይሆን ለማድረግ እነበረከት በአማራው መሀል የዘረጉት የቢሮክራሲና የአገዛዝ ባሕል እስካልፈረሰና  አብርሀም አለኸኝ  በዋና ጸሐፊነት የተሰየመበት የባንዶች ማኅበር ከአማራ ሕዝብ ጫንቃ ላይ እስካልተወገደ ድረስ ኢትዮጵያ የአማራ መታረጃ ቄራ ሆና መቀጠሏ ሳይታለም የተፈታ ነው።
Filed in: Amharic