>

የታላቁን ኢትዮጵያዊ ሊቅ የፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌን ነፍስ ይማር! (ግዛቸው ጥሩነህ (ዶ/ር))

የታላቁን ኢትዮጵያዊ ሊቅ የፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌን ነፍስ ይማር!

ግዛቸው ጥሩነህ    ዶ/ር


የፕሮፌሰር ጌታቸውን ሞት በቅርቡ ስሰማ በጣም አዘንኩ፡፡ ፕሮፌሰር ጌታቸው ስለ ሀገራቸው ኢትዮጵያ የጻፏቸውን በርካታ መጽሃፍትና አጫጭር ጽሁፎች፤ ብዙ ኢትዮጵያውንና የአለም ተመራማሪዎች በሚገባ ያውቃሉ፡፡ ስለእነዚህ አበይት ጽሁፎቻቸውም አንዳንድ ኢትዮጵውያን ሰሞኑን በጽሁፍ ገልጸውልናል፡፡ 

ከፕሮፌሰር ጌታቸው ጋር የተዋዎቅሁት፤ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1990ዎቹ መጀመርያ አካባቢ “ኢትዮጵያን ሬጅስተር” የሚባል መጽሄት በሚያሳትሙበት ግዜ ነው፡፡ በተለይም የዛሬ 10 አመታት ገደማ፤ አንድ መጽሃፍ ስለኢትዮጵያ በምጽፍበት ግዜ ለአስተያየትና ለትችት ጠይቄአቸው የለገሱኝ ሀሳቦች፤ መጽሃፌን የተሻለ ጥራት እንዲኖረው ረድተውኛል፡፡ 

ከጥቂት አመታት ጀምሮ ደግሞ፤ በስልክና በኢሚኤል ብቻ ሳይሆን በአካልም ከእሳቸውና ከባለቤታቸው ከወይዘሮ ምስራቅ ጋር በኒወርክ ከተማ ከአንዴም ሁለት ግዜ ተገናኝተናል፡፡ ምናልባትም ብዙ ሰዎች እድል አጋጥሟቸው ስለ ፕሮፌሰር ጌታቸው የማያውቋቸውን፤ ሰውን የማክበር፤ የማቅረብና የመውደድ ባህሪዎቻቸውን ፤ በአካል በተገናኘንባቸው አጋጣሚዎች በሚገባ ተገንዝቤአለሁ፡፡ 

ኢትዮጵያ በርግጥም ታላቁን ልጇን አጥታለች፡፡ ለቤተሰባቸው ጽናቱን ይስጥልኝ! አምላክ ነፍሳቸውን ይማር!

Filed in: Amharic