>

ከባባድ መሳሪያዎችን የታጠቀ የትግራይ ልዩ ሀይል በራያ ጦርነት መክፈቱ ተሰማ...!!! ( አሻራ ሚዲያ 16/10/13/ዓ.ም ባህር ዳር)

ከባባድ መሳሪያዎችን የታጠቀ የትግራይ ልዩ ሀይል በራያ ጦርነት መክፈቱ ተሰማ…!!!
  አሻራ ሚዲያ 16/10/13/ዓ.ም ባህር ዳር

የትግራይ ልዩ ሀይል ትናንት ቀን ስምንት ሰዓት ጀምሮ በራይ ቆቦ ባላ ወረዳ ቢሶ በር ቀበሌ ጦርነት እንደከፈተ ነዋሪዎቹ ተናግረዎል። ከፍተኛ መሳሪያ የታጠቀው የትግራይ ልዩ ሀይል ቢሶ በር ቀበሌ ላይ በመመሸግ ጦርነቱን ከፍቷል ነው የተባለ፡፡
እንደ ነዋሪዎቹ ገለፃ ትናንት በተጀመረው ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ደህንነታቸው አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ይገኛል። ሲቪል ልብስ የለበሱ ወደ ከተማው በመግባት ዝርፊያ መፈጸማቸው ታውቋል፡፡ በመጨረሻም አሁን ላይ ማህበረሰባችን ራሱን ከመጠበቅ ውጭ ምንም ማድረግ አልቻለም ነው ያሉ፡፡
የአማራ ልዩ ሀይል ባለው መሳሪያ እየተከላከለ ቢሆንም የትግራይ ልዩ ሀይል በያዛቸው ከፍተኛ መሳሪያዎች ጥቃት እያደረሰ ነው፡፡ የትግራይ ልዩ ሀይል በአካባቢው ስለመሸገ በየትኛውም ጊዜ ጉዳት ሊያደርሱብን ይችላሉ  ሲሉ ስጋታቸውን ተናግረዋል ነዋሪዎቹ።
Filed in: Amharic