ህዝብ አይሳሳትም ብሎ ሳይንስ የለም፤ ድብን አድርጎ ይሳሳታል…!!!
ቬሮኒካ መላኩ
አዶልፍ ሂትለር ወደ ስልጣን የመጣው የጀርመን ህዝብ መቶ ፐርሰንት መርጦት ነው። ቤኒቶ ሙሶሎኒ ወደ ስልጣን የመጣው በዴሞክራሲያዊ ምርጫ ነው። የጀርመንና የጣሊያን ህዝብ እንድሁም አለም ህዝብ አጨብጭቦ በመረጣቸው እብዶች ፍዳውን አይቷል።
በዚህ ሁለት አመታት የወሎ አማራ ከኦሮሚያ በተለይ ከወለጋ እየተገደለና እየተፈናቀለ የተረፈው እስካሁን ድረስ ወሎ ውስጥ በየሜዳው ፈሰው ይገኛሉ። እነዚህ የወሎ አማራዎች በየሜዳው የፈሰሱት ብልፅግና ባመጣው ጣጣ ተፈናቅለው እንጅ ቱሪስት ሆነው አይደለም። እትብቴ የተቀበረበት የወሎ ህዝብ ልጆቹን ያፈናቀለውን ፓርቲ በመምረጡ ሂሱን እንደ መራራ ኪኒን ዋጥ ሊያደርጋት ይገባል።