>

" ሁሉን አቀፍ ነፃ ፍትሃዊና ተቀባይነት ያለው ምርጫ እንዲካሄድኦፌኮ ጠየቀ...!!!

” ሁሉን አቀፍ ነፃ ፍትሃዊና ተቀባይነት ያለው ምርጫ እንዲካሄድ ኦፌኮ ጠየቀ…!!!


*…ከቀናት በፊት ሰኔ 14/2013 ዓ.ም በተደረገው ስድስተኛ ብሔራዊ ምርጫ ያልተሳተፈው የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ በአንድ ዓመት ውስጥ ሁሉን አቀፍ ምርጫ እንዲደረግ ባወጣው መግለጫ ጠየቀ።
 
ፓርቲው ለአገሪቱ የፖለቲካ ኃይሎች በሙሉ የመፍትሔ ሃሳብ ብሎ የሰነዘራቸውን ሦስት ነጥቦችንም ዘርዝሯል።
በመጀመሪያ ደረጃ ሁሉን አካታች የጋራ መንግሥት እንዲቋቋምና “ያልተሳካ” ብሎ የጠራውን የመንግሥት ተሃድሶ እንዲቀጥል፣ “ሁሉን አካታች ብሔራዊ የመግባባት ድርድር እንዲጀመር” የሚሉ ሃሳቦችን አስፍሯል።
በሦስተኛነትም የጋራ መንግሥቱ በጋራ የሚፈጥር ፍኖተ ካርታ እንዲመቻችና በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሁሉን አቀፍ ነፃ ፍትሃዊና ተቀባይነት ያለው ምርጫ እንዲካሄድም የሚሉ ሃሳቦችን አቅርቧል። https://bbc.in/3qp60nZ
Filed in: Amharic