>

ትግራይ ዛሬ  ሊለቀስላት የሚገባ  አሳዛኝ ምድር ሆናለች - ግድያ ፤ የጅምላ ቀብር ፤ አፈና...!! (ዘላለም መንግስት አብ)

ትግራይ ዛሬ  ሊለቀስላት የሚገባ  አሳዛኝ ምድር ሆናለች – ግድያ ፤ የጅምላ ቀብር ፤ አፈና…ሁሉም መገለጫዋ ሆኗል…!!
ዘላለም መንግስት አብ

በጣም አሳዛኝ ክስተት ነው እየሆነ ያለው። ዛሬ በተለያዩ የትግራይ ከተሞች በርካታ ወጣቶች ግለሰቦች ሴቶች ሴይቀር ተገለዋል። I mean they are assassinated!!
በትግራይ ትልልቅ ከተሞች መቀሌን ጨምሮ ዜጎች በሰላም ወጥቶ መግባት ይቅርና ዘጋግቶ ማደርም ተቸግረዋል። የግድያው ምክንያት ደሞ ሶስት ነው የሚል ነው እንደምንጮቼ።
1ኛው.
ህወሓታዊያኑ ከመንግስት ጋር ጦርነት ውስጥ በነበሩበት ትዓትና እስከዛሬም የየአካባቢያቸውን ሰላም ያስጠብቁ የነበሩ ወጣቶችን አንድ በአንድ እየለቀሙ እየገደሏቸው ነው። እየገቡመዝረፍና መድፈር የየሰዓቱ ተግባር ሆኗል። which is a perfect example for anarchism is happening in Tigrai.
2ኛው.
ሁለተኛው የመገዳደያ ምክንያት ደሞ እዛው ህወሓት (አሸባሪው) ውስጥ የተፈጠረ የመሪነት ሽኩቻ ንትርክና በጎጥ ተቦዳድኖ መገዳደል ነው። ምን አለፋችሁ። ትግራይ በህወሓት አሸባሪው ምክንያት ወደታሪክነት እየተምዘገዘገች ነው።
በጣም አሳዛኝ ነው። መከላከያ ሰራዊት እየሞተም ደፈጣ እይተከፈተበትም በጠበቁት ህዝብም እየተገደለም ሲጠብቅ ይደርስበት የነበረውን ስትሰሙ ደሞ የበለጠ ታዝናላችሁና ለጊዜው አልፌዋለው።
3ኛው.
ሶስተኛው የመገደያ ዋና ምክንያት ደሞ ከሌላ ብሄር በተለይም ከአማራና ኦሮሞ ዘር አለው የተባለ ትንሽም ዘር አለብህ የተባለ በተለይም እነሱ ንጹህ ትግሬ የሚሉት ማለትም የአድዋ ሽሬ አዲግራት ሰው ያልሆነ በሞላ በተለይም ድቅል፣ ኢሮብ፣ ኩናማ እና እንደርታ ከሆንክ ሴት መነኩሴ ህጻን ሳይሉ እየገደሉና እያፈኑ ያልታወቀ ስፍራ ወስደው እየረሸኑና የጅምላ መቃብራትን በማዘጋጄት የአማራ ልዩ ሀይልና መከላከያ የረሸናቸው ናቸው ለማለት እየሰሩ ነው።
አዝኛለው እዘኑ!! ለትግራይ ህዝብ እናልቅስ!!
ትግራይ_ወደየት
ትግራይ በቅፀበታዊ ውሳኔ ወደ መንግስት አልባነት (Stateless) ተቀይራለች። ስለ ትግራይ በፊት ከማስበው በላይ ጭንቅላቴ አሁን ደጋግሞ ሲጨነቅ ይሰማኛል። ጉዳዩ የመከላከያ ከትግራይ የመውጣት ጉዳይ አይደለም። ትግራይ ላለፉት ሁለት ሶስት ቀናት በመንግስት አስተዳደር ስር አይደለችም። መከላከያ ድሮም ድንበር እንጂ ሰፈር ቦታው አይደለም። ነገር ግን ጊዜአዊ የሲቪል አስተዳደሩ ክልሉን ለቆ ወጧል። የቀድሞው የህውሃት አስተዳደር ተመልሶ የመንግስት መዋቅሩን ዘርግቶ ማስተዳደር ይችላልን? ሌላ መልስ አልባ ጥያቄ ነው።
“ከጭፈራ ማግስት ህዝቡ ላይ ግራ መጋባት ይታያል” የሚለው ነገር በዋዛ የሚታይ ጉዳይ አይደለም። ጉዳዩን ከፖለቲካዊ ትርጉም በላይ ወስደን የህዝቡን እጣፈንታ እናስብ። የፌደራል መንግስቱ በቀረቡት ምክንያቶች መሠረት መከላከያን ማስወጣቱ ትክክል ሊሆን ይችላል። ህዝቡ እራሱ መከላከያን የሚወጋ ከሆነ፣ የመከላከያ እዚያ መቆየት ጥቅም የለውም። መንግሥት መዋቅሩን ክፍት ማድረጉ ግን ውሎ አድሮ ትልቅ ችግር ይዞ መምጣቱ የማይቀር መሆኑ ተገማች ነው።
ትግራይን ለጊዜው መንግስት አልባ  ማድረጉ፣ ህውሃት ይመኘው ለነበረው የDe facto state ሙከራና ህልም በር ከፋችም ነው። ለጊዜውም ቢሆን መንግስት አልባነቱ በትግራይ ውስጥ ትልቅ አናርኪዝም እንዳይፈጥር ያስፈራኛል።እየተሰማ ያለውም እሱ ስለሆነ። የእርስ በርስ ግጭቶችም ይገመታሉ። ኃላፊነት የሚወስድ የህዝብ አስተዳደር ከሌለ ህዝብ ውሎ አድሮ ችግር ውስጥ ይገባል።
የትግራይ ህዝብ ሁለት ነገር ሊያደርግ ይችላል። የህውሃትን አስተዳደር መልሶ መትከል አሊያም አዲስ የህዝብ አስተደዳር በሰፈርና በቀበሌ መመስረት። የመጀመሪያውን ማድረግ ከባድ ነው። ስሙም ግብሩም በአሸባሪነት በተፈረጀ ድርጅት ስም አስተዳደር መመስረት በህግ አግባብ የሚያስኬድ አይሆንም። ይህ የሚሆነው ትግራይ እራሷን ወደቻለች ሀገር ከተቀየረች ብቻ ነው። ይሄ ደግሞ ህልም የሚመስል ጉዳይ ነው። ነገሩ ግራ ነው። ምን አልባት ህዝቡ በራሱ መንገድ የህዝብ አስተዳደር እንዲፈጥር ማገዝ መፍትሔ ሊሆን ይችላል።
የፌደራል መንግስቱ ዙሪያውን አጥሮ፣ የመቀሌውን ጭፈራ በአንክሮና በፌዝ እየተመለከተ ነው። ትግራይ ወደ de facto state ብትቀዬር ከሌሎች ሀገሮች ጋር የምትገናኘው እንዴት ነው? ለጊዜውስ ቢሆን ፌደራል መንግስቱ ለትግራይ የሚያስፈልጉ መሠረታዊ ነገሮችን ያቀርባል ወይስ አያቀርብም? ትግራይ እስከመቼ stateless ሆና ትቀጥላለች? ብዙ መልስ አልባ ጥያቄዎች።
ነገሮችን ሁሉ ከህውሃት ጋር ብቻ አያይዞ ማሰብ በሁሉም ወገን አደጋ አለው። በመንግስትም፣ በህዝቡም፣ በህውሃት ደጋፊዎችም ዘንድ። ሁሌም የስበት ማዕከል መሆን ያለበት ህዝብ ነው። ለአንድ ሳምንት የእለት ጉርስ ማቅረብ ምን ያህል ፈታኝ እንደሆነ የሚያውቅ ያውቀዋል። በየቀኑ እየወጣ የሚያላዝነው ዲያስፖራም ትግራይን መልሶ መገንባት ላይ ብቻ ሳይሆን ለህዝብ የእለት ደራሽ ምግብ ማድረስ ላይ ማተኮር እንዳለበት አሳሳቢ አያሻውም። በዚህ ሁሉ መሃል ሊፈጠር የሚችለው Anarchism እና Humanitarian crisis በጣም ያሳስበኛል። ጦርነቱ ከቆሞ ለጋሽ ድርጅቶች ድጋፉን እስከመቼ ይቀጥላሉ? አይታወቅም። እነሱስ Insecurity አይሰማቸውም? ሁኔታው ቀላል አይደለም። ትግራይን ወደ ዳግም ውድመት ሊወስዳት ይችላል። ይሄ ደግሞ ህሊና ላለው ሰው የንፁሃን ሰቆቃ እንቅልፍ ይነሳል። በንፁሃን ስቃይና ሞት ለሚነግዱት ሳይሆን ሰውነት ለሚሰማቸው ያማል።
የፌደራል መንግስቱ ኩርፊያ በሚመስል መልኩ “ህዝብ ራሱ አዙሮ እየወጋን ነው። Insecurity ተሰምቶናል። ለህዝቡ የፅሞና ጊዜ እንስጠው። ጥቅማችን አልታዬውም” ብሎ እጁን ሰብስቧል። “እስኪ የምታመጡትን እንያችሁ?” አይነትም ይመስላል።  ዙሪያውን አጥሮ የጁንታውን አለቆች በንስር ዓይን መከታተል ላይ ብቻ አተኩሯል።
ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ ለትግራይ ህዝብ ጥሩ ተምኔት አይታዬኝም። ህዝቡም ሆነ አክቲቪስቶች መበሻሸቁን ትተው ሰክኖ ማሰብ ቢጀምሩ መልካም ነው። ፕሮፖጋንዳው ዳቦ አይገዛም። ውሃና መብራት አያቀርብም።
በሌላ በኩል የትግራይ ቀጠና የሽብርተኛ መፈንጫም እንዳይሆን ያሰጋል። ጠንካራ የመንግስት መዋቅር አለመኖር የሽብርተኞች ጥሩ መደላድል ነው። ህውሃት ከሌሎች የውጭ ድርጅቶች ጋር አብሮ የመስራት እድሉ ከፍተኛ ነው፣ ምንም እንኳን መግቢያና መውጫ በሮች በጥብቅ ቁጥጥር ስር ቢሆኑም።
Filed in: Amharic