>

ህውሃት ዛሬም - በክህደት እና የሸር ፖለቲካ...!!! (ያሬድ ሀይለማርያም)

ህውሃት ዛሬም – በክህደት እና የሸር ፖለቲካ…!!!

ያሬድ ሀይለማርያም

አፈር ልሳ የተነሳችው ህውሃት ዛሬም በአገር ሰላም እና አንድነት፤ እንዲሁም በንጹሀን ደም ላይ ተረማምዳ የትግራይ ሪፐብሊክን ለመመስረት እየዶለተች እና ነገር እየተበተበች መሆኑን  ያወጣችው መግለጫ ጥሩ ማሳያ ነው። በንጹሀን ደም እጃቸው የጨቀየው የወያኔ መሪዎችም ለተኩስ አቁሙ ጥሪ የሰጡት ምላሽ የትግራይን እና የቀረውን የኢትዮጵያ ሕዝብ  ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማለያየት ሰፊ ገደል እየማሱ መሆኑን እና የክልሉንም ሕዝብ በhostage ይዘው መደራደሪያ ለማድረግ ማሰባቸውን ነው የሚያሳየው። የመንግስት ክልሉን ለቆ መውጣት እንደ ሎተሪ የቆጠሩት የህውሃት አመራሮች በሰሜን ዕዝ፣ በማይካድራ እና በሌሎች የክልሉ ክፍሎች የፈጸሙትን አሰቃቂ ወንጀል ከቁብም ሳይቆጥሩ እራሳቸውን ንጹሕ ተደራዳሪ አድርገው መቅረባቸው ወያኔ የተካነችበትን ውሸት እና የጭካኔ ፖለቲካ ዛሬ ደግሞ በተጠቂነት ስነልቦና አለምን ለማደናገር እየሠራች መሆኑን ነው የሚያሳየው።
የሰላም ድርድሩ እና የተኩስ አቁም ስምምነት እየደገፍን ለመላው አለም ግን ወያኔ በአለም አቀፍ ወንጀሎች፤ አሁን በጦርነቱ ወቅት በተፈጸሙት ብቻ ሳይሆን ባለፉት 27 አመታት ሥልጣን ላይ ሆነው የፈጸሙትን ወንጀሎች በመዘክዘክ አለም ከትግራይ ሕዝብ ጎን እንጂ ከህውሃት ጎን እንዳይቆም ድምጻችንን ማሰማት አለብን። ህውሃት በእድሜው ልክ በወንጀል የተዘፈቀ ጨካኝ ድርጅት መሆኑን ከበቂ በላይ ማስረጃ ስላለ አለም የትግራይን ሕዝብ ከህውሃት ነጥሎ እንዲያይ፣ የሚደረጉ የሰብአዊ ቀውስ ድጋፎች የህውሃት ማንሰራሪያ እና መጠቀሚያ እንዳይውሉ ሁሉም ድምጹን ሊያሰማ ይገባል። የህውሃት አመራሮች ለፍርድ መቅረብ እንጂ አገር መምራት አይችሉም።
Filed in: Amharic