>

የአድዋ፣ ሽሬና አክሱም (አሸአ) ፖለቲካ ...!!! (ወንድ ካበው)

የአድዋ፣ ሽሬና አክሱም (አሸአ) ፖለቲካ …!!!

ወንድ ካበው
አሸአ (የአድዋ ሽሬና አክሱም ፖለቲካ) እንዲህ ላይ ላዩን እንደምናየው ቀላል አይደለም። የአሸአ(አክሱም ሽሬ አድዋ) ልሂቃን በተለይ ህወሀት ጫካ ከገቡ በኋላ የመጀመሪያ መጽዳት ያለበት የኛን ፊውዳል ዘርና አከባቢ ነው የሚል የውስጥ ህግ ነበራቸው። በዚህም መሰረት ህወሓት 3 አከባቢዎችንና የነዚሁ አከባቢ ነዋሪዎችን በጠላትነት ፈርጀው እስካሁን እያጠቋቸው ይገኛሉ። 
እንደርታ
እንደርታ ከቆላ ገረአልታ ጀምሮ እስከ አዲጉዶም ፣ከሳምረ እስከ ህንጣሎ የሚዘረጋ ሆኖ መቀሌ በማዕከልነት የሚጠቀም አከባቢ ነው። የዚህ አከባቢ ህዝብ እጅግ ስልጡን፣ liberalና በአገር ጉዳይ ጠባብነት የማይሰማው ኩሩ ባህል ያደለው አከባቢ ነው።
ህወሓት የዚህን አከባቢ ህዝብ ትምክህተኛና የአድዋ አክሱሜ ኢሊት ላይ ንቀት የሚያሣይ ነው በሚል በተከታታይ በልማትና በፖለቲካው እንዲቀጡ አድርጓል። የነ ገብሩ አስራት ከህወሓት መባረር የዚህ ማሳያ ነው።
መቀሌን ጨምሮ ሙሉ የእንደርታ የኢኮኖሚ መሠረቶች የተያዙት በአድዋ አክሱም ሰዎች ነው።
መቀሌ ላይ እርሻው በግዴታ ለአድዋ ካድሬ የተሰጠባቸው እናት እራሳቸውን ማጥፋታቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው።
ተንቤን
ተንቤን በባህልም ከአሸአና ከሌላውም ትግራይ አከባቢ የተለየ ነው። የዘፈን ስልተ ምታቸው ሳይቀር ከትግርኛ ይልቅ የዋግ አገውኛ ጋር ይመሳሰላል። በነገራችን ላይ የተንቤን ስልተ ምት ዋግ ላይ በተለያየ አከባቢ ባገውኛ ዘፈን ይጨፈርበታል።
ተንቤን ከፊሉ አገው ከፊሉ ትግረኛ ተናጋሪ ተጋሩ ሆኖ መቀላቀሉ አይደለም የህወሀት (አሸአ) ሰዎችን እንደጠላት እንዲያዩት ያደረገው፤ ዋናው ምክንያት አከባቢው የፊውዳል አገር ነው የሚል ነው።
ተንቤን የነ ራስ መንገሻ፣ የነ አሉላ አባነጋ፣ የነ አጼ ዮሐንስ … አገር ነው። ይህ ደግሞ በህወሀት ሰዎች የጨቁነውናል ትርክትን ፈጥሮባቸዋል። ተንቤን ከሁሉም በተለየ በልማት እንድትቀጣ የሆነውም በዚሁ ምክንያት ነው። ከአከባቢው የሚወጡ ፖለቲከኞችም የፊውዳል አስተሳሰብ ያለባቸው ናቸው በሚል በተደጋጋሚ ይመታሉ። የነ ስየ አብርሃ ቁርቁስና እስር ብዙሃኑ የዚሁ አከባቢ ፖለቲከኞች መሆናቸውን ልብ ይሏል።
አዲግራት(አጋመ)
የህወሓት የአጋመ ጥላቻ ጉዳይ ከእንደርታና ከተንቤን ይለያል። አጋመዎች እጅግ ስራ ወዳድ፣ ምንም ስራ የማይንቁ፣ የትም ቦታና የትኛውንም ስራ ቢሠሩ የሚሳካላቸው ታታሪ ህዝቦች ናቸው። ይህ አካሄድ ለህወሓት ሰዎች እብሪትና እኛ እንበልጣለን አካሄድ የሚመች አልሆነም። በርግጥ ከህወሓት በፊት ቀድመው ደርግን ተቃውመው ጫካ የገቡት የአጋሜ አዲግራት ታጋዮች ነበሩ። አዲግራቶችን ህወሓት መግደል የጀመረው እነዚሁኑ ታጋዮች አንዋሀድ ብለው ጠርተው በተኙበት ሁሉንም በመረሸን ነበር።
ስለ ሃብት ውድድራቸው።
አንድ ጓደኛየ የነገረኝን ሹክ ልበላችሁ።
ሙሉ መቀሌ ያሉት ትልልቅ ህንጻዎች የአጋሜዎች ነበሩ አሉ። በጣም የሚቃጠሉ የአድዋ የካድሬ ሃብታሞች ብር ይሰበስቡና ለ3 ሆነው ሁሉንም ህንጻዎች የሚበልጥ ህንጻ ገነቡ። ከዛም የህንጻውን ስም ምን ይሊታል “እርር በይ አጋሜ”
አጋሜዎች ከእንደርታዎች ጋርም በዚሁ (ሠቀሌን ወረውብናል) አልፎ አልፎ ይጎሻሸማሉ። በተለይ የ70እንደርታና የወልዋሎ ኳስ ሲኖር ሁሌም እንደተደባደቡ ነው።
ባጠቃላይ ቀዳማይ ህንፍሽፍሽም ሆነ ኻልአይ ህንፍሽፍሽ (የህወሓት ስንጥቃቶች) የአሸአና ከላይ የጠቀስኳቸው አከባቢዎች ፍትጊያ ውጤቶች ነበሩ።
እናም አሁን ላይ የአሸአ ኢሊቶች በነዚህ አከባቢዎች የከፈቱት የስድብና የጥላቻ ዘመቻ የዛሬ አይደለም። የቆየ ነው።
ያቀንየለይ።
Filed in: Amharic