>
5:13 pm - Friday April 19, 8452

ሁሌም  ታሪክ ራሱን የሚደጋግምባት ምድር ኢትዮጵያ....!!!! (መስከረም አበራ)

ሁሌም  ታሪክ ራሱን የሚደጋግምባት ምድር ኢትዮጵያ….!!!!

መስከረም አበራ 

በጸጥታው ምክር ቤት ፊት ለፊት ሲያበራ ያመሸው ጥቁር አልማዝ ዶ/ር ኢንጅኔር ስለሺ በቀለ –   ለም/ቤት ምን አሉ ?
•  የጸጥታው ምክር ቤት የፖለቲካ እና የጸጥታ ጉዳይን ብቻ የሚመለከት ተቋም ነው፤ የውሃ ጉዳይ እንዲያይ መደረጉ አግባብ አይደለም፤ ምክንያቱም እየገነባን ያለነው የውሀ ግድብ እንጂ የኒውክሊየር ማብላያ አይደለም!
 
•  ኢትዮጵያውያን የአባይ ውሃን የመጠቀም መብት እንዳላቸው የጸጥታው ምር ቤት ሊገነዘበው ይገባል፡፡
 
•  ኢትዮጵያ የዜጎቿን የኃይል ፍላጎት ለማሟላት እና በስደት የሚንገላቱ ወጣቶቿን ለመታደግ ነው የህዳሴ ግድብን የምትገነባው፡፡
 
•  ግድቡ ሰሞኑን ከመካከለኛው ምስራቅ አገራት በባዶ እግራቸው የሚባረሩ ዜጎቻችንን ነፃ ያወጣል፡፡
 
•  ለሱዳንና ለግብፅ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር መፍትሔ የሚያገኘው በፀጥታው ምክር ቤት ሳይሆን በሶስቱ ሀገራት ቀና መንፈስ በሚደረግ ውይይት ነው።
 
•  የታላቁ ህዳሴ ግድብ በትክክለኛ ጊዜ በትክክለኛ ቦታ በኢትዮጵያውያን ሃብት እየተገነባ ያለ ግድብ ሲሆን የግድቡ መሞላት ማንም የሚረዳው ፊዚክሳዊ ቀመር ነው፡፡
 
•  ኮንክሪት ተሞልቶ ዝግጁ ከሆነ ውሃው መሞላቱ የሚጠበቅ ነው።
 
•   ግድቡ በ5 ቢሊየን ዶላር ወጭ እየተገነባ ያለው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በኢትዮጵያውያን ላብ፣ ደምና እንባ ነው፡፡ 
 
•   እኛ የመልማት እንጂ የትኛውንም አገር የመጉዳት ፍላጎት የለንም፡፡ 
 
•   ኢትዮጵያ እየገነባችው ያለው ግድብ ከአፍሪካ ብሎም ከአለም የተለየ አይደለም፡፡
 
•   ኢትዮጵያ ወቅታዊ እና የወደፊት ፍላጎቶች አሏት፡፡
 
•   በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ከ65 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የኤሌክትሪክ ኃይል አያገኙም፡፡
 
•   በኢትዮጵያ ከ25 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ንጹህ ውሃ አያገኙም፡፡ 
 
•  የህዳሴ ግድብ ውሃ የመያዝ አቅም ከግብጹ አስዋን ግድብ በሶስት እጥፍ ያነሰ ነው፡፡
 
•  ለአፍሪካ ህብረት የተለየ ክብር አለን፡፡
 
•  ጉዳዩ የሚመለከተው የአፍሪካ ህብረትን በመሆኑ በጀመረው መሰረት ሚናውን ሊወጣ ይገባል፡፡
 ኢትዮጵያ ዛሬ ያለችበት ሁኔታ በማይጨው ጦርነት ዘመን የነበረችበትን ይመስላል። ያኔም ውድ ልጆቿ በአለማቀፉ መድረክ በመርዝ ጭስ ስለሚያልቀው ህዝቧ ሲማልዱ ፤ ሃገር ውስጥ ያሉ አርበኛ ልጆቿ ከየጥጋጥጉ ተጠራርተው ለነፃነቷ ይዋደቁ ነበር።
 በዚህ ፈታኝ ወቅት ሃገራችን በዓለም መድረክ ፋሽዝምን ከወገነው የሃሰት ዓለም ጋር ስትሞግት ከጎኗ የነበሩ ወዳጅ ሃገራት ዛሬም ስለመልማት መብቷ ሽንጣቸውን ገትረው ተከራክረውላታል። በሃገር ውስጥ በዛ አሰቸጋሪ ወቅት ከሃገር ዳርቻ ለነፃነት ሲዋደቁ የነበሩ ኢትዮጵያዊ  አርበኞችን  ከጀርባ ሲወጋ የነበረው ባንዳም አሁንም አለ!
 በታሪክ ኢትዮጵያ የቀጠለችው ወዳጁም ጠላቱም፣ባንዳውም  አርበኛውም ባለበት ነው።  በየዘመኑ ሰው የማታጣው ሃገራችን ትናንትም  በዶ/ር ኢንጅነር ስለሽ በቀለ ቆፍጣና ሙግት ከፍ ብላለች ፣ በሚገርም የራስ መተማመን የሃገራቸውን እውነት ፈርጠም ብለው ለዓለም ላስረዱት ዶ/ር ኢንጅነር ስለሽ በቀለ ምስጋናችን ታላቅ ነው፣ኮርተናል!!!🙏
 
ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ – በተባበሩት መንግስታት ፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የሰጡት ማብራርያ…
 
ዶ/ር ስለሺ በቀለ ማን ናቸው
በህዳሴ ግድብ ድርድር ላይ ሀገራቸውን ወክለው እየተሟገቱ ያሉት ወርልድ ክላስ የሆኑት ዶ/ር ስለሺ በቀለ ማናቸው ሲል  አሰሳ አድርጓል እንደሚከተለው ይቀርባል።
የኢትዮጵያ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ አውላቸው በአመራር ፣ በምርምር ፣ በማስተማር እና በአማካሪነት ሥራዎች ፣ በኢነርጂ ፣ በመሬት ፣ በአየር ንብረት ለውጥ ፣ በአቅም ልማት እና በፖሊሲ የ 30 ዓመታት ልምድ አላቸው ፡፡
ዶ/ር ስለሺ በቀለ አውላቸው በኒው ዮርክ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ዋና መስሪያ ቤት በኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ጉዳዮች መምሪያ ውስጥ አማካሪ ሆነው ሰርተዋል፡፡
በመጀመሪያ የተባበሩት መንግስታትን ሲቀላቀሉ ለአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) ከፍተኛ የውሃ እና የአየር ንብረት ለውጥ ባለሙያ ሆነው አገልግለዋል፡፡
በተባበሩት መንግስታት ቆይታቸውም በአፍሪካ ፣ በእስያ ፣ በላቲን አሜሪካ እና በካሪቢያን አባል አገራት ብሔራዊ ልማት ዕቅዶች ውስጥ ዘላቂ ልማት እንዲሰፍን አስተዋጽኦ አበርክቷል።
ዶ/ርስለሺ በቀለ ናይል ተፋሰስ እና ለምስራቅ አፍሪካ ዓለም አቀፍ የውሃ አስተዳደር የክልል ጽ/ቤትን በመምራትም መቀመጫቸውን አዲስ አበባ በማድረግ ከፍተኛ ተመራማሪ ሆነው አገልግለዋል፡፡
ከአፍሪካ እና ከሌሎች ክልሎች የተውጣጡ ከ 45 በላይ የሳይንስ ባለሙያዎችን ጥምረት በማስተባበር የናይል ወንዝ ተፋሰስ ፣ የውሃ ፣ ግብርና ፣ የኑሮ ሁኔታ እና አስተዳደርን በተመለከተ አጠቃላይ መጽሐፍ መሪ አርታኢ በመሆንም አገልግለዋል ፡፡
ዶ/ር ስለሺ በቀለ በኢትዮጵያ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዲን እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው አገልግለዋል በዩኒቨርሲቲ ቆየወታቸውም dams and hydropower, irrigation and drainage, water resources and hydrology የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞችን አቋቁሞዋል።
በኢትዮጵያ እና በጀርመን በሃይድሮ ፓወር ፣ በውሃ ሃብት ፣ በተፋሰስ አያያዝ እና በአካባቢያዊ ተፅእኖ ምዘና ትምህርቶችን አስተምረዋል፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሲቪል መሐንዲስነት የተማረ ሲሆን በዩናይትድ ኪንግደም ታይኔ ላይ በኒውካስል ዩኒቨርሲቲ በሃይድሮሊክ ምህንድስናና በሃይድሮሎጂ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል፡፡ በጀርመን ከድሬስደን የቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በውሃ ሀብቶች እና በሃይድሮሊክ ምህንድስና ፒኤችዲ አግኝተዋል፡፡
የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ በኢትዮጵያ አሸናፊነት ከተጠጠናቀቀ በኋላ ኢትዮጵያን በመወከል ዶ/ር ስለሺ በቀለ ለጋዜጠኞች የሰጡት ማብራሪያና ምላሽ 
Filed in: Amharic