የአፍሪቃ አዳራሽ ሥራ
ጦቢያን በታሪክ (ቴሌግራም)
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን በአፍሪካ እንዲከፈት ውሳኔ ሲያስተላልፍ የአፍሪካ መንግሥታት ሕንፃው በኢትዮጵያ ይሁንልን ስላሉ ሥራው እንዲሠራ ዕድል ገጠመው። (ሊቢያ፣ ግብፅ እና ናይጄሪያ እኛ ጋር ይሁን ብለው ቢፎካከሩም ኢትዮጵያ በተመራጭነት እንጂ በተፎካካሪነት አልቀረበችም ነበር።) ታዲያ የጊዜው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ዶ/ር ተስፋዬ ገብረ እግዚእ ስለነበሩ ወደ ጃንሆይ ሄደው ውሳኔውን እንዲናገሩ ሲደረጉ ጃንሆይ ቅድሚያ መጠናት ስላለበት ደጃዝማች መንገሻ እንዲያስጠኑት አዘዙ።
ሜዜ ዲማ የሚባል አማካሪ ድርጅት አጥንቶ ሥራው አምስት ሚሊየን ብር እና ሦስት ዓመት እንደሚፈጅ ተናገረ። ለሥራው የተሰጠው የጊዜ ገደብ ግን አንድ ዓመት ስለሆነ ችግር ሆነ። በሦስት ፈረቃ በቀን 24 ሰዓት እየተሠራ ለመጨረስ እንዲሞከር ተወሰነ። በዚህ ሁኔታ በ10 ወራት ውስጥ የአፍሪካ አዳራሽ ተሠርቶ አለቀ።
ሕንፃው እንዳለቀ 33 የአፍሪካ መንግሥታት መሪዎች በተገኙበት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ተቋቋመ።
ራስ መንገሻ ሥዩም – የትውልድ አደራ ገጽ 116-117
ፎቶ⇑ ጃንሆይ የአፍሪካ አዳራሽ መሠረት ውስጥ የኢትዮጵያ ገንዘቦች ሲያስቀምጡ (ዛሬ ቢከፈት ብሮቹ ይገኛሉ ማለት ነው ፡))