>

አጭር ግልጽ መልዕክት ለክቡር ጀነራል ተፈራ ማሞ (መስፍን አረጋ)  

አጭር ግልጽ መልዕክት ለክቡር ጀነራል ተፈራ ማሞ

መስፍን አረጋ  

ክቡር ጀነራል ተፈራ ማሞ፡፡  የአማራን ሕዝብ በተመለከተ ሰው በጠፋበት ሰው ሁነው በመገኘት ያማራን ልዩ ኃይል ለመምራት ፈቃደኛ በመሆንወ ከፍተኛ አክብሮቴን ልገልጽልወት እወዳለሁ፡፡  እግረ መንገዴን ግን ባዲሱ ሹመትዋ የሚሰማኝን ከፍተኛ ስጋት ልገልጽልወ እፈልጋለሁ፡፡  

የአማራን ልዩ ኃይልና ፋኖን በማዳከም አመርቂ ውጤት አስመዝግቦ ለዐብይ አሕመድ ታማኝነቱን በማረጋገጥ ለከፍተኛ ሹመት የበቃው አቶ ተመስገን ጡሩነህ እና መሰሎቹ፣ አሁንም ቢሆን ይህን ልዩ ኃይልና ፋኖን በሙሉ ልብ መደገፍ ቀርቶ በበጎ ዓይን ይመለከቷቸዋል ብየ አላምንም፡፡  እነዚህ ግለሰቦች አማራዊ ሰብዕናቸው በወያኔ ስለተሰለበ፣ ሊታደጓቸው ከተሰለፉት ከአማራ ልዩ ኃይልና ከፋኖ ይልቅ ሒሳብ ሊያወራርዱባቸው የሚገሰግሱትን ወያኔንና ሳምሪን ቢመርጡ አይገርምም፡፡  

በሌላ በኩል ደግሞ ባማራ ልዩ ኃይል አከርካሪውን ተመትቶ የነበረው ወያኔ፣ በብርሃን ፍጥነት አንሰራርቶ ካማራ ሕዝብ ጋር ሒሳብ ለማወራረድ እስከመዛት የደረሰው፣ በዐብይ አሕመድ ጠቅላይ አዛዥነት የሚመራውን መከላከያን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የተቆጣጠሩት ኦነጋውያን በሚያደረጉለት ከፍተኛ ድጋፍና ማመቻቸት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡  

ስለዚህም ወያኔና ኦነጋውያን ከነ አቶ ተመስገን ጥላሁን ጋር በመመሳጠር ባማራ ሕዝብ ላይ ትልቅ ሴራ እያሴሩ ሆኖ ይሰማኛል፡፡  ሴራውም እሰወን ጀነራል ተፈራ ማሞን ጦርነት ውስጥ በመግደል፣ በማስገደል፣ ወይም በማስማረክ፣ ወይም ደግሞ በእርስወ የሚመራ ዘመቻ ከፍተኛ ሽንፈት እንዲደርስበት በማድረግ፣ የአማራን ሕዝብ ሞራል መግደል ነው፡፡  የእርስወን አዲስ ሹመት በተመለከተ የሚሰማኝ ከፍተኛ ስጋት ይሄውና ይሄው ብቻ ነው፡፡  ስጋቴን ከፍ የሚያደርገው ደግሞ አቶ ዐበረ ዐዳሙ ለሚመራው ሕዝብ የመቆርቆር ስሜት ማሳየት ከመጀመሩ ባጭሩ መቀጨቱ ነው፡፡  

 

አክባሪወ መስፍን አረጋ  

mesfin.arega@gmail.com 

Filed in: Amharic