የአማራ ክልል ለሚሊሺያዎች፣ የጦር መሳሪያ ለታጠቁ ግለሰቦች እና ወጣቶች የክተት ጥሪ አቀረበ…!!!
በአማራ ክልል ቴሌቪዥን ጣቢያ በኩል በ“ሰበር ዜና” የተላለፈው የዛሬው የክተት ጥሪ፤ በአማራ ክልል የሚገኝ “ማናቸውም የጦር መሳሪያ የታጠቀ ሃይል” የሚመለከት ነው ተብሏል።
“በክልላችን የሚገኝ የመንግስትን የጦር መሳሪያ የታጠቀ ሚሊሺያ፣ ሚሊሺያም ያልሆነ በሙሉ፣ በክልላችን ውስጥ የሚገኝ የግል ጦር መሳሪያ የታጠቁ በሙሉ፣ በክልላችን ውስጥ በሁሉም ቀበሌ ውስጥ የሚገኝ አካላዊ ሁኔታው ለግዳጅ፣ ለጦርነት ብቁ የሆነ ወጣት በሙሉ፣ ከነገ ጀምሮ በሁሉም የወረዳ ማዕከል እንዲከት ይህ የክተት ጥሪ ተላልፏል” ብለዋል የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር።
በክልሉ ባሉ የወረዳ ማዕከላት የሚገቡ ታጣቂዎች፣ በግዳጅ የሚሰማሩበት ቀጠና ወይም ግንባር እንደሚነገራቸው አቶ አገኘሁ በዛሬው መግለጫቸው አስታውቀዋል። በአማራ ክልል ያሉ “ተመላሽ የሰራዊት አባላት” እነዚህን ታጣቂዎች የ“መምራት፣ የማታገል እና የማዋጋት” ድርሻን የመወጣት ኃላፊነት የተጣለባቸው መሆኑንም አስገንዘበዋል።
በዚህ ሳምንት የአማራ ክልል ልዩ ኃይልን በአዛዥነት እንዲመሩ የተሾሙት ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ ለክልሉ ቴሌቭዥን ጣቢያ በሰጡት ቃለ መጠይቅ በ“ወልድያም ሆነ በተለያዩ ከተሞች ከበቂ በላይ ኃይል አለ። ይኸ ኃይል ደግሞ መሰማራት በሚገባው፣ ማድረግ በሚገባው ተዘጋጅቶ ነው ያለ” ብለው ነበር። የልዩ ኃይል አዛዡ ሰራዊቱን “በተሻለ ደረጃ ሊመሩ የሚችሉ ጥሪውን ተቀብለው እየገቡ ነው። ወጣቱም ልዩ ኃይሉን ለማጠናከር በከፍተኛ [ደረጃ] ወደ ስልጠና ማዕከሎች ገብቷል” በማለት የክልሉ መንግስት ለሚቆጣጠረው የቴሌቭዥን ጣቢያ አብራርተዋል።
ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider. com/2021/4016