>

“ንጉሥ ሹዋሚዎች” ነን ብዮች ሁሉ ብቅ ብቅ እያሉ ነው (ዓለማየሁ አበበ ሸንቁጥ)

ንጉሥ ሹዋሚዎች” ነን ብዮች ሁሉ ብቅ ብቅ እያሉ ነው 

  ዓለማየሁ አበበ ሸንቁጥ


መቼም የኛ ጉድ ተሰምቶ አያልቅም፡፡ ዛሬ ደግሞ የአገራችን ህልውና አደጋ ላይ በወደቀጭበት ወቅት ፤ የቀድሞ ለኢትዮጵያ ውድቀት ፈርቀዳጅ የሆኑ አካሎችና ድርጅቶች አገሩን ከጥፋት የምናድንበትን መንገድ አለን ብለው መንቀሳቀስ የጀመሩ እንዳሉ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ብቅ ብቅ ማለት ጀምረዋል፡፡

በዛሬው በዚች ለመነጋገሪ እንድትጠቅም ብዬ አዳሬን ጊዜ ወስጄ ስሞነጫጭር አደርኩ፡፡ ጉዳዩ የአገራችን ጉዳይ ያገባናል በሚሉ ቀደም ሲል ግራና ቀኝ እየዘላዘሉ በየፓርቲዎቹ ጣልቃ የሚገቡና አሁን ለኢትዮጵያ የሚበጀውን እናውቃለን የሚሉ ናቸው፡፡ በመሠረቱ የኢሕአፓ ርዝራዦችና ቀደም ሲለ በታሪካችን ህዝቡ የማያስፈልግ መስዋዕትነት እንዲከፍል ያደረጉ ናቸው፡፡ አጅሬ ሕውሀት በመሠሪው መሪዋ አማካይነት ከሌሎች ፓርቲዎች በማስከዳትና ምርከኞችን በመሰባሰብ ለአማሪው ሕዝብ ተጠሪ የሚሆኑ የባንዳ ስብስብ ብአዴን በተባለ የሕውሐት አማርኛ  ተናጋሪ ቡድን መመሥረት ነበር፡፡ እነዚህም ታዘዥ ጭፍራዎች በእንደ ታምራት ላይኔ የመሰሉ ይመራ ነበር፡፡ የኸው ታምራት ላይኔ ከነያሬድ ጥበቡ ጋርና አሁን በአፍላ ብቅ ያለው ቴዎድሮስ ጸጋዬን ጨምሮዋል፡፡ እነዚህ ደግሞ ተቀጽላ ወይም ተወዳዳሪ ብአዴን ፈጥረው ከነደብረጺዎን ጋር በመስማማት ሠላም እናወርዳለን ብለው የተነሳሱ ናቸው፡፡ ዋናው ቁም ነገር ወያኔ ላይ ነፍስ ለመዝራት ነው፡፡ 

 ለመሆኑ ታምራት ለይኔ ማለት ማን ነው፡፡ ለኢትዮጵያስ ተቆርቁዋሪ ሆኖ ለመታየት የትኛው ቁም ነገር ነው በሱ የተፈጸመው፡፡

  ስለታምራት ላይኔ በገሀድ የሚታወቀው ምንድን ነው? 

ታምራት ላይኔ የተባለ ዘረኛው መለስ ዜናዊ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ የሾመው በ1984 ዓ.ም. ጉዞ ወደ አርባ ጉጉ አውራጃ አድርጎ ህዝብን ሰብስቦ የሕዝብን አቤቱታ ሰማቶ ሲበቃ  “እናንተ ትናንት ሽርጣም እየተባላችሁ ስትጨፈጨፉ ስትገዙ የነበራችሁ ዛሬ ጊዜው የእናንተ ነው እንዴት ዝምብላችሁ ታያላችሁ”  ብሎ በአማራው ላይ ጦር እንዲመዘዝ ቅስቅሳ ማካሀየዱ ይታወሳል፡፡ ይህ የዲያብሎስ ቁራጩ አቶ አቻምየለህ አሰፋ የተባሉትን በቁማቸው ቆዳቸው ሲገፈፍ፤ እርጉዞዋ ሴት ሆዱዋ ተቀዶ ውሰጡዋ ያለውን ሽል ከፊትዋ ሲወድቅ ፤ ለዚህ አህዛባዊ ድርጊት መልስ ሲሰጥ “ሀረር ብሎ አማራ አላውቅም አርሲ ብሎ አማራ፤ ባሌ ብሎ አማራ አላውቅም “  ብሎ በመሳለቅ ያፌዘ ምንደኛ ከሀዲ  የአማረም ሕዝብ በኢትዮጵያ ሕዝብ ፊት ጠላት አድርጎ በማቅረብ ጌታውን ለማስደሰት የሄደበት መንገድ መሆኑን  አረጋግጡዋል፡፡

 ከሁሉ የሚገርመው የተከበረው የሕዝብ አይንና ጆሮ የሆነው ኢትዮ 360 የህን ሰው ሕዝብ ፊት አቅርቦ በሙስና መጨማለቁን ያመነ ወራዳና እንደ ሰብአዊ መብት ተሙዋጋጅ አስተያየት ለሕዝብ እንዲያቀርብ ማድረጉ ሕዝብን ማወናበድ መምሰሉን መገንዘብ እንዴት አቃተው ፡፡ እንዴት  እኮ ዘብጥዬ ወርዶ ማቆ የወጣ ሰው መሆኑ ተረሳ፡፡ከዚህም በላይ  የሚያሰዝነው አቶ ሀብታሙ አያሌውና አቶ ኤርሚያስ ለገሠ  የተከበሩ የኢትዮ 360 “አንከር” የሆኑ ጋዜጠኞች ጋብዘው ሕዝብ ፊት ማቅረባቸው በሕዝብ ፊት ታማኝታቸውንና ተቆርቁዋቂነታቸውን ጥያቄ ውስጥ ሊጥለው እንደሚችል መገመት አለመቻላቸውም ይገርማል፡፡

  ከዚህ ዘረኛና አጭበርባሪ ሰው ጋር አብረው መቀመጣቸው ጸያፍነቱን ለመገመት አለመቻላቸው አሁንም እጅግ ይገርማል፡፡

  ስለዚህ እንደዚህ ያለ ሰው ነው ዛሬ ዓይኑን በጨው አጥቦ    “ንጉሥ ሹዋሚ”  ልሁን የሚለው፡፡

    መንግሥት እርዳታ ለሠላማዊው የትግራይ ሕዝብ  እንዲደርሰው ከሱዳን መቀሌ የሠላም ቀጠና እንዲፈጠር መንግሥትን የሚማጸነው፡፡ ማነው ጦርነቱን ያወጀው? ማነው የራሱን ሕዝብ በግፍ የሚጨፈጭፈው? መንግሥት ጦሩን ያወጣው ሕዝቡ ከችግር እንገላገል ብሎ አይደለም እንዴ? ጦርነት አላቆምም ያልው እኮ ወያኔ ነው፡፡ ለምን እነሱኑ ጌቶቹን አይጠይቃቸውም፡፡   

 የሚገርመው ኢትዮጵያ በፌዝ የታጠረች አገረ መሆኑዋን ስንገነዘብ ምን ያሕል ልባችን ይቆሰል ? ይብላኝ መድረሻችን !!  እረ እባካችሁ ሚዛን በሚደፋ ጉዳዮች ላይ እንጠመድ፡፡

Filed in: Amharic