>
5:13 pm - Tuesday April 18, 6311

ንጉሱ ራቁታቸውን ናቸው...!!!! (መርእድ እስጢፋኖስ)

ንጉሱ ራቁታቸውን ናቸው…!!!!

መርእድ እስጢፋኖስ

ሀንስ ክርስቲያን አንደረስን 1837 ለልጆች የተፃፈ የተረት መፅሀፍ ነው።በ100 ቋንቋዎች ተተርጉሟል።እስፓንሾችም የኛ ነው ይላሉ ።ህንዶችም፡አረቦች የየራሳቸው ቨርዥን አሏቸው።ግን የምወደው ፈረንሳዊው የፓርዚያኑ ዥን ማኑኤል የፃፈውን ነው።1282-1348 ይኖር የነበረው “የቨሊናው ንጉስ ታሪክ ነው”።
ደልቃቃ ነው።ህዝቡ በሚከፍለው የታክስ ገንዘብ ኑሮው አጅግ ሲበዛ ወጣ ያለ ነው።ልብስ አብዝቶ መቀያየር ይወድ ነበር።የወርቅ እና የአልማዝ ልቡጥ ካፖርቶቹን ደርቦ የወርቅ ጫማውን ተጫምቶ አጃቢዎቹን ግራ እና ቀኝ አሰልፎ ሲያበቃ በትንሿ ከተማዋ መሀል ያልፋል።ማለዳ ቀትር ማምሻ ሁሌም እንደዚሁ።ከቤተ መንግስቱ በወጣ ቁጥር ልብሱን ለማሳየት ነው።
ድሀው የከተማዋ ነዋሪ በመንገድ ላይ ያለ እጅ ነስቶ ንጉሳቸው እንደሚያምር ይናገራሉ አለባበሱንም ያደንቃሉ።በቤታቸው ያሉም በመስኮት ድምፃቸውን ከፍ አርገው ያሰማሉ”ታምራለህ ይሉታል”።እነዚህ ደሀ ረሀብተኛ ህዝቦች።
ይሄን ሁኔታውን የተመለከቱ ሁለት የልብስ ሰፊ ባለሞያዎች ወደ ንጉሱ ቀረቡና “አንተ ታላቅ ንጉስ እኛ ላንተ ብቻ የሚሆን ልብስ ልንሰራልህ እንወዳለን አሉ።ልብሱ በደንቆሮዎች እና እውቀት በሌላቸው ሰዎች አይታይም።የመንፈሳዊ አይን በሌላቸው ሰዎች አይታይም።invisible ነው ።ለአንተ ብቻ እንሰራዋለን አሉት” ንጉሱም በጣም ተመሰጠ።ወዲያው ቀጠራቸው።
የልብስ ስራውን ጀመሩ።ወርቅም አልማዝም ጠየቁ ለስራው ጣቃዎችም እንዲሁ።ሁሉም ተሰጣቸው።
ማለዳ ተነስቶ ወደሰፊዎቹ ይገባና ይሄ ለጠቢባን እና ላዋቂዎች እንዲሁም በእግዚአብሄር ለተመረጡ ብቻ የሚታየውን ልብሱን ይጎበኛል።
በቃ አድንቆ እንዲፋጥኑት ነግሮ ይወጣል።ይሄን ልብስ ለብሶ በከተማዋ መሀል ማለፍ ጓጉቷል።ምንም ይልበስ ምን “የከተማው ድሀ ህዝብ ያምርብሀል ይሉታል የኛን ንጉስ የመሰለ ለባሽ ከየት ይገኛል ይሉታል።” እናም ተምረኛውን ልብስ ሊሳያቸው ቸኩሏል።
አሁን ልብሱ እንዳለቀ ተነገረው።ወደሰፊዎቹ ሄደ ።ሰአታት ወስደው የለበሰውን ልብስ አውልቀው ሲበቁ የማይታየውን invisible ልብስ አለበሱት።በቃ አስተያየት አልሰጠም ምክንያቱም መንፈሳዊ አይን የለውም እንዳይባል አዋቂ የተማረ አይደለም እንዳይባል።ልብሱን ለብሶ እንዳበቃ።ወደ አጃቢዎቹ ሄደ።
ገና እንዳዩት መሬት ወድቀው አዲሱ ልብስ እንዴት ያምራል ግርማሞገስህን ከፍ አርጎታል የዛሬውን አይነት ተለብሶ አይታውቅም አሉት።ይህን ካላሉ መንፈሳዊ አይን የላቸውም ጠቢብና የተማሩ አይደሉም እናም ስራቸውንም ያጣሉ።ሊባረሩ ይችላሉ።
በሉ በከተማው መሀል ልለፍ ወደ ባቡር ጣቢይውም ልድረስ ተነሱ አለ።አጀቡት እንደተለመደው ግራና ቀኝ ሆነው።ንጉሱ የውርቅ ጫማውን ብቻነው ያደረገው።
ጎዳናው ላይ ያለው ህዝብ ንጉሱን እያየ እንዴት እንደሚምር ግርማ ሞገሱ በዚህ እለት የብዛ እንደሆነ እየተናገሩ በአድናቆት ሰገዱ።በቤታቸውም ያሉ በመስኮት ብቅ እያሉ ታላቁ ንጉስ ልብስና መጎንናፀፊህ እጅግ ያምራል አሉ።ንግሱ ሀሴት አደረገ።የማይታየውን ልብስ የሱ ህዝቦች ማየታቸው አስደሰተው።ህዝቦቼ ጠቢባን ናቸው አለ።መንፈሳዊ አይን አላቸው አለ።
ግን ደስታው አልቆየም
ከአባቱጋር የነበረ ሕፃን አባቱ እየሰገደ ንጉሱን ታምራልህ ግርማሞገስህ ጨምሯል እያለ እንደብዙዎች ሁሉ ሲወራ ህፃኑ ልጅ ግን”ልብስ አልበሰም ራቆቱን ነው” ብሎ ተናገረ።ንጉሱም ይህን ነገር ሰማ ወደልጁም ቀረበ “ራቆቱን መሆኑን ነገረው”
ከዛ ሁሉም እየቀባበሉ “ንጉሱ ራቆቱን ነው ማለት ጀመሩ” ንጉሱም እውነት የሚነግረው አጃቢም ይሁን ቤተሰብ ወይም ህዝብ እንደሌለው አወቀ እድሜ ለህፃኑ”
በፖለቲካው አለም ታዲያ “ንጉሱ ልብስ እንዳለበሰ እና ራቆቱን እንድሆነ አንድሰው ሊነግረው ይገባል ይባላል”…በጣም ሲበዛ
በህዝቡ የሚፈራ መንግስት መሆን።አንባገነን መሆን።ማንነትን በትክክል እንዳያውቅ ያደርጋል።ወያኔም የገጠሟት የነበረው ችግር ይኽው ነው።ራቆታቸውን እንደሆኑ የሚነግራቸው ማጣት።
ህዝቡ እንዳይነግራቸው ፈራ።እነሱ ያሉትን እያለ ይኽው እስከዛሬ ዘለቀ።እናም መጨረሻ ልብስ እንደሌላቸው ተረዱ። ይህ እንግዲህ የውሽታም መንግስት እና የሚፈራ ህዝብ ታሪክ ነው። ወደኛ አገር ስንመለስ ደግሞ የታሪኩን እውነትነት ፍንትው አርጉ ያሳያል።
ዛሬ ሁለት አመት ተቃዋሚዎችን አስረን ዲሞክራሲ ልንገነባ አንችልም ያሉን የተከበሩ ጠ/ሚ አብይ አህመድ ዛሬ በአፍሪካ ግልገል አምባገነን በመሆን ሊመዘገቡ በደጅ ቆመው እያንኳኩ ነው።17 ጋዜጠኛ በማሰር ጓደኛቸው አል ሲሲን እየመሩ ነው።
ተቃዋሚዎችን አስረው ምርጫም ሊያኪሂዱ ነው ።አሁን ችግሩ ወዲህ ነው።ዶ/ር አብይ ያውቁታል ወይ? የሳቸው አለም በተደጋጋሚ እንደፃፍኩት ከኛ ከምናውቀው ይለያል።እሳቸው የሚሉን በኢኮኖሚም በልፅገናል ነው።እኛ የምንለው በድህነት በልፅግናል ነው።እሳቸው የሚሉት ከዘረኝነት ወጥተን  በልፅገናል ነው ።እኛ ደግሞ የምንለው በዘረኝነት በልፅገናል ነው።እሳቸው የሚሉት ከተረኝነት ወጥተን በልፅገናል ነው ።እኛ የምንለው በተረኝነት ፖለቲካ በልፅገናል ነው።  እሳቸው የሚሉት አገሪቱ ሰላም የሰፈነባት ሆናለች ነው።እኛ የምንለው ደግም አገሪቱ በየቀኑ አነሰ ቢባል 20 አማራ የሚታረድባት ለዛውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀዘን መግለጫ እንኳ የማይሰጥባት አገር ሆናለች ነው። ይህን እና ያንን እየመዝውዝን መቀጠል ይቻላል።
ጠቅላያችን አንዳች ጋርዶባቸው የኛን አለም ሊያዩት እንዳይችሉ ሆነው ሰማይ ላይ ተንጠልጥለዋል።” እኛም ፈቃዳቸው በሰማይ እንደሆነ እንዲሁም በምድር አንዲሆን እየፀለይን ነው” ።
out of touch የሆኑት መሪያችን ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በመሆን የፈጠሩት የህልም አለም አገሪቱን ይዞ እንደሚጠፋ የታወቀ ነበር።ዛሬ ዛሬ ግን እሳቸውንም ይዞ ሊጠፋ እንደሚችል በየቀኑምልክት አየታ የነው ። በኦሮምያ 20 በላይ  የአማራ ተወላጆች በየቀኑ በሚባል ደረጃ በብሄራቸው እና በሀይምስኖታቸው ታደነው እየታረዱ ባሉበት ባሁኑ ወቅት አንድም አለም አቀፍ ድርጅት አንድም መንግስት አላወገዘም።በወያኔ እብሪት ለተጀመረ ጦርነት ግን አለም ከበሮ እየደሰቀ ነው።ጣቱንም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ቀስረዋል።  የእሳቸውንም መጨረሻውን አላሁ አለም ።መድሀኒያለም ነው የሚያውቀው።
አገራችን በሁለት የውጭ መንግስታት ተወራለች።ሶዎስተኛው በመንገድ ላይ ነው።በሁለት ዘረኞች ጠባብ ብሄረተኞች በሆኑት በወያኔና ኦነግ በሀገር ውስጥ ትናጣለች።ኢኮኖሚው ገደል ግርብቷል።ዲፕሎሚሲያዊ አቅማችን ገደል ገብቷል።አንድነታችን ገደል ገብቷል።የቀረው እንግዲህ banana republic መባል ነው።
ይህ ሁሉ ጥፋት የመጣው እንግዲህ ጠ/ሚ አብይ ከእውነቱ መራቃቸው ፥እውነቱን የሚነግራቸው ማጣታቸው ነው። አና አምባገነን በመሆናቸው ነው።
በህዝብ ላይ አምባገነን የሆኑ መንግስታት አንድ ቀን ራቆታቸውን መሆናቸውን ያውቃሉ።አንድ ህፃን እስኪገኛቸው ድረስ ብቻ ነው።እንሆ ተጽፎአል “መንግስተሰማያት ህፃናትን ትመስላልች አይደል ያለው ቃሉ። አዎ ህፃናትን አትከልክሎቸው” እና ውሽታም መንግስቶቻችን እና ውሽታም ህዝቦቿ……ቀጥለናል።……..እግዜር ያስረዳን!አሜን!

Filed in: Amharic