>

"ኢህአዲግ፣ አጋር፣ ግንባር ፣ ላኪ ተላኪ ሁሉም የኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው የምንለውም በምክንያት ነው....!!!" (ጎዳና ያእቆብ)

“ኢህአዲግ፣ አጋር፣ ግንባር ፣ ላኪ ተላኪ ሁሉም የኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው የምንለውም በምክንያት ነው….!!!”

ጎዳና ያእቆብ

*… ኦነግና ሻቢያም የታላቋ የኢትዮጵያ ወዳጅ ለመሆን ተፈጥሮአቸው አይፈቅድላቸውም! 
 *… <<እኛ ከእናንተ ጋር ልንሰራ የምንችለው ይሄ ኢትዮጵያ የምትባለዋ ሀገር ተፈጥሬበታለሁ የምትለው [በሰሜን ኢትዮጵያና በኦርቶዶክስ ተዋህዶ የሚነገርላት] አፈ ታሪክን የምታጠፉና አዲስ ዲሞግራፊ መፍጠር የምትችሉ ከሆነ ነው>> ሲሉ እነ የማነ ገብረአብ በኤርትራ ከትመው ለነበሩ ለኦሮሞ ብሔርተኞች (የአብይ አህመድ አማካሪና አሁን የሳውዲ አረቢያ አምባሳደር ሆኖ በአብይ አህመድ የተሾመውን ሌንጮ ባቲ የስብሰባው ታዳሚ እደነበር ጋዜጠኛ ሰናይ ገብረመድህን ምስክርነቱን ይሰጣል::
*….. እነ አብይ አህመድ ታዬ ደንደአ “ቀድማ የተሰራችው ኢትዮጵያ እኛን ስለማትመስል አንድ ሁለት ብለን ነቅሰን አውጥተን እንቀይረዋለን ” ያለው ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ከኤርትራ ጋር ያላቸው ያልተቀደሰ ጋብቻ ከየት የመነጨ እንደሆነ ማወቅ አያዳግትም::
በምን መርህ ላይ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት እንደተመረኮዘ ሊነግሩን የማይፈቅዱታ የግለሰቦች ግንኙነት ነው ለሚል ድምዳሜ ያደረሰው ይኼው ነው:: ኤርትራ ውስጥ አፍ መፍቻ ቃል <<አድጊ አማራ>> የሚል ሕዝብን እንደሕዝብ የሚያዋርድ እንዳልሆነ ሁሉ ዛሬ ህዋሃት አጣልቶን አቃቅሮን እያሉ የጦስ ዶሮ ማሰሳቸውን ቀጥለዋል::
በኤርትራዊያን እንደተነገረኝ ከሆነ ከትግራይ እና ከአፋር ውጪ ያለው የኢትዮጵያን ሕዝብ እንዳለ አማራ በማለት ነው የሚጠሩት የሚል ነው::
የሆነ ሆኖ <<ታላቋ ኢትዮጵያ>> ተረት ተረት ነች የሚል የረዥም ጊዜ እምነት የህዋሃት ብቻ ሳይሆን የሻቢያም እንደነበረ ነው:: የኦሮሞ ብሄርተኞችም ኢትዮጵያን ለማሳነስ የሚያደርጉት ጥረት ባህል ከሆነ ሰንብቷል::
ኢህአዲግ እንደኢህአዲግ አጋር ግንባር ላኪ ትላኪ ሳይባል ሁሉም የኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው የምንለውም በምክንያት ነው::
ኦነግና ሻቢያም የታላቋ የኢትዮጵያ ወዳጅ ለመሆን ተፈጥሮአቸው አይፈቅድላቸውም::
ከአንድ ጨርቅ የተቀደዱና ተጣብቀው የተወለዱ ናችው:: ያው ናቸው:: አንድ ናቸው::
ልዩነት የሚመስል ነገር ካለ የአካሄድ እንጂ የአስተሳሰብ አይደልም:: አብቹ በለው ደፂ:ደመቀ በለው ሀይለማሪያም: ጌች በለው ኢሱ ሁሉም ሀገር ጠል ታሪክ ጠል ናቸው::
ከነሱ መሀል መምረጥ ከዝንጀሮ ቆንጆ መምረጥ ነው:: የዝንጀሮ ቆንጆ ደግሞ የለውም::
Filed in: Amharic