>

አቶ ታዲዮስ ታንቱ ያሉበት እስር ቤት ታውቋል.. !!! (ወረታው ዋሴ)

አቶ ታዲዮስ ታንቱ ያሉበት እስር ቤት ታውቋል.. !!!

ወረታው ዋሴ

*…  በፖሊስ መምሪያው ምንም ዓይነት ምግብ የማይቀርብላቸው ሲሆን በራሳቸው ገንዘብ በፖሊሶች መልካም ትብብር እየገዙላቸው ህይወታቸውን እስካሁን አቆይተዋል። እጅግም ተጎሳቁለዋል።
ከአንድ ወር በፊት ከቤታቸው በሌሊት ተወስደውና አድራሻቸው ጠፍቶ የቆዬው ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ በአሁኑ ሰዓት ገላን ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ታስረው የሚገኙ ሲሆን እስካሁኗ ስዓት ድረስ ፍርድ ቤት አልቀረቡም። ከተያዙበት ዕለት ጀምረው ወደ አዋሽ መልካ ተወስደው ለ22 ቀናት በጨለማ ቤት ታሰረው በቀን አንድ ጊዜ ብቻ ምግብ እየቀረበላቸው ከቆዩ በኋላ አሁን ወደሚገኙበት ጣቢያ ተዛውረው ታስረው ይገኛሉ።
በፖሊስ መምሪያው ምንም ዓይነት ምግብ የማይቀርብላቸው ሲሆን በራሳቸው ገንዘብ በፖሊሶች መልካም ትብብር እየገዙላቸው ህይወታቸውን እስካሁን አቆይተዋል። እጅግም ተጎሳቁለዋል።
አሁን በአካልን ነፃ ማውጣት ህግ ከእስር እንዲለቀቁ ሁላችንም የምንችለውን በማድረግ ልንረዳቸው ይገባል።
የደረሰባቸውን እንግልት ወደፊት ከእራሳቸው አንደበት እንሰማዋለን።
በስማቸው  ተከፍቶ ስለተሰበሰበው ጎፈንድ ጉዳይ እመለስበታለው
Filed in: Amharic