>
5:33 pm - Sunday December 5, 7193

‹‹ የውጭ ኃይሎች የተቀናጀ ዘመቻ የአፍሪካ ቀንድ አገራት ግንኙነትን እንደስጋት በመመልከታቸው ነው››  (አቶ ታዬ ቦጋለ )

‹‹ የውጭ ኃይሎች የተቀናጀ ዘመቻ የአፍሪካ ቀንድ አገራት ግንኙነትን እንደስጋት በመመልከታቸው ነው›› 
-አቶ ታዬ ቦጋለ የታሪክ መምህርና የማህበረሰብ አንቂ
(ኢ ፕ ድ) 

የውጭ ኃይሎች በኢትዮጵያ ላይ የተቀናጀ ዘመቻ የከፈቱበት ዋና ምክንያት በአፍሪካ ቀንድ አገራት መካከል የታየው መልካም ግንኙነት ስጋት ስለሆነባቸው እንደሆነ የታሪክ መምህርና የማህበረሰብ አንቂ አቶ ታዬ ቦጋለ ገለጹ።
አቶ ታዬ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የምትከተለው የለውጥ እንቅስቃሴ ምስራቅ አፍሪካን የማገናኘት አቅም ስላለውና በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ባሉ አገራት በተለይ ደግሞ በኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረው መልካም ግንኙነት በአንዳንድ የውጭ ኃይሎች ዘንድ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።
የምስራቅ አፍሪካን የማገናኘት አቅም ያለው የኢትዮጵያ የለውጥ እንቅስቃሴና በአገራቱ የታየው መልካም ግንኙነት በአንዳንድ የውጭ ኃይሎች ስጋት በመፍጠሩ የተቀናጀ ዘመቻ በኢትዮጵያ ላይ እንዲከፍቱ ምክንያት ሆኗል ብለዋል።
የውጭ ኃይሎች እንዲህ አይነቱን አፍሪካዊ የኢኮኖሚ ትስስር ወደ ፖለቲካዊ ትስስር ያመራል ብለው ስለሚያስቡ በስጋት ይመለከቱታል ያሉት መምህሩ፤ ኢትዮጵያ እየተከተለች ያለው የልማት እንቅስቃሴ ለእነዚህ ኃይሎች ከፍተኛ ስጋት እየሆነ መምጣቱን አስታውቀዋል።
እነዚህ የውጭ ኃይሎች የእነሱን ጥቅም የሚያስጠብቅ ደካማ መንግሥት እንጂ የራሱን ፖሊሲ የሚከተል ጠንካራ መንግሥት በየትኛውም አገር እንዲኖር አይፈልጉም።አሁን ኢትዮጵያ ላይ የከፈቱት
 የተቀናጀ ዘመቻም የዚሁ አካል ነው ፤ ዓላማቸውም ኢትዮጵያን ማጥቃት ነው ብለዋል።
Filed in: Amharic