>
5:26 pm - Sunday September 15, 4143

የኢትዮጵያን እዳ የተሸከመችው የወልዲያ ከተማ .. !!! (አሳዬ ደርቤ)

የኢትዮጵያን እዳ የተሸከመችው የወልዲያ ከተማ .. !!!

አሳዬ ደርቤ

ከአሸባሪው መንጋ ጋር የሚደረገው ጦርነት እያንዳንዱን ወጣት ብርቱ ሠራዊት አድርጎታል፡፡ ከዚህ ሠራዊት መሃከልም የማረጋጋትና የማዋጋት መክሊት የተቸረው ሙሐመድ ያሲን የተባለ የጦር ጠበብት መፍለቅ ችሏል፡፡
 በሌሎች ግንባሮች ግንባር ግንባሩን ሲባል የከረመው አሸባሪ ደግሞ ወልዲያ ከተማን የትኩረት ማዕከሉ አድርጓታል። አማራ ሕዝብ ላይ አለኝ የሚለውን ሒሳብ ለማወራረድ ብሎም በጥጋብ ስሜት ወደ ጦርነት ገብቶ በርሐብ የሚቆሻመድ ጦሩን ለመመገብ ከዚህ በፊት ቂም የቋጠረባትን የወልዲያ ከተማን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ትግል በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
የጁዎች ግን ክንዳቸውን ሳይንተራሱ ከተማቸውን የሚያስቀምሱ አልሆኑም፡፡ ከሲኖትራክ እየተራገፈ ልጋጉን ለሚያዝረበርበው የተራበ ጅብ አምቦ ላይ ያጋጠመውን አይነት ትግል አቀጣጥለው ጠበቁት እንጂ ወልዲያ እንደ አጣዬ እንዲትሆን አልፈቀዱም፡፡
.
በመሆኑም የቆቦን መያዝ በሰሙበት ቅጽበት ወደ ደሴ የሸሹ አንዳንድ አመራሮቻቸውን ተከትለው በመሸሽ ፈንታ የሙሐመድ ያሲንን ጽናት በመጋራት ከመከላከያ ሠራዊቱና ከአማራ ልዩሃይል ጎን ተሰልፈው በየሰዓቱ የሚራገፈውን ጦር ሲረፈርፉት ሰንብተዋል፡፡
የሚልኩት የሽብር መንጋም ወልዲያን ቆረጣጥሞ በመብላት ፈንታ በእርሳስ እየተበላ የቀረባቸው እነ አቶ ጌታቸው ረዳ አልደፈር ያለቻቸው ከተማ ተደናግጣ እንዲትሸሽ ለማድረግና በየቦታው ያጋጠማቸው ሽንፈት ያሳደረባቸውን ብስጭት ለማስታገስ አስበው ትናንት ማታም ሆነ ዛሬ ወደ ንጹሐን ጎጆ ከባድ መሳሪያ በመተኮስ ላይ ይገኛሉ፡፡
የወልዲያ ወጣቶችና የጦር መሪያቸው አቶ ሙሐመድ ያሲን ግን ይህ የከባድ መሳሪያ ተኩስ ህውሓት ያጋጠመውን ከባድ ሽንፈት ከመግለጽ ባለፈ ለሽሽት የሚያነሳሳቸው አልሆነም፡፡ በየሠዓቱ የሚዘረገፈው የአሸባሪው መንጋ የቁጥሩ ብዛት ካላቸው ጥይት በላይ መሆኑን ገልጸው ተጨማሪ ሃይል ከመጠየቅ ውጭ አላፈገፈጉም፡፡
ይሄም ጥያቄያቸው ተገቢ መልስ አግኝቶ በዙሪያቸው የሚያንዣብበውን የጅብ መንጋ የሚደመሰስ ጦር ማግኘት ባይችሉም ልክ እንደ ሰሞኑ ሁሉ ዛሬም እስከዚች ሰዓት ድረስ የከበባቸውን ጅብ እንዲህ እያሉ ይረፈርፉት ይዘዋል፡፡
ዞር በል
የወልዲያን ወጣት- ላትበላው እንደ እህል
ቀየህ ላይ ጨምተህ- ስንዴህን ተቀበል፡፡
ወግድ…
እዳ ተሸክመህ- ለእኛ የሚወራረድ
ባልሰጠኸን ዱቤ – ወልዲያን ላታነድ
ከወንዶች ምድጃ- ነፍስህን አትማግድ
ክላ…
በየጁዎች እርሳስ- ከምታልቅ በጅምላ
ዝርፊያህን ተውና- እርዳታህን ብላ፡፡
Filed in: Amharic