>

ጦማር➜ ከጦር ግንባር...!!! (አሳዬ ደርቤ)

ጦማር➜ ከጦር ግንባር…!!!

አሳዬ ደርቤ

ወልቃይትና ሑመራ ግንባር፡- 
➜ከአሸባሪው ሃይል ባለፈ የጎረቤት አገራትና የምዕራቡ መንግሥታት ዋነኛ ትኩረት ያረፈበት
➜የሱዳንን እና የግብጽን ዘመናዊ ጦር መሳሪያ የታጠቀ ብሎም ለስምንት ወራት ሲሰለጥን የቆዬ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአሸባሪው ጦር የተሰለፈበት
➜የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩሃይልና ፋኖ በሚገርም መናበብ ከጎረቤት ክልልና ከጎረቤት አገር እየተቀፈቀፈ የሚተምመውን አገር አፍራሽ ሃይል ድባቅ እየመቱ ከፍተኛ ድል ያስመዘገቡበት
➜ተላላኪው ትሕነግ ብቻ ሳይሆን ላኪዎቹም ጭምር የኢትዮጵያን ጥንካሬ የተረዱበት
➜ከፉከራና ከፕሮፖጋንዳ የጸዳ ጠንካራ ትግል የሚካሄድበት
➜ለማንነቱ የሚጋደል ሕዝብ የተሰለፈበት
የአፋር ግንባር፡- 
➾በሱዳን ኮሪደር ተስፋ የቆረጠው ሽብርተኛ የጂቡቲን መስመር ለመዝጋት ከፍተኛ ጦር ያዘመተበት
➾ከመከላከያ ሠራዊቱ ጋር የተቀናጀው የአፋር ታጣቂ ክልሉን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን የማያስደፍር መሆኑን ያሳየበት
➾የአሸባሪው ወያኔ ጦር ‹‹ወያኔ›› የተባለውን አረም ተደግፎ ያሸለበበት
➾በኢትዮጵያ አሞራዎች የህውሓት ከባድ መሣሪያዎችና ከባድ መኪኖች እንደ ደመራ የነደዱበት
➾ባለከዘራው ኮሎኔል ለድል የተፈጠረ አዋጊ መሆኑን የገለጸበት
➾በአፋር ሕዝብ የደረሰበት ጉዳት ለብስጭት የዳረገው አረመኔ ሃይል 240 ሕጻናትና አዛውንት አርዶ አረማዊ መንፈሱን ያረካበት
የሰቆጣ ግንባር፡-
➻የሰቆጣ ወጣት እራሱን አደራጅቶ ተደራጅቶ የመጣውን አሸባሪ በታትኖ የቀበረበት
➻የዋግሹም ልጆች ከአባቶቻቸው የወረሱትን የአገር አለኝታነት በተግባር የገለጹበት
➻እልፍ አእላፍ ጀብዱ ተፈጽሞ በመረጃ እጥረት ብዙ ያልተነገረለት
➻ሰቆጣን ለመቆጣጠር አስቦ የዘመተው አሸባሪ ትርፍራፊ ጦሩን ይዞ አበርገሌ ላይ እንባውን ለማዝራት የተገደደበት
➻‹‹የሰቆጣን ዳገት- የወረረው ሠንጋ››
በዋግሹሞች እርሳስ- አለቀ በመንጋ›› የተባለበት
ጋይንት ግንባር፡- 
➛‹‹ስማዳ ስማዳ ስማዳ ገባች›› የሚል ዘፈን እያንጎራጎረ ቤርሙዳ መግባቱን የተረዳው አሸባሪ ‹‹እንደ ሱዳን አምባሳደር ሾልኬ እወጣ ዘንድ አንድ እድል ስጡኝ›› ብሎ የተማጸነበት
➻የትሕነግ ወራሪ ‹‹አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ›› የሚል እርግማኑን የተጎነጨበት
➛ንፋስ መውጫ የገቡ ጥቂት አሸባሪዎች ባንክ ቤት በራፍ ላይ ቆመው ቀብራቸው ላይ የሚለጠፍ አንድ ፎቶ ከተነሱ በኋላ ወደ መቃብራቸው የተሸኙበት
ሰሜን ወሎ ግንባር፡-
➜ባልተገመተ ቁማር ራያን እና ኮረምን ለቅቆ የወጣው ጦር ሕዝቡ ተደራጅቶ እራሱን እንዳይከላከል ከባድ አሻራ ያሳረፈበት
➜ጠባቂ ወታደሩን ብቻ ሳይሆን የሚያደራጅ አመራሩን ያጣ ሕዝብ ለከፍተኛ መፈናቀልና እክል የተዳረገበት
➜ይሄንንም ምቹ ሁኔታ የተረዱት የአሸባሪው መሪዎች ሕዝባዊ ማዕበል በማስነሳት የተወሰኑ ወረዳዎችን ከተቆጣጠሩ በኋላ ወልዲያ ላይ ሲደርሱ በየጁዎች እጅ የእጃቸውን ያገኙበት
➜በሐሺሽ የተበረገደ የምግብ ፍላጎቱን ወልዲያን በመብላት ማስታገስ የተመኘው የጅብ መንጋ በመሐመድ ያሲን ጦር እንደ አንበጣ የረገፈበት
➜የተናጠል ተኩስ አቁሙ ከተነሳ ጊዜ አንስቶ መከላከያ በወሰደው እርምጃ በወልዲያም ሆነ በመርሳ የአሸባሪው ጦር ከባድ ቅጣት ያስተናገደበት
➜የፌደራሉና የክልሉ መንግሥት አቋምና አቅም ወደፊት የሚፈተሽበት…
ድል ለኢትዮጵያ!
Filed in: Amharic