>

ከአብይ ጎን አልቆምኩም አልቆምም...!!!  ( ጎዳና ያእቆብ)

ከአብይ ጎን አልቆምኩም አልቆምም…!!!

         ጎዳና ያእቆብ

 

*….  ከኦነግ ጋር ህዋሃት ተጣመረ ሲሉም መች ተፋተው የሚያውቁትን ነው ነው ያልኩት:: አብይን እና አስተሳሰቡት በተመለከተ ከህዋሃት ጋር  አንድ ፀቡ  አላቸው እሱም የበኩርና ብቻ ነው:: ከስልጣን ውጪ ባሉት ነገሮች ሁሉ ከህዋሃት ጋር የሚያስማማ እንጂ የሚያጣላ ነገርየላቸውም:: እንደውም ከነ ድክመቱ መስማማት የሚቸግረው ከብአዴን ጋር ነው የሚሆነው…!!!
 
በኔ እምነት የነሱ እንዳትፈርስ የሚፈልጓት ኢትዮጵያ አብይ አህመድ እና ስልጣኑ ናት:: እኔ ይቅርታ እድርጉልኝና ማንም በጅምላ የተቀበሩትን: እርጉዝ ሴቶችን ማህፀን ቀርደደው ልጅ እውጥተው በእጃቸው የሰጧቸውን: ልጅ አገረዶች ማህፀን ውስጥ ባእድ ነገር የጨመሩትን: የአማራ ደም በመሬታችን ላይ አይፈስም ብለው በሽንት ቤት ውስጥ አርደው ያፈሰሱትን: አስክሬን የጎተቱትን ያቃጠሉትን የቆራረጡትን ያፈናቀሉትን አጣዬን ያቃጠሉት መላው የአማራ ማህበረሰብ ሊረሳው ይችላል እኔ ግን መቼም አልረሳውም:: ለሚቀጥሉት 300 አመታት በህይወት ብኖር አልረሳውም::
ሰብአዊነቴ  ግፍና ሰቆቃውን ልረሳን  ከአብይ አህመድ ጋር ልሰለፍ እንድል አይፈቅድልኝም:: መቼም አላደርገውም:: እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ  ዘፈን ኣውጥቶ አወድሶ ሙሴ ብሎ ዙፋን ሰርቶና ካባ አልብሶ ሺ አመት ንገስ ያለውን የአማራ ማህበረሰብ ሰበርናቸው አደቀቅናቸው ብለው የተፈፀመው ግፍን መቼም ይቅር የምለው አይደለም::
እንደ አንድ ኦሮሞ ደግሞ እነዚህ ሁሉ አሰቃቂ ግፎች የተሰሩት በስሜ  አንተን ለመጥቀም ነው የሚል ለትውልድ የሚሻገር እና የተገኘሁበትን ደግ ማህበረሰብ ላይ cultural genocide የፈፀሙበት ስለሆነ መቼም ልረሳው ይቅር ልለው እናም ከአብይ አህመድና ከሽመልስ አብዲሳ ጎን ልቆም ልሰለፍ አልችልም:: አላደርገውም::
እንተወው::  ጊዜው አይደለም:: የአስተዳደር ችግር ነው:: ለሚሉኝ ወይ የወንጀሉን ልክ አላወቁትም ካልሆነም ደግሞ ያልተነካ ግልግል ያውቃል ማለት ነውና የተሰራው አሰቃቂ ግፍ ማህበራዊ ፓለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የስነ ልቦና ቀውስ የፈጠረ መሆኑን ስላልተረዱት ነው:: ቁስል እንዳለ ቢያውቁም የቁስሉን ጥልቀት ስላላወቁት ነው ባይ ነኝ:: አለመረዳት ነው:: ወይም የሚዘውራቸው ጥላቻ ነው ማለት ነው::
የኔ ጉዳይ ከፍትህ ነው:: ጉዳዩ ከእውነት ነው::
ወንጀልን እና ግፍን ለወደድኩት የምቀንስ የጠላሁት/የፈራሁት ላይ ደግሞ የምወዝፍ አይደለሁም:: ግብዝነት ከምሸሸው በሽታ አንዱ ነው:: ኢህአዴግ ብልፅግና [ህዋሃት የተቀነሰበት ኢህአዴግ] ሁሉም እኩል ነቀርሳዎች ናቸው::
አንዱን ጉዳት የሌለው ወይም ቅንነት የጎደለው ኪንታሮት ሌላውን ነቀርሳ/ካንሰር አድርጎ የመሳል ቅጥፈት ውስጥ ለሴኮንዶች ሽርፍራፊ አልተባበርም:: እፀየፈዋለሁና:: በቅንነቱና በሰው አማኝነቱ አሰቃቂ ግፍ ከአብይ አህመድ ጎን እንዳልቆም ያግደኛል:: በደጉና በየዋሁ በኦሮሞ ስም የማይነገር ግፍና ሰቆቃ ከፈፀሙት አብይ አህመዶችና ሽመልስ አብዲሳዎች ጎን መቼም አልቆምም:: እኔ ኢትዮጵያ በጦነትነት የሚፈታ ችግር የላትም የሚል ፅኑ እምነት አለኝ:: ሰላም ውይይት እና ድርድር አስፈላጊ ነው ብዬ አምናለሁ:: አለዚህ ተወያዩ ተደረደሩ እላለሁ::
ሰላም አማራጭ አይደለም ድርድር አያስፈልግም ጦርነት ብቻ ነው መንገዳችን ለምትሉ በጦርነት የሀገር ህልውናን የማስጠበቅ አቅም አብይ አህመድ እንደሌለው የምናውቀው ትናንት መቀሌን ተቆጣጥሮ ዱቄት ነው ያለው ሀይል መቀሌን አስመልሶ በአማራ ክልልና በአፋር ላይ ጦርነት ላይ ነውና ግፋ በለው ለሚሉትም ቢሆን በጦርነት የማሸነፍ አቅም እንደሌለው አይተናል:: የተኩስ አቁም የሚል ቀልዱን ትተን ሀቁን ብናየው ትእግስት ሳይሆን አቅም ማነስ ነው ዛሬ ህዋሃትን ወሎ ያደረሰው::
ስለዚህ ውይይት ድርድር::
ህዋሃትና ኦነግ 4 ኪሎ የሚገባው አሁን በምንሄድበት መንገድ መቀጠል ነው:: የኔ የሰላም ጥሪ አልሰራም አይሰራምም የሚል መከራከሪያ ለምታቀርቡ ጦርነቱ እስካሁን አላዋጣም:: ኢትዮጵያንም አላፀናም:: ባይሆን ለድርድር ልባችንን እንክፈትና ለድርድር እንዘጋጅ ካልሆነ ጦርነት የሚባል ቅርጫት ውስጥ ብቻ የኢትዮጵያን እጣ ፋንታን ጨምረን ለድርድር የተዘጋጀ ሀይል አለመኖሩ ነው ህዋሃትና ኦነግ በኢትዮጵያ ጉዳ. ፈላጭ ቆራጭ የዛሬ 30 አመት የሆኑት:: ያሁኑም ጭፍንነት ጥላቻ እና ጀብደኝነትከ30 አመት በኃላ  የሚይስከትለው ተመሳሳይ ነገር ነው::
ህዋሃት 4 ኪሎ እንዲገባ ካልፈለግክ ጦርነቱን እዚህ ላይ ገትተህ ለውይይት ለድርድር ተቀመጥ:: ህዋሃት እና ኦነግ እንደ 1983 ኢትዮጵያን ብቆጣጠር ተጠይቂዎቹ የጦርነት አታሞ መቺዎችና አብይን ለማዳን የድርድር መድረክ ይዘጋ ያላችሁ በኢትዮጵያዊነት ካባ ያላችሁ ሰዎች ናቸው:: ለማንኛውም ሁሉ ነገር ወደ ጦር ግንባር የምትሉ ለህዋሃት ትልቅ ውለታ እየሰራችሁለት ነውና እርግጠኛ ነኝ ጌታቸው ረዳና ደብረፂዎን ያመሰግናችኃል::
የርስ በርስ ግጭት መሆኑን ክዶ ትግራይ በምትባል ሀገር እና በኢትዮጵያ መካከል የሚደረግ ጦርነት አድርገው ሲያቀርቡ የኖሩትም ኦነግ አገው እና በቅርብ ሌሎች ኢትዮጵያዊች መካከል ያለ የርስ በርስ ጦርነት መሆኑ አለማመን አሁን አይቻልም:: የርስ በርስ ጦርነት ደግሞ በጦርነት የሚፈታ ሳይሆን የፓለቲካ መፍትሄ ነው የሚሻው::
የህዋሃትን እና የኦነግን የ4 ኪሎ ግስጋሴ መግታት የሚፈልግ ኢትዮጵያዊ ካለ ውይይት ድርድር:: አሳደህ በለው ያንን አመፀኛ ተገንጣኝ ወንበዴ መድረሻ አሳጣው የሚል ዘፈንዛሬም እንዴት እንዘፍናለን? መች ነው ቆም ብለን ነገሮችን የምናጤነው?
እውነት ስንቶቻችን ማእከላዊ መንግስቱ የጥሞና ጊዜ ሊሰጥ ነው የወጣው ብለን የእውነት እናምናለን? ስንቶችችንስ የእውነት የህዋሃት ኃይል ወሎ የደረሰው ለታክቲክ ነው ብለን የእውነት እናምናለን?
ኸረ ግዴለም ጎበዝ ቀልድም ልክ እና አይነት አለው እኮ?!
እንዴት በሀገር እንዲህ ይቀለዳል? እንዴት ጥላቻና ኩራት ወጣቶችን ለጦርነት ለመማገድ በቂ ምክንያት ይሆናል? እንዴት ለአንድ አብይ አህመድ የስልጣን ጥማትና የልጅነት የንግስና ህልም ሲባል ሀገር የጦርነት አውድማ ይሆናል? ትኩረቴ በማእከላዊ መንግስቱ ላይ የሆነው ህዋሃትን ጠንቅቀን እናውቃለን ብሎ ሁሉም ስለሚምልና ስለሚገዘት ነጋሪ አያስፈልገውም በሚል ነው:: ለመለያየትም ቢሆን ተወያዩ::
ኢትዮጵያ ማለት ጋራ ሽንተረሩ ብቻ ሳይሆን አሁን ግፍ ዝመት የምትሉት ወጣትም ጭምር ነው:: በጦርነት የምታደቁት ኢኮኖሚም ጭምር ነው:: እኔ ከኢትዮጵያ ጎን ነኝ:: ሁሌም እሆናለሁ:: በኢትዮጵያ ስም ግን የምንንም ጥላቻ: የምንንም የስልጣን ጥማት: የምንንም እብሪት ተሸካሚ አልሆንም::
ጦርነት ብቸኛ አማራጫችን ነው የምትሉ እሱ የናንተ እርግማን ነው::
የኔ ኢትዮጵያ መነጋገር አቅቶአቸው ዝንተ አለማቸውን የሚገዳደሉ: ዘመኑን ያልዋጁ የግፋ በለው ፓለቲከኞች መናሀሪያ አይደለችም:: የኔ ኢትዮጵያ ለውይይት እድል የምትሰጥ አንተ ትብስ አንቺ ትብሽ ብላ ክፉውንም ደጉንም አብራ የምታሳልፍ ነች:: የኔ ኢትዮጵያ የልጆቿ የማያባራ ጦርነት የሰለቻት የታከታት ነች::
Filed in: Amharic