>

የተደበቀው የወልዲያ መያዝ ድብቅ እውነታ ሲገለጥ....!!! (ወንድወሰን ተክሉ)

የተደበቀው የወልዲያ መያዝ ድብቅ እውነታ ሲገለጥ….!!!

ወንድወሰን ተክሉ

 *….   ወልዲያ ከተያዘች ዛሬ ስድስተኛ ቀኗ ነው-ብልጽግና እና የብልጽግና ካድሬ ግን ቅጥፈታቸውን ውጠው ጸጥ አሉ እንጂ መያዟን መግለጽ አልፈለጉም፣! ለመሆኑ የወልዲያን መያዝ መደበቅና ማፈን ለምን አስፈለገ??እስከ መቼስ ነው እውነትን እየካዱ የሚያደናግሩን???
 
*…. እነዚህ ታንኮች በወያኔ አባባል “የተማረኩ!”
እውነታው ግን ለወያኔ የተሸጡ (በማፈግፈግ ስም ጥለውላቸው የወጡ) ናቸው!
በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ እጅግ በሚያስጩንቅ ስሜት ውስጥ ሆኜ የዘገብኩትን የወልዲያን በወያኔ እጅ የመያዝ ዜናን ሁሉም እንደ ጆፌ አሞራ እየተጠራራ በውግዘት ሲረባረብ እውኑትም የወልዲያ መያዝ ውሸት ሆኖ እኔ ልቅና ህዝቤ ነጻ ይሁን ብዬ እስከመመኘት ብደርስም የግሪሳው ጩህት እውነትንና ሀቅን መሰረት የደረገ ሳይሆን ምኞትን እና የአቢይንና የብአዴንን ፕሮፖጋንዳን መሰረት የደረገ ነበርና የእኔው እማልወደው የወልዲያ መያዝ ዜና እና መረጃ ትክክለኛና እውነተኛ ሆኖ ሲገኝ የእንፋሽ አጎንባሹ ግሪሳው መንጋ ጩህት ግን መሰረተቢስ ቅጥፈት ሆኖ ተገኘ።
ግን ለምን???
ለኡኔ እነዚህ ታንኮች  በመከላከያ ተብዬው  ለወያኔ ተቸብችበው የተሸጡ በወያኔ አገላለጽ ግን ተዋግታ  የማረከቻቸው  ከወልዲያ ህዝብ ጋር በወያኔ ኡጅ የገቡ ናቸው።
እኔን የሚያቃጥለኝ በመከላከያ ተብዬው ገልቱ አሻጥረኛ ወልዲያ ላይ ለወያኔ ስለተሸጡት ታንክና ብረት ለበስ የጦር መሳሪያዎች ጉዳይ ሳይሆን ምትክና እማይተመን ዋጋ ያለውን የወገኔን የወልዲያን ህዝብ መሸጥ ጉዳይ ነው እሚያበግነኝ እንጂ የብረቱ መቸብቸብ አይደለም።    ከሁሉ በላይ እጅግ አሳዛኙና አስደናቂው ጉዳይ የወልዲያን በጠላት መያዝ ስንናገር ከብልጽግና ካድሬዎች ጫጫታ ይልቅ የወልዲያ ልጅ ነኝ የወሎ ልጅ ነኝ አሁን ደውዬ መረጃ አግኝቻለሁ እኔ የምኖረው ወልዲያ ነው እያሉ ሲበጠረቁ የነበሩ ደናቁርት ብአዴናዊያን ከርሳቸውን አስበልጠው ስለአጠቃላይ የወልዲያ ህዝብ ስቃይ ሲደብቁ ማየቴ ነው ትንሽ አስገርሞኝ የነበረው።    ለምንድነው ሀቅን እንዲህ ቀብሮ መደበቅ የተፈለገው??? ለምንድነው የአካባቢው ተወላጅ ነኝ ባይች በወገናቸው ደምና ስቃይ በመነገድ የወልዲያ ህዝብ ያጋጠመውን መጥፎ ሁኔታ በህዝብ እንዳይታወቅ ለማፈን ሲረባረቡ የነበረው??? ማነው በሽታውን ደብቆ መዳን የቻለ?? ዛሬ አማራን ወጥሮ ካሰረው ካቴና ውስጥ አንዱና ዋነኛው የአቢይን ቅጥፈታዊ ፕሮፖጋንዳ አስተጋቢ ሆኖ መገኘት ነው።  ይህ ማለት አንድ መኖሪያ ቤቱ በእሳት እየተቃጠለ ያለን ሰው ቤት በእሳት ተያይዧል ብትለው የምን እሳት ነው የምታወራው ቤቴ አይደለም እሳት ቅዝቃዜ ነው ያለበት ብሎ እየሞገተ በእሳት በእሳት በሚነደው ቤት ውስጥ ልተኛ ብሎ በሩን እንደሚዘጋብህ እብድ ወይም እራሱን በራሱ ገዳይ ሰው እነዚህ የወልዲያና አካባቢው ልጆች ነን ባዮች የወልዲያ መከበብና ብሎም መያዝ ሲናገር አንተ ችግር ጠሪ ወልዲያ ሰላም ናት እያሉ እውነትን ለማዳፈን ነጣራቸው መልስ ያላገኘሁለት አሳዛኙ ገጽታ ነው።።  እውነት አርነት ያወጣችኋል እንዳለው ኢየሱስ እውነት የመፍትሄዎች ሁሉ ቁልፍ መነሻ ነችና ስለምን እውነትን ሸሽተን በሀሰት ላይ መንጠልጠልን እንደቱያያዝነው እራሳችንን መጠየቅ የእውነት እፍቃሪና የእውነት እክባሪ መሆን ህገባናል። በሀሰት እምንገነባው በሙሉ የእምባይ ካብ ኡንጀ መሰረት ያለው ግንብ አይደለምና ሁላችንም ከእውነት ጋር የታረቅን እንሁን። ወያኔ በወልዲያ ከተማ ከመሰንበቱና ከመላመዱም የተነሳ ህዝቡን በአደባባይ ከተማ ውስጥ ሰብስቦ የማወያየትን ስራ ሲሰራ ቢታይም መንግስት ተብዬው ግን እስካሁን የወልዲያን መያዝ ትንፍሽ ብሎ የገለጸው ነገር የለም።
Filed in: Amharic