>

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል “በጸረ ሰላም ኃይሎች” ላይ የማያዳግም እርምጃ እንዲወሰድ ትእዛዝ ሰጠ....!!! (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል “በጸረ ሰላም ኃይሎች” ላይ የማያዳግም እርምጃ እንዲወሰድ ትእዛዝ ሰጠ….!!!

ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከዛሬ ቅዳሜ ነሐሴ 8 ጀምሮ ሁሉም የጸጥታ አካላት “በክልሉ ሽብር ለመፍጠር በሚንቀሳቀሱ ጸረ- ሰላም ኃይሎች” ላይ የማያዳግም እርምጃ እንዲወሰዱ ትዕዛዝ አስተላለፈ። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ የሚገኙ የደቡብ፣ ሲዳማ እና ጋምቤላ ክልል ልዩ ኃይሎችም እርምጃ በመውሰድ ስራው ላይ እንደሚሳተፉ የክልሉ የሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዮት አልቦሮ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
የእርምጃ ትዕዛዙ የተላለፈው፤ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ትላንት አርብ ምሽት ባወጣው መግለጫ ነው። የቢሮው መግለጫ፤ በክልሉ በመተከል፣ ካማሺ እና አሶሳ ዞኖች ሲፈጸሙ የቆዩ ጥቃቶች ጀርባ የህወሓት እጅ አለበት ሲል ወንጅሏል። የቢሮው ኃላፊም፤ ህወሓት የክልሉን ሰላም ለማደፍረስ “ማስተር ማይንድ ሆኖ እየሰራ ነው” ሲሉ የሚመሩትን መስሪያ ቤት ክስ አጠናክረዋል።
ቢሮው መግለጫ “የጥፋት ቡድን” በሚል በተደጋጋሚ የተጠቀሰው ህወሓት፤ በክልሉ ተጨማሪ ጥቃቶች ለመፈጸም በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑም ተገልጿል። “ክልሉ ከሱዳን ጋር ሠፊ ድንበር የሚጋራ እና ጠረፋማ መሆኑን እንደምቹ ሁኔታ በመጠቀም፤ አሁንም ይህ አሸባሪ ቡድን በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ትልቅ ቀውስ ለመፍጠርና ተጨማሪ ጉዳት ለማድረስ አባላቱን ማሰማራቱ ተደርሶበታል” ሲል የሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ አስታውቋል።
“ከዚህ በኋላ የክልሉ መንግስት እነዚህን ጸረ-ሰላም ኃይሎች የሚታገስበት ጊዜ አልቋል” ያለው የቢሮው መግለጫ፤ “በክልሉ ሽብር ለመፍጠር የሚንቀሳቀሱ” በተባሉ ኃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ ትዕዛዝ አስተላልፏል።
ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦
Filed in: Amharic