>

ዘመቻው ‹‹የህልውና›› ነው...!!! (ዮሀንስ መኮንን)

ዘመቻው ‹‹የህልውና›› ነው…!!!

ዮሀንስ መኮንን

በዓለማችን ላይ 233 መንግሥታ ሲኖሩ 77ቱ የበለጸጉ፣ 109ኙ መካከላኛ ገቢ ያላቸው እና 47ቱ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት ናቸው፡፡ ከ47ቱ ድሃ ሀገራት መካከል 28ቱ ደግሞ በፍጹም ድህነት ውስጥ የሚማቅቁ ናቸው፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከመጨረሻዎቹ 28 የድሃ ድሃ ሀገራት ዘርዝር ውስጥ ትገኛለች፡፡
ደረጀ ፈይሳ ‹‹Aid negotiation: the uneasy ‘‘partnership’’ between EPRDF and the donors” በሚል ርእስ ባሳተሙት ጥናት እናዳረጋገጡት ትህነጎች ኢህአዴግ የሚባለውን ፓርቲ በመሩበት ከ1984 ዓ.ም. ጀምሮ 26 ቢሊዮን ዶላር (ከ1.17 ትሪለዮን ብር በላይ) በእርዳታ ስም ተቀበልዋል፡፡ ይህ የእርዳታ መጠን ሀገራችን ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ከኢንዶኔዢያ በመቀጠል ሁለተኛዋ ከፍተኛ እርዳታ ገንዘብ ተቀባይ ሀገር አድርጓታል፡፡ ቀጥሎ የሚነሳው ጥያቄ ‹‹ይህን ያህል ዶላር የት ገባ?›› የሚለው ይሆናል፡፡
ከሦስት ዓመታ በፊት ተራነስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ባስነበበው ሪፖርት የግሎባል ፋይናንስ ኢንተለጀንስ (GFI) መረጃዎች በመንተራስ አንዳስታወቀው ከምርጫ 97 ባኋላ በነበሩት 10 ዓመታት ውስጥ ብቻ ኢትዮጵያ 26 ቢሊዮን ዶላር (ከ1.17 ትሪለዮን ብር በላይ) ተዘርፋለች፡፡ ይህን ያህል ሀብት ያውም በድህነት ከምትማቅ ሀገር ሲዘረፍ ዋንኞቹ ሌቦች እና የሌቦች ከለላ ሰጪዎቹ የትህነግ ቁንጮ ባለሥልጣናት ነበሩ፡፡
ከሦስት ዓመታ በፊት ኢትዮጵያውያን ከዳር እስከዳር ባቀጣጠሉት ተቃውሞ የትህነግ ሰዎች ከሥልጣን ተባረው ወደ መቀሌ ሸሽተው ሲደበቁ የኢትዮጵያ ህዝብ ‹‹የዘረፋችሁትን (1.17 ትሪልየን ብር) መልሱልኝ›› ሳይላቸው የዘረፉትን ሀብት አርፈው እንዲበሉ የ‹‹ወንዶች በር›› ሰጥቷቸው ነበር፡፡ ኦሮሞዎች ሲተርቱ  ‹‹መስረቅ የለመደ እጅ ተቆርጦም ይንቀሳቀሳል›› እንደሚሉት እንዳለመታደል ሆኖ የትህነግ ሰዎች ሀገሪቱን እርቃኗን አስቀርተው የዘረፉትን ሀብት ከልጅ ልጆቻው ጋር ቁጭ ብለው ከመብላት ይልቅ ጥጋብ አላስችል ብሏቸው በድህነት እርቃኗን ያስቀሯትን ሀገራችንን ኢትዮጵያ እንደገና ለመውጋት ጦር ሰብቀው መጥተዋል፡፡
ትህነጎች የከፈቱት ጦርነት አንድም በተደጋጋሚ በአደባባይ ሲናገሩት እንደተደመጠው ‹‹እስከ ሲኦልም ቢሆን ወርደን ኢትዮጵያ እናፈርሳታለን›› ብለው በተማማሉት መሠረት ከደማቸው የተዋሃዳቸው የኢትዮጵያ ጥላቻ ሲሆን አንድም ሳይሠሩ እና ሳይደክሙ ኪሳቸውን ይሞሉበት የነበረው የዘረፋ ሱስ ነው፡፡
በእኔ አመለካከት ኢትዮጵያውያን ፊት ለፊታችን የተደቀነው ግልጽ ጥያቄ ይህ ነው!  ኢትዮጵያ እንደ ሀገር እድተፈርስ እና የቀራት ጥቂት ጥሪት (እርሱም ካለ ነው) ሙልጭ ተደርጎ ዳግመኛ እንዲጋጥ እፈቅዳለን ወይስ አንፈቅድም? መልሱ ከሁላችንም ይጠበቃል። ምክንያቱም ጉዳዩ የመሪዎች ወይንም የሚመሩት ፓርቲ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህልውና ጉዳይ ነው።
ዘመቻው ‹‹የህልውና ነው›› የተባለው በምክንያት ነው፡፡
Filed in: Amharic