>

የኢትዮጵያ የህልውና አደጋ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያኖችን አስሮ ማሰቃየት ነው...!!! (ጎዳና ያእቆብ)

የኢትዮጵያ የህልውና አደጋ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያኖችን አስሮ ማሰቃየት ነው…!!!

ጎዳና ያእቆብ

 

 በአገራቸው ላይ ግዞተኛ ማድረግ ነው:: ኢትዮጵያ የምትፈርሰው ልጆቿን አስራ ስታሰቃይ ስታንገላታ ነው:: ሎሌና አገልጋዮች ሰልጥነው ጌታና ቀጣሪ የሆኑ ዜጎችን በማን አለብኝነት እንኳን የዜግነት ቀርቶ የሰብአዊነት ነፃ የመሆንና ፍትህ የማግኘት መብታቸውን ሲነፍጋቸው ነው:: 
 
ግፍን እንጂ ግፈኛን አንፈራም የሚሉ የከተማ ባህታዊን ሽብርተኛ ብለው ሲያስሩና ግፍ ሲፈፅሙ ነው:: 
 
ምስክር ከመጋራጃ ጀርባ ካላደረግን ብለው አለም አቀፍ የእስረኞች አያያዝ ውልን ሲያፈርሱ ነው:: 
 
ትላንት በኢህአዴግ ቀዳማዊ ዛሬም በኢህአዴግ ዳግማዊ (ብልፅግና) እነ እስክንድር ነጋ ቀለብ ስዩም ስንታየሁ ቸኮል አስካለ ደምለውን እንደትላንቱ ሁሉ ዛሬም ሲያንገላቱ ነው:: 
 
በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የህሊና እስረኞች በብልፅግና ዘመን አሉ:: 
 
ነፃ እርምጃ ኦሮሚያ በሚባል ክልል ላይ በአዋጅ እያስወሰዱ ነው:: 
 
ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ እንዲሉ ትላንት አሸባሪ ነበርን ይቅር በሉን ብለው ደጉ የኢትዮጵያ ሕዝብ 27 አመት ያሰቃዩአቸውን የኢህአዴግ ግንባርና አጋሮችን ይቅር ቢሉም በለመዱት የአሸባሪነት ባህሪ ንፁኃንን በፓለቲካ አመለካከታቸው ብቻ አስሮ እያሰቃየ ነው:: 
 
ለዚህ ነው በኢህአዴግና በኢህአዴግ መካከል እርከን አላወጣም የምለው:: ህዋሃትም ደህዴንም ኦህዴድም መራው ኢህአዴግ ያው ኢህአዴግ ነው::  
 
አጀንዳ እየፈጠሩና ቀውስ እየፈጠሩ አይናችንን ከዲሞክራሲ ከፍትህ ከእኩልነት (ተረኛነት ሳይሆን) ላይ አይናችንን ነቅለን መጡላችሁ መጡብህ ሊሉን ቢፈልጉም አይናችንን ከግባችን እሱም ለዜጎቿ ምቹ የሆነች ኢትዮጵያና ከበለፀገ ኢትዮጵያዊነት ላይ አንነቅልም:: 
 
ፍትህ ለንፁኃን! ድል ለዲሞክራሲ!!!
Filed in: Amharic