>

በአዋሽ ሰባት ኪሎ ከተማ በእስር ላይ የቆዩ አራት ጋዜጠኞች ተፈቱ...!!! (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

በአዋሽ ሰባት ኪሎ ከተማ በእስር ላይ የቆዩ አራት ጋዜጠኞች ተፈቱ…!!!

ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

በአፋር ክልል አዋሽ ሰባት ኪሎ ከተማ በሚገኝ የፖሊስ ማሰልጠኛ ካምፕ ለ49 ቀናት በእስር ላይ የቆዩት አራት የኢትዮ ፎረም እና የአውሎ ሚዲያ ጋዜጠኞች በዋስትና ተፈቱ። በዛሬው ዕለት ከእስር የተለቀቁት ጋዜጠኞች የ“ኢትዮ ፎረም” አዘጋጁ ያየሰው ሽመልስ እና ባልደረባው አበበ ባዩ፣ የአውሎ ሚዲያ ዋና አዘጋጅ በቃሉ አላምረው እንዲሁም በሚዲያው በተንታኝነት ይሳተፍ የነበረው ፋኑኤል ክንፉ ናቸው።
የአራቱን ጋዜጠኞች የምርመራ የጊዜ ቀጠሮ ጉዳይ ሲመለከት የቆየው የአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ፍርድ ቤት፤ እያንዳንዳቸው ተጠርጣሪዎች አምስት ሺህ ብር ዋስትና አስይዘው እንዲፈቱ ውሳኔ አሳልፎ የነበረው ከትላንት በስቲያ ሰኞ በዋለው ችሎት ነበር። የጋዜጠኞቹ ቤተሰቦች ለዋስትና የተጠየቀውን ገንዘብ የዚያኑ ዕለት ከፍለው ቢያጠናቅቁም፤ ተጠርጣሪዎቹ ላለፉት ሁለት ቀናት ሳይፈቱ ቆይተዋል።
ሆኖም በዛሬው ዕለት ጠዋት ሁለት ሰዓት ገደማ፤ አራቱን ጋዜጠኞች ጨምሮ ስምንት ተጠርጣሪዎች በእስር ከቆዩበት የአዋሽ ሰባት ኪሎ ከተማ የፖሊስ ማሰልጠኛ ካምፕ መፈታታቸውን የቀድሞው የ“ሰንደቅ” ጋዜጣ ምክትል ዋና አዘጋጅ ፋኑኤል ክንፉ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። ከእስር የተለቀቁት ጋዜጠኞች ከረፋዱ አምስት ተኩል ገደማ አዲስ አበባ መግባታቸውንም ገልጿል።
ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2021/4302/
Filed in: Amharic