>

የሳዑዲ አረቢያ መንግስት «ሕገ-ወጥ» በማለት ኢትዮጵያዉያንን በገፍ ማጋዟን ቀጥላለች...!!! (ዶቸ ቬለ)

የሳዑዲ አረቢያ መንግስት «ሕገ-ወጥ» በማለት ኢትዮጵያዉያንን በገፍ ማጋዟን ቀጥላለች…!!!

ዶቸ ቬለ

*…  የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ኢትዮጵያዉያን ስደተኞችን በጅምላ መያዝና ማሰር ከጀመረበት ካለፈዉ ሐምሌ ጀምሮ በሶስት ሳምንታት ጊዜ ዉስጥ ከ40 ሺሕ የሚበልጡ ኢትዮጵያዉያንን ወደ ሐገራቸዉ ልኳል፤ በየሳምቱ ሶስቴ በሚደረግ በረራ በሳምንት አንድ ሺሕ ኢትዮጵያዉያን ሐገራቸዉ ይገባሉ
ሳዑዲ አረቢያ ኢትዮጵያዉያንን ማጋዟን ቀጥላለች
የሳዑዲ አረቢያ መንግስት «ሕገ-ወጥ» በማለት በየማቆያ ማዕከሉ (እስር ቤቶች) የያዛቸዉን ተጨማሪ ኢትዮጵያዉያን ስደተኞችን ወደ ሐገራቸዉ መላክ ጀመረ።የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ኢትዮጵያዉያን ስደተኞችን በጅምላ መያዝና ማሰር ከጀመረበት ካለፈዉ ሐምሌ ጀምሮ በሶስት ሳምንታት ጊዜ ዉስጥ ከ40 ሺሕ የሚበልጡ ኢትዮጵያዉያንን ወደ ሐገራቸዉ ልኳል።በጂዳ የኢትዮጵያ ቆስላ ምክትል ኃላፊ ነብዩ ተድላ ዛሬ ለዶቸ ቬለ እንደገለፁት ደግሞ እስካሁን በተለያዩ የሳዑዲ አረቢያ ማቆያ ጣቢያዎች የታሰሩ ኢትዮጵያዉያን ከዛሬ ጀምሮ ወደ ሐገራቸዉ ይላካሉ።አቶ ነብዮ አክለዉ እንዳሉት የኢትዮጵያና የሳዑዲ አረቢያ መንግስታት ከፍተኛ ባለስልጣናት ባደረጉት ስምምነት መሠረት በየሳምቱ ሶስቴ በሚደረግ በረራ በሳምንት አንድ ሺሕ ኢትዮጵያዉያን ሐገራቸዉ ይገባሉ።ስደተኞቹን ወደ ሐገራቸዉ መመለሱ ዛሬ ከሪያድ ሳዑዲ አረቢያ ተጀምሯል።በተለያዩ የሳዑዲ አረቢያ ማቆያ ጣቢያዎች የሚገኙ ኢትዮጵያዉን ስደተኞችን ብዛት ግን «በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ» ከማለት በስተቀር ትክክለኛዉ ቁጥር እንደማይታወቅ አቶ ነብዩ ገልጠዋል።የሳዑዲ አረቢያ ፀጥታ አስከባሪዎች መኖሪያ ቤቶችን ጭምር እየሰበሩ ኢትዮጵያዉያንን በጅምላ የመያዝ ዘመቻ በመጠኑም ቢሆን መቀነሱ ተዘግቧል።አቶ ነብዩ እንዳሉት ደግሞ ፀጥታ አስከባሪዎች መኖሪያ ፍቃድ ያላቸዉ ኢትዮጵያዉያንን መያዛቸዉንም፣ ካሰሩ በኋላ አሻራ እያነሱ መልቀቃቸዉን ቀንሷል።የሳዑዲ አረቢያ መንግስት በኢትዮጵያዉያን ላይ የከፈተዉን የመያዝ፣የማሰርና የማጋዝ ዘመቻን «ፖለቲካዊ» በማለት የሚወቅሱ አሉ።ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ የሚኖሩና የሚሰሩ ኢትዮጵያዉያዉን ስደተኞች ለየቤተሰቦቻቸዉና ለሐገራቸዉ ጠቀም ያለ ገቢ ያስገኛሉ።
Filed in: Amharic