>
5:13 pm - Sunday April 18, 8877

ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው ታሰረ !  ባልደራስ

ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው ታሰረ ! 

የምስክር አሰማም ሂደት ለጥቅምት ተቀጠረ ! 
ባልደራስ

*..  በጋዜጠኞች ላይ የሚደረገው አፈና ከግዜ ወደግዜ ከእለት ወደ እለት የጠነከረ ነው። አቶ ታዲዮስ ታንቱ ከእውነታቸው ጋር ዛሬም እስር ላይ ናቸው። ሌሎችም እንዲሁ። አንዳንዶችን በእጅ አዙር ከስራው ለማራቅ እየተደረገ ያለውን ሸፍጥ እየታዘብን ነው ። 
   በእነ እስክንድር የክስ መዝገብ ፤ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጸረ ሽብርና ሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት፤  ከችሎት ዘገባ ጋር በተያያዘ ጠበቃ ቤተማርያም አለማየሁ  ፣ ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው እንዲሁም አሐዱ ራዲዮ ” የተሳሳተ እና  ዘገባ እና ጽሁፍ ” በማቅረቡ እና ችሎት መድፈር ህግ ተላልፋችኋል  በማለት  ከፍተኛ ፍርድ ቤት  በፖሊስ በላከው መጥሪያ መሰረት ተጠርጣሪዎች  ዛሬ ፍ/ቤት ቀርበዋል።
   ፍ/ቤቱ የክስ ዝርዝር በችሎት ላይ እንደገለጸው 1ኛ ተጠሪ ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው ” መንግሥት በእነ እስክንድር ነጋ ላይ የመሰረተው ሀሰተኛ ክስ በአስቸኳይ ይቋረጥ ” በሚል የፍርድ ቤት የዳሰሰ ጽሁፉ ውስጥ የተሳሳተ መረጃ ተላልፏል በማለት ሲሆን።
2ኛ እና 3ኛ ተከሳሽ ጠበቃ ቤተማርያም አለማየሁ በእነ እስክንድር የክስ መዝገብ ከአሐዱ ራዲዮ ጋር ቃለ መጠይቅ ባደረጉበት  ወቅት የሰጡት አስተያየት ጋር ተያይዞ ” ችሎት የፓለቲካ ችሎት ነው” የሚል አንድምታ ያለው ቃለ መጥይቅ፤ አድርጋችኋል በማለት “የችሎቱ ገለልተኝነት ” ጥያቄ ውስጥ የሚያስግባ ዘገባ ተሰርቷል በማለት ፍ/ቤቱ የክስ ዝርዝሩን በችሎት ገልጿል ።
1ኛ ተጠሪ ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው የዳሰሳ ጽሁፉን እንደፃፈ ፣ በችሎት ሂደት የታዘበውን መዘገቡ እና ለዘገባው የተለያዩ የመረጃ ምንጮች እንደተጠቀመ ፤ እንዲሁም የመረጃ ምንጮችን ከሙያው አንፃር ለመግለፅ እንደማይገደድ ለፍ/ቤቱ  ምላሽ ሰጥቷል ። የእነ እስክንድር ጠበቃ የሆነው ቤተማርያም አለማየሁ በእነ እስክንድር ጉዳይ ከአሐዱ ራዲዮ ጋር ቃለ መጠይቅ ማድረጋቸውን በማመን በቃለ መጠይቅ ወቅት የሰጠውን አስተያየት ሙሉ ቃል በአሐዱ የቀረበ ባይሆንም ፣ አቶ ዛዲግ አብርሃም ለቢቢስ በሰጡት ቃለ መጠይቅ “የፖለቲካ እስረኛ” የለም ማለታቸውን አስመልክቶ ከእሳቸው ተቃራኒ ሃሳብ ገልጫለው ይህ ደግሞ ከችሎት እና ከዳኞች ጋር በተያያዘ ፤ በተለይ ከዚህ ችሎት ጋር በቀጥታ የተገናኘ አስተያየት አልሰጠሁም በማለት ምላሽ ሰጥተዋል ።
አሐዱ ራዲዮ በተወካይ (በጠበቃ አማካኝነት) በሰጠው ምላሽ ከጠበቃ ቤተማርያም አለማየሁ ጋር ቃለ መጠይቅ መደረጉ ፣ ሆኖም በኤዲቶሪያል መሉ ዘገባው አለመታየቱን ለችሎት አስረድቷል ።
ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን ምላሽ ከሰማ በኋላ ፤ 1ኛ ተከሳሽ ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው ጥፋተኛ በማለት ውሳኔ የሰጠ ሲሆን ፤ ዛሬ ታስሮ በነገው ዕለት የቅጣት ማቅለያ ይዞ እንዲቀርቡ ትዕዛዝ በመስጠት ለነገ ነሐሴ 14 ቀን 2014 ዓ.ም ጠዋት ለብይን ቀጠሮ ሰጥቷል ።
ጠበቃ ቤተማርያም አለማየሁ ችሎት በነፃ አሰናብቷቸዋል። አሐዱ ራዲዮን ችሎት በቢሮ እንደሚያናግራቸው በመግለጽ የክስ መዝገቡን አቆይቶታል።
ይህ ችሎት የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ ላይ  የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች በግልፅ ችሎት ይሰሙ በማለት ፤ የምስክሮች አሰማም ሂደት የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ችሎት የሰጠው ውሳኔ ተፈፃሚ እንዲሆን በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት
ምስክሮችን ለመስማት  ጥቅም 4 ፣ 5 ፣ 8 ፣ 9 እና 10 ዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን አቅርቦ እንዲያሰማ ትዕዛዝ ሰጥቷል ።
በጋዜጠኞች ላይ የሚደረገው አፈና ከግዜ ወደግዜ ከእለት ወደ እለት የጠነከረ ነው። አቶ ታዲዮስ ታንቱ ከእውነታቸው ጋር ዛሬም እስር ላይ ናቸው። ሌሎችም እንዲሁ። አንዳንዶችን በእጅ አዙር ከስራው ለማራቅ እየተደረገ ያለውን ሸፍጥ እየታዘብን ነው ።
አንዳንዶችን ደግሞ ዘገባችሁ መንግስትን አልደገፈም  በሚል ለእስር እየተዳረጉ ነው ። ዛሬ ጌጥዬ ያለው ለእስር የተዳረገው ከዚህ ውቅር ነው ።
ጌጥዬ ያለው እነስክንድር ከታሰሩ ጀምሮ በየችሎቱ በመገኘት የታዘበውን ሳይጨምር ሳይቀንስ በመዘገብ በፍርድ ችሎት ላይ ላልተገኘን የፍርድ ቤቱን ድባብ እና ሂደት እንድናይ በማድረግ ይታወቃል ። ዛሬ ምን ተገኝቶ ለእስር ተዳረገ?
ሙያውን ለማዳፋትና ጋዜጠኞችን በአጠቃላይ የመንግስት አጎብዳጅ ለማድረግ ፍርድ ቤቶችም የድርሻቸውን እየተወጡ ነው። ለነገሩ ከዚህ የላቀ ምን ይጠበቃል?
ለማንኛውም ጌጥዬ ያለው ለእውነት ቆርጦ አደባባይ የወጣ ስለሆነ ብታስሩትም እውነትን እያሰራችሁ መሆኑን ይነግራችኋል እናም ፍቱት ።
Filed in: Amharic