>
5:31 pm - Tuesday November 12, 2391

"አማራ ክልል" እና "አፋር ክልል" እንጂ ትግራይ ክልል ውስጥ አንድም ጦርነት የለም!  (አቻምየለህ ታምሩ)

“አማራ ክልል” እና “አፋር ክልል” እንጂ ትግራይ ክልል ውስጥ አንድም ጦርነት የለም! 

አቻምየለህ ታምሩ

*…. BBC News Amharic, VOA Amharic, DW Amharic,  Addis Standard,  SBS Amharic,  ወዘተ አይነት ሜዲያዎች ዛሬም የሚያላዝኑት ስለ ትግራይ ጦርነት ነው። 
ለመሆኑ ባሁኑ ወቅት በትኛው የትግራይ አካባቢ ነው ጦርነት እየተካሄደ ያለው?  ከሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. ወዲህ ትግራይ ውስጥ ጦርነት የሚካሄድበት ቦታ አለ? ከሌለ የትግራዩ ጦርነት ዘጠነኛ ወሩን ያዘ እያሉ ሕዝብን የሚዋሹት ከየት አምጥተው ነው? 
የትግራይ ጦርነት ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. ካበቃ በኋላ ትግራይ ውስጥ አንድ ጥይት ጮሆ አያውቁም። ጦርነት ባሕላዊ ጨዋታዬ ነው የሚለው ፋሽስት ወያኔ ግን  የትግራይ ጦርነት  ካበቃበት ከሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም.  በኋላ  ያለ ጦርነት መኖር ስለማይችል ከትግራይ ተሻግሮ “ከአማራ ክልል” አራት ዞኖችን ማለትም ሰሜን ወሎን፣ ዋግ ሕምራን፣ ደቡብ ጎንደርና ሰሜን ጎንደርን፤ ከአፋር ክልል ደግሞ ዞን አራት የሚባለውን ወርሮ ከያዘና የዘር ፍጅት፣ የጦር ወንጀልና በሰብዓዊ ፍጡር ላይ የሚፈጽሙ ዘግናኝ ጭካኔዎችን መፈጸምን እለታዊ ተግባሩ ካደረገ ከአንድ ወር በላይ ሆነው።
ለዚህ ማሳያ ይሆን ዘንድ፤  
1ኛ. በደብረ ታቦር፣ በወልድያና መሰል ከተሞች አካባቢ ከባድ መሳሪያና ሮኬት በተደጋጋሚ እያስወነጨፈ የፈጃቸው በርካታ የአንድ ቤተሰብ አባላትን፤
2ኛ. ቴሌግራፍ ያጋለጠውን በሰሜን ወሎ ሀብሩ ወረዳ አጋምሳ በሚባል ቦታ ድምጥማጡን ያጠፋውን የአንድ የገጠር ቀበሌና ቤት ለቤት እየተዘዋወረ የፈጃቸውን የአንድ መንደር በመቶ የሚቆጠሩ የአማራ አርሷደሮችን፤
3ኛ.  በአፋር ክልል በከተፈው ጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች ተጠልለውበት በነበረው በጋሊኮማ መጠለያ ጣቢያ  ላይ ባካሄደው የከባድ መሳሪያ ድብደባ  ከመቶ በላይ  የሚሆኑ ሕጻናትን ጨምሮ የፈጃቸውን በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጽሐን ዜጎችን መጥቀስ ብቻ ይበቃል።
ሆኖም ግን በተለይ በኢትዮጵያ ቋንቋዎች የሚጽፉት እንደ  BBC News Amharic, VOA Amharic, DW Amharic,  Addis Standard,  SBS Amharic,  ወዘተ አይነት ሜዲያዎች ዛሬም የሚያላዝኑት ስለ ትግራይ ጦርነት ነው። ይባሱኑ ትናንትና ዛሬ እያወጧቸው ባሉ ዘገባዎቻቸው   የትግራዩ ጦርነት ዘጠነኛ ወሩን ያዘ እያሉ ሌት ተቀብ በማላዘን ላይ ናቸው ።
ለመሆኑ ባሁኑ ወቅት በትኛው የትግራይ አካባቢ ነው ጦርነት እየተካሄደ ያለው? እነዚህ ሜዲያዎች የሚያውቁት እኛ ግን የማናውቀው ከሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. ወዲህ ትግራይ ውስጥ ጦርነት የሚካሄድበት ቦታ አለ? ከሌለ የትግራዩ ጦርነት ዘጠነኛ ወሩን ያዘ እያሉ ሕዝብን የሚዋሹት ከየት አምጥተው ነው?
በእነዚህ የምዕራብ ሜዲያዎች ውስጥ በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ለኢትዮጵያውያን ዘገባ እንዲሰሩ የተቀጠሩ አብዛኛዎቹ ጋዜጠኛ የወያኔ ግብረ በላዎችና የምዕራባውያን ቅጥረኞች [mercenaries] እንደሆኑ ብናውቅም  ከሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. ወዲህ አንድም ቦታ ጦርነት በሌለበት በትግራይ ውስጥ አሁንም ጦርነት እየተካሄደ እንደሆነ አድርገው ሜዲያዎቹ  24/7 ሲለፍፉ ሲውሉ የሚጣላ ኅሊና ያላቸውና ቤተሰቦቻችን ምን ይሉን ብለው የሚያስቡ  አንድና ሁለት  ለሀቅ የቆሙ እውነተኛ ጋዜጠኞች በነዚህ ሜዲያዎች ውስጥ እንዴት ይጠፋሉ?
24/7 የሚያግዙትና ያልተቋረጠ ሽፋን የሚሰጡት ፋሽስት ወያኔ “አማራ ክልል” እና “አፋር ክልልን” ወርሮ ስለሚያካሂደው የዘር ማጥፋት ጦርነት፣ የጦር ወንጀልና በሰብዓዊ ፍጡር ላይ የሚፈጽም ወንጀል ፋሽስት ወያኔ እየፈጸመ እንደሆነ እነዚህ ሜዲያዎች ዘገባ የሚሰሩት መቼ ነው? መቼስ ነው የአማራና የአፋርን ጦርነት በስሙ የሚጠሩትና የትግራይ ጦርነት እያሉ ያለ ስሙ መጥራታቸውን የሚያቆሙት?
Filed in: Amharic